በቀጣዩ የትምህር ዘመን ለተማሪዎች ትምህርት ቤት ምዝገባ ፋይዳ መታወቂያ መያዝ አስገዳጅ መሆኑ ተገለጸ
በቀጣዩ የ2018 ዓ.ም ትምህር ዘመን የተማሪዎች የትምህርት ቤት ምዝገባ፤ የልደት እና የፋይዳ ምዝገባ አስገዳጅ ቅድመ ሁኔታ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
የተማሪዎች የትምህርት ቤት ምዝገባ ማስጀመርያ በዛሬው ዕለት በይፋ የተጀመረ ሲሆን፤ በዚህም መሠረት ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በላይ የሆናቸው ሕጻናት በዘመቻ ምዘገባ እንደሚከናወን ተነግሯል።
ለዚህም የትምህርት ማህበረሰቡን እና የተማሪ ወላጆችን ከሚወክሉ አደረጃጀቶች ጋር ውይይት በዝግጅት ምዕራፍ መከናወኑ ተመላክቷል።
የፋይዳ ምዝገባ ቁጥር በአዲስ አበባ የመንግሥት ተቋማት አገልግሎት ለማግኘት በቅድመ ሁኔታነት የተቀመጠ ሲሆን፤ በከተማው ያሉ የመንግሥት ሠራተኞች የቅጥር እና ዝውውር እንዲሁም የደመወዝ አከፋፈል ስርዓት ከምዝገባ ስርዓቱ ጋር እንዲቀናጅ በአስገዳጅ ስርዓትነት ተቀምጧል፡፡
በዚህም መሠረት የከተማው ትምህርት ቢሮ የልደት እና የፋይዳ ምዝገባ የ2018 ዓ.ም የተማሪዎች የትምህርት ቤት ምዝገባ ቅድመ ሁኔታም እንደሆነ ይፋ አድርጓል።
ላለፉት ወራት በተፈጠረው የጋራ ንቅናቄ በከተማው ከ2 ነጥብ 1 ሚልዮን በላይ አዲስ ተመዝጋቢ መመዝገብ መቻሉ የተገለጸ ሲሆን፤ ከዚህም ውስጥ 900 ሺሕ የሚጠጋው ምዝገባ በቀጥታ በሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ መዋቅር ጽ/ቤቶች የተደረገ ምዝገባ ተመላክቷል።
ትክክለኛ መረጃ የምትገኙበት የ 12ኛ
https://t.me/+esqs-EEENtxlM2Q8
Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
♨️ ♦️ @ethiouniversity1 ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1 ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1 ♨️
╚═══════════╝