ይግባኝ ምክረ ሕግ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Huquq


📞በስልክዎ ባሉበት ሆነ በማንኛውም ሕግ⚖️ነክ ጉዳዮች ላይ ነፃ🆓️የሕግ ምክር አገልግሎት የሚያገኙበት ገጽ! በነፃ እና በነፃነት ማወቅ፣ መረዳት እና ማብራሪያ በሚፈልጉባቸው ሕግ ተኮር ጉዳዮች ላይ ይግባኝ ይበሉ! በማንኛውም ሕግ ነክ ጉዳዮች ላይ እስኪገባዎት ድረስ ይግባኝ ይበሉ!⚖️

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Huquq
Statistika
Postlar filtri


ለተበዳይ ቤተሰቦች ስለመካስ
👉በወንጀል ሕግ ቁጥር 197 ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ እንደተመለከተው ለአንድ ሰው ቅጣቱን ለመገደብ ከሚያስፈልጉ መሠረታዊ ነገሮች መካከል አንደኛው “በሚቻለው መንገድ ሁሉ በጥፋቱ ያደረሰውን ጉዳት እንደሚክስ ወይም ለተበዳዩ እንደሚከፍል” ማረጋገጫ ማቅረብ አስፈላጊው ቅድመ ሁኔታ ነው።
👉ጥፋቱን ያደረሰው ግለሰብ ካሳ ሲክስ በሁለት ዓይነት መንገድ ሊክስ እንደሚችል ይታወቃል።
☝️ተበዳዩን መካስ
👉በዚህ ረገድ የሚደረገው ካሳ ምንም አሻሚነት የለም፤ በተፈጸመው የወንጀል ድርጊት የተጎዳውን ሰው በእርቅ ስምምነት ለደረሰበት ጉዳት ከበዳይ ወገን የሚሰጥና የሚከፈለው ካሳ ነው።
✌️የተበዳዩን ቤተሰቦች መካስ
👉ለተበዳይ ቤተሰቦች የሚሰጠው ካሳ በተፈጸመው የወንጀል ድርጊት ለደረሰባቸው በደል የሚከፈላቸው ካሳ ሲሆን ካሳው ለባለቤት፣ ለልጆች፣ ለወላጆች ወይም በሟች ገቢ ጥገኛ ሆነው ይኖሩ ለነበሩ የሚከፈል ካሳ ነው።
⚠️⚠️⚠️ይህ ካሳ ሲከፈል ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች፦⚠️⚠️⚠️
1️⃣ካሳ ከመክፈልዎት በፊት ካስ የሚከፍሏቸው ሰዎች የወራሽነት ማስረጃ ያላቸው መሆኑን ያረጋግጡ። ምክንያቱም ካሳውን ለመቀበል ብቁ ካልሆነ ላልተገባ ሰው ካሳ መክፈልዎት ቅጣቱን አያስገድብልዎትም።
2️⃣የእርቅ ውል ስምምነት ሳይፈጽሙ የካሳ ክፍያ ገንዘብ ክፍያ አይፈጽሙ።
3️⃣የእርቅ ውል ስምምነትዎን ጉዳዩ በምርመራ ላይ ያለ እንደሆነ ከፖሊስ የምርመራ መዝገብ እንዲሁም በክስ ሂደት ላይ ያለ እንደሆነ ከፍርድ ቤት መዝገብ ጋር እንዲያያዝልዎት ያድርጉ።
ይግባኝ መብት ነው
©️ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
☎️ 09 10 61 69 50
በማንኛውም የፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ


በድሀ ደንብ ክስ መመስረት

መሠረቱ
📌 በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 215 ላይ እንደተመለከተው በገንዘብ ሊተመኑ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ የሚቀርቡት ክሶች ሁሉ ዳኝነት ካልተከፈለባቸው በቀር ተቀባይነትን አያገኙም።
ግለሰቡ ለዳኝነት የሚከፍለው ገንዘብ የሌለው ከሆነ?
📌 የፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 467 ንዑስ አንቀጽ 2 ላይ “ማናቸውም ሰው ለሚያቀርበው ክስ የሚያስፈልገውን የዳኝነት ገንዘብ በሙሉ ወይም በከፊል ለመክፈል የማይችል መሆኑን ገልጾ ከዚህ በላይ ባለው ንዑስ ቁጥር በተነገረው ድንጋጌ መሠረት የነፃ ፋይል ከፍቶ ክስ ለማቅረብ እንዲፈቀድለት ለማመልከት ይችላል።” በማለት ይደነግጋል።
📌 በመሆኑም ለፍርድ ቤት ለዳኝነት የሚከፈል ገንዘብ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የሌለው ሰው ጉዳዩን በቅድሚያ በድሀ ደንብ እንዲታይለት በመጠየቅ ክሱን በማቅረብ መብን ማስከበር ይቻላል።
📌 ይህ ማለት ግን ግለሰቡ በክርክር ሂደት መሐል ሀብት ንብረት ያገኘ ከሆነ ወይም ፍርድ ቤት እንዲቀርብ በሰጠው ቀጠሮ ሳይቀርብ የቀረ እንደሆነ ወይም ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ንብረት ሦስተኛ ወገን ጥቅም ጥቅም እንዲያገኝበት ያደረገ መሆኑ ሲረጋገጥ ለዳኝነት እንዲከፍል የተተመነውን ከመክፈል የሚያስቀረው አይደለም።
ሂደቱ ምን ይመስላል?
📌 በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 468 ላይ እንደሰፈረው ከሳሽ ከሚያቀርበው መደበኛ ክስ ጋር በማድረግ በመሐላ ቃል በተደገፈ አቤቱታ ክሱ በድሀ ደንብ እንዲታይለት ከሚጠይቅ ማመልከቻ እና የሰነድ ወይም የሰው ማስረጃዎች ጋር በመሆን እንዲቀርብ ይደረጋል። በተጠየቀው አቤቱታ ላይም በቅድሚያ ተከሳሽ መልስ እንዲሰጥበት ይደረጋል።
ፍርድ ቤቱ ከሳሽ ያቀረበውን በድሀ ደንብ ክስ እንድመሰርት ይፈቀድልኝ አቤቱታን ውድቅ ያደረገው እንደሆነ ጉዳዬ ዳኝነት ሳይከፈልበት በነፃ ሊታይልኝ ይገባል በማለት ይግባኝ መጠየቅ የሚቻል ስለመሆኑ የፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት በቅፅ 6 በመዝገብ ቁጥር 23744 በሆነው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል።
በድሀ ደንብ ክስ ለመክፈት መሟላት ያለበት
📌 በድሀ ደንብ ክስ እንዲታይልዎት ከሚያቀርቡት ማመልከቻ ጋር
1️⃣ ከሚኖሩበት ወረዳ ለዳኝነት ሊከፈል የሚችለውን የገንዘብ መጠን ለመክፈል የማይችሉ ድሀ ስለመሆንዎት የሚያስረዳ ማስረጃ፤
2️⃣ ዳኝነት ለመክፈል የማይችሉ ስለመሆንዎት ሊያስረዱ የሚችሉ ቢያንስ 03 /ሦስት/ የሰው ምስክሮች ስም ዝርዝር።
ሆነ ብሎ ድሀ ሳይሆኑ ድሀ ነኝ ማለቱ ቅጣቱ
📌 አንድ ሰው ድሀ ሳይሆን ለፍርድ ቤት ሊከፈል የሚገባውን የዳኝነት ገንዘብ ላለመክፈል በማሰብ ብቻ በሐሰት ድሀ ነኝ ብሎ ድሀ አለመሆኑ እና ለዳኝነት ሊከፍል የሚችለው ገንዘብ ስለመኖሩ የተረጋገጠበት እንደሆነ በኢፌዴሪ የወንጀል ሕግ መሠረት ችሎቱ ተገቢ ነው በማለት በሚያምንበት የሕግ ድንጋጌ ከ06 /ስድስት/ ወራት ቀላል እስራት እስከ 7 /ሰባት/ ዓመት ሊደስ በሚችል ጽኑ እስራት ሊያስቀጣው ይችላል።
©️ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
☎️ 09 10 61 69 50
በማንኛውም የፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ




ክፍፍሉ እንዴት ይሆናል?
📌 ክፍፍልን በተመለከተ ግማሹ የባል ድርሻ ተለይቶ በዚህ ንብረት ላይ የሟች ልጆች የሚካፈሉት ሲሆን፤
📌 ግማሹን ድርሻ ሁለቱም ሚስቶች እኩል የሚካፈሉት ይሆናል።
📌 ከሁለት ሚስቶች አንደኛቸው ከሟች ልጆች ያልወለዱ እንደሆነ የወለደችው ሚስት ልጅ በራሱ ወይም በእናቱ ሞግዚትነት ግማሹን የሟችን ድርሻ በሙሉ የሚወርስ ይሆናል።
ይግባኝ መብት ነው!!!
©️ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
☎️ 09 10 61 69 50
በማንኛውም የፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ


በሴት አንቀጽ የተቀመጠው ለወንዶችም ተፈጻሚነት አለው።
📌በሀራችን ሁለት ትዳር መመስረት ለየትኛው ተጋቢ በሕግ የተከለከለና በወንጀል ጭምር የሚያስቀጣ ነው።
የኢፌዲሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 650 /1/
ማንም ሰው አስቀድሞ በሕግ በጸና ጋብቻ ታስሮ ሳለ ይኸው ጋብቻ ከመፍረሱ ወይም ከመሻሩ በፊት ሌላ ጋብቻ የፈፀመ እንደሆነ፤በቀላል እሥራት፣ ወይም ነገሩ ከባድ ሲሆን በተለይም ጥፋተኛው የራሱን እውነተኛ ሁኔታ በመሰወር ከርሱ ጋር ሁለተኛውን ጋብቻ የፈጸመውን ሰው አውቆ ያሳሳተ እንደሆነ፤ ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እሥራት ይቀጣል።

ነገር ግን
📌 ትዳሩ በሕግ አግባብ ፍቺ ሳይፈጸምበት ወይም ሳይሻር እንደጸና እያለ ባልየው ቢሞት በንብረት ክፍፍል ረገድ የሁለት ሚስቶች ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል? የሚለው አከራካሪ ነጥብ ነው።
📌 በሕግ አግባብ ከሁለት የአንደኛቸው ሚስቶች ትዳር እስካልፈረሰ ወይም እስካልተሻረ ድረስ በባልየው መሞት ምክንያት ትዳሩ የፈረሰ እንደሆነ ሁለቱም ሚስቶች ከትዳሩ በተፈሩት ንብረቶች ላይ እኩል መብት ይኖራቸዋል።
📌 ከትዳሩ በተገኙ ንብረቶች ላይ እኩል ድርሻ ሊኖራቸው የሚችለው ክርክር የሚደረግበት ንብረት በፈጸሙት ጋብቻ ወቅት የተገኘ እንደሆነ ብቻ ነው።
📌 ለምሳሌ 2ኛዋ ሚስት ከሟች ጋር ጋብቻዋን የፈጸመችው ከ2005 ዓ.ም ላይ የነበረ ከሆነ እና ክርክር የሚነሳበት ቤት የተሰራው ሟች ከመጀመሪያ ሚስቱ ጋር በ1989 ዓ.ም ሲጋቡ የሰሩት ቤት እንደሆነ 2ኛዋ ሚስት ከሟች ጋር ልጅ ያላቸው ካልሆነ በቀር በፈጸመችው ጋብቻ ወቅት ላልተፈጠረ ንብረት ምናልባት ከጋብቻዋ በኋላ በቤቱ ላይ ዓይነተኛ ለውጥ ከሌለ በስተቀር ድርሻዬ ብላ ልጠይቅ አትችልም።


ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተገልጋዮች
*********
በ3ኛ ሰበር ችሎት በወንጀል ጉዳይ ጉዳያችሁ እየታየ የነበራችሁ ባለጉዳዮች በሙሉ ከዚህ በታች የተዘረዘረው የመዝገብ ቁጥር ወደ 1ኛ ሰበር ችሎት የተቀየረ በመሆኑ ከሕዳር 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በየቀጠሮአችሁ በ1ኛ ሰበር ችሎት የምትስተናገዱ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡
❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️


ትርጓሜ
👉 በአጭሩ ይርጋ ማለት አንድ ሰው ከሌላ ሰው ላይ እንዲከበርለት የሚጠየቀውን መብት ሊጠይቅ የሚችልበት የጊዜ ገደብ ነው በማለት መግለጽ ይቻላል።
🤔 ለምሳሌ አንድ ሠራተኛ አሰሪው የመጋቢት ወር 2016 ዓ.ም ደመወዙን ሳይከፍለው ሲቀር ለምን አልተከፈለኝም? ብሎ ሲጠይቅ በቀጣይ ወር እንከፍልሃለን፤ ቢባልና በተባለው ጊዜ ሳይከፈለው ቢቀር ሠራተኛው ያልተከፈለውን ደመወዝ ይከፈለኝ ብሎ በሕግ አግባብ በ06 ወራት ውስጥ ካልጠየቀ ደመወዙን እንዳልፈለገው ተቆጥሮ ያልተከፈለውን ገንዘብ የመጠየቅ መብቱ በይርጋ /በጊዜ ገደብ/ የሚታገድ ይሆናል።
ዓላማው
👉 ይርጋ ሁለቱንም ወገኖች ለመጠበቅ የተቀመጠ የሕግ ጽንሰ ሃሳብ ሲሆን
መብቱን ለሚጠይቀው ወገን
☝️ ከሳሽ የሚሆነውን ወገን
📌 በጉዳዩ ላይ መብት አለን የሚሉ ሰዎች ዝንጉ ሳይሆኑ መብታቸውን በጊዜ መጠየቅ እንዲችሉ ለማድረግ ነው።
✌️ ተከሳሽ የሚሆነው ወገን
📌 ከሳሽ በፈለገው ሰዓትና ጊዜ ክስ እየመሰረተ እንዳያጉላላውና ዕለት ዕለት እየሰጋ እንዳይኖር ለመጠበቅ ነው።
ውጤቱ
📌 ይርጋ መብት አለኝ የሚለው ወገን ምንም እንኳን በጉዳዩ ላይ መብት ቢኖረው በጊዜ ባለመጠየቁ መብቱን ያሳጣዋል፤
📌 መብት የሌለውን ወገን ክርክር በተነሳበት ጉዳይ ላይ በጊዜ ባለመጠየቁ ከተጠያቂነት ነፃ ማድረግና በጉዳዩ ላይ ባለመብት የማድረግ ውጤት ይኖረዋል።
መብትዎን በጊዜ ይጠይቁ!!!
⚖️ይግባኝ መብት ነው!!!
©️ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
☎️ 09 10 61 69 50
በውስጥ መስመር በጽሑፍ በማንኛውም የሕግ ጉዳዮች ምክር ለመጠየቅ በዚህ @laws2016 አድራሻ መጠየቅም ይችላሉ።
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ


ሕገ ወጥ የሥራ
አታባረው ነገር ግን እንዲለቅ አድርገው!

መርሕ
📌 አሰሪው ሥራውን ለማከናወን በሚያስችለው መንገድ ሁሉ ሠራተኛውን ከአንድ የሥራ ቦታም ሆነ የሥራ መደብ በማዘዋወር ማሰራትን የሚከለክለው ድንጋጌ በአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ዓ.ም ላይ የለም።
📌 በሕጉ ላይ ስለ ዝውውር በግልጽ የተቀመጠ ድንጋጌ ከሌለ ድርጅቶች አንድን ሠራተኛ ከአንድ የሥራ መደብ ወይም የሥራ ቦታ ወደ ሌላ የሥራ መደብ ወም ቦታ ሲያዘዋውሩ መሠረት ሚያደርጉት በድርጅቱና በሠራተኞች መካከል የተደረገውን የሕብረት ስምምነት መሠረት በማድረግ ነው።
ዝውውር ሁለት ዓይነት ሊሆኑ ይችላሉ።
☝️ከአንድ የሥራ መደብ ወደ ሌላ የሥራ መደብ የሚደረግ ዝውውር
👉አንድን ሠራተኛ ይሰራበት ከነበረው የሥራ መደብ ወደ ሌላ የሥራ መደብ ቀድሞ ይከፈለው የነበረውን ደመወዝና ጥቅማጥቅም ባልቀነስ ሁኔታ የሚደረግ ዝውውር ነው።
የደመወዝና ጥቅማጥቅም ለውጥ ካለ ከደረጃ ዝቅ ማድረግ እንጂ ዝውውር ሊባል አይችልም።
✌️ ከአንድ የሥራ ቦታ ወደ ሌላ የሥራ ቦታ የሚደረግ ዝውውር
👉 አንድን ሠራተኛ በመደበኛነት ተቀጥሮ ይሰራበት ከነበረበት የሥራ ቦታ ወደ ሌላ የሥራ ቦታ ቀድሞ ይሰራበት በነበረው የሥራ መደብ ይከፈለው የነበረውን ደመወዝና ጥቅማጥቅም ባልቀነስ ሁኔታ የሚደረግ ዝውውር ነው።
ዝውውሩ ሕገ ወጥ ነው ሚባለው መቼ ነው?
📌 ዝውውሩ የተደረገው የሠራተኛው መደብ ባልሆነ እና ተመሳሳይነት በሌለው የሥራ መደብ ከሆነ፤
📌 አሰሪው ሠራተኛውን ያዘዋወረው ለድርጅቱ ጥቅም ሳይሆን ሆን ብሎ ለመጉዳት በማሰብ ያደረገው ዝውውር እንደሆነ፤
📌 ሠራተኛው የተዘዋወረው በአሰሪውና በድርጅቱ መካከል ከተደረገው የሕብረት ስምምነት ውጪ እንደሆነ፤
📌 አሰሪው ሠራተኛውን አዘዋውሬሃለውኝ ባለበት ደብዳቤ ላይ ምክንያቱን በግልጽ ያላስቀመጠ እንደሆነ እና በመሳሰሉት ምክንያቶች ነው።
ምን ማድረግ ይጠበቅበዎታል?
📌 የዝውውር ደብዳቤው እንደደረሰዎት በዝውውሩ ያላመኑበት እንደሆነ ወዲያውኑ ክስ በማቅረብ ዝውውርዎትን ያሳግዱ፤
📌 ዝውውርዎትን በተመለከተ ለጊዜው ዕግድ ያልተሰጠ እንደሆነ ወደ ተዘዋወሩበት የሥራ መደብም ሆነ ቦታ በመገኘት በሥራ ገበታዎት ላይ ይገኙ፤ ምክንያቱም በተከታታይ 05 የሥራ ቀናት የሥራ ገበታ ላይ አለመገኘት ከሥራ ያለማስጠንቀቂያ ለማሰናበት ለአሰሪው ከበቂ በላይ ምክንያት ይሆነዋልና።
⚖️ይግባኝ መብት ነው!!!
©️ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
☎️ 09 10 61 69 50
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ


⚖⚖⚖⚖⚖
የፌዴራል የማናቸውም ፍርድ ቤቶች ጥብቅና ፈቃድ ማውጣት ለምትፈልጉ ሁሉ
⚖⚖⚖⚖⚖

Contact: @laws2016

            📱0910616950

👉 @laws2016
👉 t.me/etonlinelegalchat
👉 t.me/etonlinelegal

Join on👇

Telegram Group
👉 t.me/etonlinelegalchat
Telegram Channel
👉 t.me/etonlinelegal
Follow on Tiktok
👉 @tewodros2016

#Ethiopia #ህግ #lawyer #AddisAbaba #ጠበቃ #law #crime

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ


⚖️መርህ⚖️
👉የተወሰነበትን ቅጣት የፈፀመ ወይም ቅጣቱ በይርጋ ወይም በይቅርታ የቀረለት ወይም ፍርዱ ወይም የቅጣቱ አፈፃፀም የታገደለት ወይም በአመክሮ የተለቀቀ ማንኛውም ጥፋተኛ ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱትን ሕጋውያን ግዴታዎች ከፈፀመ፣ ከመቀጣቱ በፊት የነበረው ንፁህ ስም ተመልሶለት እንዲሰየምና የተወሰነበትም ፍርድ እንዲሰረዝለት መጠየቅ ይችላል።
🧐ማን መጠየቅ ይችላል?🧐
👉የጥፋተኝነት ውሳኔ የተሰጠበት ግለሰብ እራሱ ወይም
👉ወንጀለኛው ከመቀጣቱ በፊት ወደነበረው ንፁህ ስም ተመልሶ ለመሰየም ጥያቄ ለማቅረብ ችሎታ ያጣ ወይም የሞተ እንደሆነ ሕጋዊ ወኪሉ ወይም ከቅርብ ዘመዶቹ አንዱ ጥያቄውን ለማቅረብ ይችላል።
⚠️አስፈላጊ ሁኔታዎች⚠️
👉ቅጣቱ ፅኑ እስራት፣ እስከ መጨረሻው ከአገር መውጣት ወይም የንብረት መውረስ የሆነ እንደሆነ
🔗ቅጣቱ ከተፈፀመበት ወይም በይርጋ ከታገደበት ቀን አንስቶ፣ ወይም ቅጣቱ በይቅርታ በመሻሩ ምክንያት ተቀጪው ከተለቀቀበት ቀን ጀምሮ ወይም ተቀጪው ቅጣቱ ታግዶለት ወይም በአመክሮ ተፈትቶ የተፈናውን ጊዜ በሰላም ጨርሶ እንደሆነ ቅጣቱ ከታገደለት ወይም በአመክሮ ከተፈታበት ቀን አንስቶ
👉ቢያንስ የአምስት ዓመት ጊዜ ያለፈ እንደሆነ፣ በሌላ ሁኔታ ግን ያለፈው ጊዜ ቢያንስ ሁለት ዓመት የሆነ እንደሆነ፤
👉የተወሰነ ተጨማሪ ቅጣት ካለ ይኸው ቅጣት ተፈፅሞ እንደሆነ፤ እና
የተለቀቀው ተቀጪ የራሱ ችሎታና የጊዜው ሁኔታ በሚፈቅድለት መጠንና ራሱም ሊፈጽመው ይገባዋል ተብሎ በሚገመትበት ሁኔታ በፍርድ የተወሰነበትን ካሣ፣ የዳኝነትና ማናቸውንም ሌላ ኪሣራ በሚገባ አጠናቅቆ ከፍሎ እንደሆነ
👉የተለቀቀው ተቀጪ በተገለፀው ጊዜ ውስጥ በመልካም ጠባይ ተመርቶ እንደሆነና በማናቸውም በእስራት በሚያስቀጣ ወንጀል ጥፋተኛ ሳይሆን ቆይቶ እንደሆነ፤ ነው።
❗️ልዩ ሁኔታ❗️
👉መሰየም በሕጉ ከተመለከተው ጊዜ በታች ሊሰጥ አይችልም።
👉ነገር ግን ተቀጪው በሕዝባዊ፣ በወታደራዊ ወይም በማኅበራዊ አገልግሎት የሚያስመሰኝ ልዩ አበርክቶ ካለው ከጊዜው በፊት ሊሰይም ይችላል።
🆓የመሰየም ውጤቶች🆓
👉ተቀጥቶ የነበረው ሰው ከተሰየመበት ጊዜ ጀምሮ ተወስኖበት የነበረው የመብት፣ የማዕረግ፣ ወይም የችሎታ ማጣት ለወደፊቱ ቀሪ ሆኖለት ሕዝባዊ መብቱንና የማስተዳዳርና የሙያ ሥራ የመሥራት መብቱን እንደገና ለመያዝ ችሎታ ይኖረዋል፤
👉የቅጣቱ ፍርድ ከወንጀለኞች መዝገብ ላይ ይፋቅለታል፣ ወደፊትም እንዳልተፈረደበት ይቆጠራል፤
👉በጠላትነት ወይም በማናቸውም ሌላ ምክንያት ቢሆን ያለፈውን ጥፋት አንስቶ መውቀስ፣ ወቃሹን በስም ማጥፋት ወንጀል ያስቀጣል፣ በሕዝብ ጥቅም የተደረገ ነው ብሎ መከላከልም አይቻልም።
👎👎👎የጥያቄው ተቀባይነት ማጣት👎👎👎
👉ለመሠየም የቀረበውን ጥያቄ በቂ አይደለም በማለት ፍርድ ቤቱ ሣይቀበለው የቀረ እንደሆነ ሁለት ዓመት ከማለፉ በፊት እንገና ጥያቄ ለማቅረብ አይቻልም።
❌የተሰጠውን ውሳኔ መሻር ❌
👉እንዲሠየም ከተፈቀደለት በኋላ በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደገና በሞት ወይም በፅኑ እስራት እንዲቀጣ የመጨረሻ ፍርድ ተወስኖበት እንደሆነ የተፈቀደለት መሠየም ይሠረዛል፤ እንዲሁም ዳግመኛ እንዲሠየም ሊፈቀድለት አይቻልም።
⚖️ይግባኝ መብት ነው!!!
©️ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
☎️ 09 10 61 69 50
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ




1️⃣ በሕግ ፊት እውቅና ያላቸው የጋብቻ አፈጻጸም ሥርዓቶች
ሀ. በክብር መዝገብ ሹም ፊት የሚፈጸም ጋብቻ
ለ. በሃይማኖት ሥርዓት መሠረት የሚፈጸም ጋብቻ
ሐ. በባህል ሥርዓት መሠረት የሚፈጸም ጋብቻ ናቸው። #የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ ከአንቀጽ 2 እስከ 4
ሁሉም ዓይነትየጋብቻ አፈጻጸም ሥርዓቶች በሕግ ፊትእኩል እውቅና እና ውጤት አላቸው።
2️⃣ ተጋብተው 6 ወር ያልሞላቸው ባልና ሚስት በስምምነት ለመፋታት አይቀፈድላቸውም።
#የተሻሻለው የቤተስሰብ ሕግ አንቀጽ 77 ንዑስ አንቀጽ 2
3️⃣ ማንኛውም ተጋቢዎች ፍቺ በሚጠይቁበት ወቅት በአቤቱታቸውም ሆነ በቃል የፍቺያቸውን ምክንያት እንዲገልጹ አይገደዱም።
#የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 77 ንዑስ አንቀጽ 3
4️⃣ በተጋቢዎች መካከል ያለ ጋብቻ ሊፈርስ የሚችለው
ሀ. ከተጋቢዎቹ አንዱ ሲሞት ወይም በፍርድ ቤት የመጥፋት ውሳኔ ሲሰጥ ወይም
ለ. ጋብቻ ለመፈጸም መሟላት ካለባቸው ሁኔታዎች አንዱ በመጣሱ ምክንያት በሕግ መሠረት ጋብቻው እንዲፈርስ ሲወሰን ወይም
ሐ. የፍቺ ውሳኔ ሲሰጥ ብቻ ነው። ከዚህ ውጪ በመንደር የሚደረጉ የመፋታት ስምምነቶች ተቀባይነት የላቸውም።
#የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 75
5️⃣ በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል ጋብቻ ያለ መሆኑን ለማስረዳት የጋብቻ ምስክር ወረቀት በማቅረብ ማስረዳት ይቻላል። የጋብቻ ምስክር ወረቀቱ በሌለ ጊዜ ጋብቻ ለመፈጸሙ የትዳር ሁኔታ መኖሩን በማረጋገጥ ማስረዳት ይቻላል።
#የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 94 እና 95
⚖️ይግባኝ መብት ነው!!!
©️ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
☎️ 09 10 61 69 50
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ


👉 ምስክሮች
📌 ምስክር የተቆጠሩበትን ጉዳይ ባያውቁትም እንኳን በችሎት ቀርበው አለማወቅዎን ያስረዱ እንጂ የፍርድ ቤት መጥሪያ ደርስዎት አይቅሩ።
📌 የማይቀርቡበት ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት እንደጤና እክል፣ ፈቃድ ሊሰጥዎት የማይችል ሥራ እና የመሳሰሉት ከገጠመዎት በቆጠረዎት ወገን በኩል ተለዋጭ ቀጠሮ ያሳስቡ።
⏳ የውሎ ማስረጃ
📌 በፍርድ ቤት ክርክር ጉዳይ ላይ ፍርድ ቤት ስለመገኘትዎ ማስረጃ የሚያስፈልግዎት እንደሆነ የውሎ ማስረጃ ይሰጠኝ በማለት በማመልከት ማግኘት ይችላሉ።
አቤቱታው እንደአባሪ ተያይዟል።
⚖️ይግባኝ መብት ነው!!!
©️ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
☎️ 09 10 61 69 50
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ


ፍርድ ቤት መቅረብ የግዴታ ሚሆንባቸውንና ማይሆንባቸውን ጉዳዮች እነሆ፦
የወንጀል ተጠያቂነት
በፍርድ ቤት ወይም በሌላ በማናቸውም የዳኝነት ነክ ሥልጣን ያለው አካል በያዘው ጉዳይ ላይ በግል ተበዳይነት ወይም በተከሳሽነት ወይም በምስክርነት ወይም በአስተርጓሚነት ወይም በአስረጂነት እንዲቀርብ የታዘዘ ማንኛውም ሰው "በቂ ምክንያት ሳይኖረው ሳይቀርብ የቀረ ወይም ለመቅረብ እንቢተኛ እንደሆነ ከ2 ወር በማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም ከ1ሺ ብር በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል።" የኢፌዲሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 448 ንዑስ ቁጥር 1
በፍትሐ ብሔር ጉዳይ
👉 ከሳሽ
📌 ክስ የመሰረተ ወገን ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ባዘዘው ቀጠሮ ሁሉ የመቅረብ አስፈላጊው ቢሆንም ግዴታው አይደለም። ምክንያቱም፦
ከሳሽ በፍትሐ ብሔር ጉዳይ ባለመቅረቡ ክስ ያቀረበበትን ጉዳይ መብቱን ከማጣቱ እና ለሚቀርበው ተከሳሽ ወጪና ኪሳራ እንዲከፍል ከመደረጉ በስተቀር የወንጀል ተጠያቂነትን አያመጣበትም።
👉 ተከሳሽ
📌 ከሳሽ ብቻውን እስከቀረበ ድረስ ተከሳሽ ባይቀርብም ክርክሩ የሚቀጥል በመሆኑ በፍትሐ ብሔር ጉዳይ ላይ ተከሳሽ በልዩ ጊዜያት ካልሆነ በስተቀር የመቅረብ ግዴታ የለበትም።
📌 ነገር ግን ፍርድ ቤት ወይም የዳኝነት ሥልጣን ያለው አካል እንደፍርድ አፈጻጻም ያሉ ቀጠሮዎች ላይ ተከሳሽን የግድ እንዲቀርብ አዝዞት ያልቀረበ እንደሆነ የወንጀል ኃላፊነቱ ይኖርበታል።


እንደሚታወቀው ገንዘብ ወደሌላ ሰው የሚተላለፍበት መንገድ ሁለት ዓይነት ነው።
1️⃣በባንኮች በአካል በመቅረብ ፎርም በመሙላት የሚደረግ የገንዘብ ዝውውር
2️⃣በስልክ መተግበሪያ የሚደረግ የገንዘብ ዝውውር
⚠️⚠️⚠️
#አንድ ሰው ወደ ባንክ ቀርቦ ወደ ሌላ ሰው ገንዘብ በራሱ ፈቃድ ያስተላለፈ እንደሆነ ያ ያስተላለፈውን ገንዘብ በስህተት ያስተላለፍኩት ነው በማለት ክስ ለማቅረብ አይችልም።
⚖️በዚህ ረገድ የፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት በቅጽ 26 በመዝገብ ቁጥር በሆነው አስገዳጅ ውሳኔ ሰጥቶበታል።
#ነገር ግን ገንዘቡን ያስተላለፈው ሰው ሊከፍለው ከሚገባው ገንዘብ በላይ የከፈለ እንደሆነ እላፊ የከፈለው ገንዘብ እንዲመለስለት መጠየቅ ይችላል።
📱በስልክ መተግበሪያ የሚደረገ  የገንዘብ ዝውውር
#በዚህ ረገድ የሚደረግ ዝውውር በስህተት ወይም በመጭበርበር የሚደረግ ሊሆን ይችላል።
#ማንኛውም ሰው በስህተት ወይም በመጭበርበር ያስተላለፍኩት ገንዘብ ይመለስልኝ በማለት ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት ክስ በማቅረብ ገንዘቡን ማስመለስ ይችላል።
⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️
ገንዘቡን ከተጭበረበሩ ወይም በስህተት ካስተላለፉ በኋላ ወጪ እንዳይደረግ
⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️
1️⃣ገንዘቡን ባስተላለፉበት ባንክ በኩል ለ24 ሰዓታት እንዲታገድልዎት ያድርጉ።
2️⃣በአካባቢዎት በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ያመልክቱ።
3️⃣ወዲያውኑ ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት ክስ አቅርበው ገንዘቡ ወጪ እንዳይደረግ የዕግድ አቤቱታ ያቅርቡ።
⚖️ይግባኝ መብት ነው!!!
©️ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
☎️ 09 10 61 69 50
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ




💔🤵💔👰
በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 76 ላይ እንደተመለከተው ጋብቻ ሊፈርስ የሚችለው በሁለት መንገድ ነው፦
1ኛ. በስምምነት ለመፋታት በሚቀርብ የፍቺ አቤቱታ፤
2ኛ. በአንደኛው ተጋቢ በኩል በሚቀርብ የፍቺ አቤቱታ።
⚠️⚠️ከዚህ ውጪ ጋብቻ ሊፈርስ የሚችልበት አግባብ የለም።⚠️⚠️
✍✍ፍቺ በውክልና ይቻላል ወይ?✍✍
በዚህ ረገድ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ በግልጽ ያስቀመጠው የክልከላም ሆነ የመፍቀድ ድንጋጌ የለውም። ፍቺን በተመለከተ ዳኞች ወይም ተጋቢዎቹን በአካል እንዲቀርቡ ሊያደርጉ የሚችሉት ጋብቻው እንዲቀጥል ለማስማማትና ለማነጋገር በማሰብ ነው፤ ይህ ደግሞ የግዴታ አይደለም። በመሆኑም በሕግ አግባብ ለጠበቃም ሆነ ለቤተሰብ አባል የሚሰጥ ሕጋዊ ውክልና ካለ ፍቺን በውክልና ማድረግን የሚከለክል ሕግ የለም።
⚖⚖ፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት⚖⚖
👉በዚህ ረገድ የፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት በቅጽ 23 በመዝገብ ቁጥር 150408 ላይ በሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 58 እና በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2199 መሠረት ውክልና ያለው ሰው ፍቺን የሚጠይቀው ተጋቢ በአካል ባይኖርም ፍቺን መጠየቅና ውሳኔን ማሰጠት እንደሚችል አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል።
⚖️ይግባኝ መብት ነው!!!
©️ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
☎️ 09 10 61 69 50
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ


የመስከረም_ወር_2017_ዓም_የሐራጅ_ሽያጭ_ማስታወቂያ.PDF
3.2Mb
⚠️⚠️⚠️💰💰💰⚠️⚠️⚠️
የመስከረም ወር 2017 .ም
የጨረታ ማስታወቂያ
⚠️⚠️⚠️💰💰💰⚠️⚠️⚠️
ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
https://t.me/laws2016
በማናቸውም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች
ጠበቃና የሕግ አማካሪ
09 10 61 69 50


የመንግሥት መኖሪያ ቤት ለ3ኛ ወገን ማስተላለፍ
📌መርሕ
#የመንግሥት ቤትን የተከራየ ማንኛውም ሰው በሞት ሲለይ ወይም ከአካባቢው በተለያየ ምክንያት ሲለቅ ቤቱን ለአከራይ እንዲመልስ ይደረጋል።
📌ልዩ
ነገር ግን ሟች በተከራየው ቤት ውስጥ
#የተከራይ ባል ወይም ሚስት ለመሆናቸው ሕጋዊ ማስረጃ ሲቀርብ ወይም የተከራይ ልጆችና በሕጋዊ መንገድ በጉዲፈቻ ያደጉ ልጆች በቤት ውስጥ እየኖሩ መሆናቸው በወረዳው ቤቶች አስተዳደር ሲረጋገጥ፤
#በችግር ምክንያት ከተከራይ ጋር በጥገኝነት የሚኖሩ የባል ወይም የሚስት እናት ወይም አባት ለመሆናቸው በወረዳው ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ሲረጋገጥ፤
እነዚህም ወራሾች ስለመሆናቸው እና በስማቸው ወይም በትዳር አጋራቸው ስም የጋራ መኖሪያ ቤት፣ የግል መኖሪያ ቤት ወይም የቤት መስሪያ ቦታ ወይም ከመንግሥት የተከራዩት ቤት የሌላቸው መሆኑን ወይም ክ1997 ዓ.ም በኋላ በሽያጭ ወይም በሥጦታ ያላስተላለፉ መሆኑ በማስረጃ ሲረጋገጥ በቀድሞው ውል እንዲዋዋሉ ይፈቀድላቸዋል።
📌ጠቅላላ መርሆች
#ቤቱ ወደ ወራሾች ሲተላለፍ ከላይ በተቀመጠው ቅደም ተከተል መሠረት የሚሆን ይሆናል።
#ወራሾች ብዙ የሆኑ እንደሆነ በእነ ስም ውል የሚፈጽሙ ይሆናል።
⚖️ይግባኝ መብት ነው!!!
©️ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
☎️ 09 10 61 69 50
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ



20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.