የሶርያ ዋና ከተማ ደማስቆ በአማፅያን እጅ ገብታለች። የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት በሽር አል-አሳድ ዋና ከተማውን ለቀው ወደ ኢራን ሄደው ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬ አለ። ነገር ግን የተሳፈሩበት ጀት እዚያው ሶርያ ውስጥ ሁምስ አካባቢ አርፎ ሊሆን ይችላል ምናልባትም ተከስክሶ ሊሆን ይችላል የሚሉ መረጃዎችም እየተሰሙ ነው። ለሶርያ ክርስቲያኖች እንጸልይ። የአሳድ መንግሥት አምባገነን ቢሆንም ለክርስቲያኖች ደህንነት የተሻለ ጥበቃ ያደርግ ነበረ። አማፂያኑ የፖለቲካ ታጋዮችና የሽብርተኞች ድብልቅ ናቸው። ምዕራባውያንና የእስራኤል መንግሥት ለገዛ ጥቅማቸው እንጂ ለክርስቲያኖች ምንም ግድ የላቸውም። ከ2003 በፊት በኢራቅ አገር ወደ 1.5 ሚሊዮን የሚጠጉ ክርስቲያኖች ነበሩ፣ ነገር ግን ይህ አሃዝ በአሁኑ ጊዜ ከ150,000 በታች መውረዱ ይነገራል። ከ 2013 ጀምሮ ከ 90 በመቶ በላይ የሚሆኑ የኢራቅ ክርስቲያኖች አገሪቱን ለቀው ተሰደዋል።