ሰውዬው ድግስ ነበረበትና በሬውን አረደ
ከድግሱ እንዲቋደሱለት ዘመድ አዝማድ እና ጎረቤት መጋበዝ ፈልጎ ሴት ልጁን ጠርቶ "ሄደሽ ጎረቤቶቻችንን እና ወዳጆቻችንን እየዞርሽ ጥሪያቸው: ከእኛ ጋር ይብሉ ይጠጡ" አላት
ሴት ልጁም የሰፈሩ መስቀለኛ መንገድ ላይ ወጥታ "እባካችሁን ጎረቤቶቻችን ቤታችን በእሳት ተያይዞ እየነደደ ነው: እባካችሁን መጥታችሁ በማጥፋት አግዙን" ስትል ጮኸች
የተወሰኑ ሰዎች የልጅቷን ጥሪ ሰምተው እየሮጡ ወደ አባትየው ቤት ሄዱ: ሌሎች ደግሞ ሰምተው ዝም አሉ
ድግሱ ተጀመረ: ምግብ መጠጡ ቀረበ :ሁሉም መደሰት ጀመረ
ሰውዬው ቅርብ የሚላቸው ወዳጆቹ እና ጎረቤቶቹ ጋብዟቸው ባለመምጣታቸው ቅር ብሎታል
ሴት ልጁንም ጠርቶ "እዚህ የማያቸው ሰዎች በቅርቡ ወደ ሰፈራችን የመጡ ናቸው: አንዳንዶቹን ደግሞ ከነአንካቴው አላውቃቸውም:: ጎረቤቶቻችን እና የቅርብ ወዳጆቻችን የታሉ? አልጠራሻቸውም እንዴ" ሲል ጠየቃት
ልጅቱም እንዲህ አለችው
“እዚህ የምታያቸው ሰዎች ቤታችን ውስጥ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት እና እኛን ለመርዳት የመጡ ናቸው: ድግስ መኖሩን አያውቁም ነበር"
"ስለዚህ እነዚህ ናቸው ወዳጆቻችን እና ጎረቤቶቻችን: ከእነዚህ ጋር ነው ደስታችንን መካፈል እና ድግሳችንን መቋደስ ያለብን"
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
@eyetaye12