FBC (Fana Broadcasting Corporate)


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


This is FBC's official Telegram channel.
For more updates please visit www.fanabc.com

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


በ1 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባው የፕላስቲክ ፎርምዎርክ ፋብሪካ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ከ1 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባውን የፕላስቲክ ፎርምወርክ ፋብሪካ መርቀው ሥራ አስጀምረዋል። ፋብሪካው ገቢ ምርትን በመተካት በዓመት ከ15 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ የማዳን አቅም እንዳለው ተገልጿል። አቶ መላኩ አለበል በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ለአምራች ኢንዱስትሪ በልዩ ትኩረት የፖሊሲ እና የህግ ማእቀፎችን…

https://www.fanabc.com/archives/281974


ብሄራዊ ገዥ ትርክትን ለማስረጽ በትኩረት መስራት ይገባል – አቶ አሻድሊ ሃሰን

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ ተወያይተዋል፡፡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን በዚህ ወቅት እንደገለጹት÷ፓርቲው በተለይም ከመጀመሪያው ጉባዔው ጀምሮ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ ዘርፎች በርካታ ተጨባጭ ውጤቶችን ማስመዝገብ ችሏል። ክልሉ ሕዝቡን በማሳተፍ ሰላምን በዘላቂነት ለማፅናት ቀዳሚ…

https://www.fanabc.com/archives/281971


ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ የብልጽግና ፓርቲ የትኩረት አቅጣጫ ነው – ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነትን እውን በማድረግ የኢትዮጵያን ብልጽግና ማረጋገጥ የብልጽግና ፓርቲ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ገለጹ። በ2ኛው የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባዔ ባለፉት ሦስት ዓመታት ፓርቲው ለሕዝብ የገባውን ቃል በብዙ ጥረትና የተቀናጀ ሥራ እያሳካ እንደቆየ ተገምግሟል። ኢዮብ…

https://www.fanabc.com/archives/281968


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
የኦሮሚያ ክልል የኮሪደር ልማት ቅኝት


የአይ ኤም ኤፍ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ክሪስታሊና ጂዮርጂቫ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ፣ የብሄራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ እና የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጽም አሰፋ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ማኔጂንግ ዳይሬክተሯ በቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ከሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጋር በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እድገት፣ ቅድሚያ በሚሳጣቸው ፖሊሲዎችና በኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል፡፡


የጌዴኦ ብሔር ዘመን መለወጫ “ዳራሮ” በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጌዴኦ ብሔር ዘመን መለወጫ “ዳራሮ” በዓል ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ሃላፊዎች በተገኙበት በዲላ ከተማ እየተከበረ ነው፡፡ በዓሉ ”ዳራሮ ለአንድነት፣ ለልማትና ለዕድገት” በሚል መሪ ሃሳብ እየተከበረ እንደሚገኝ የክልሉ ከሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል። በአከባበር ሥነ ሥርዓቱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደን ጨምሮ የፈዴራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት…

https://www.fanabc.com/archives/281960


ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሰላምና መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተች ነው – አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሰላምና መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተች መሆኗን በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ። አምባሳደሩ የኢትዮጵያ ሰላም ለጎረቤቶቿ ሰላም ወሳኝ እንደመሆኑ መጠን የጎረቤት ሀገራትም ሰላም የራሷ ሰላም መሆኑን በተግባር አረጋግጣለች ብለዋል። ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ነጻነት ያበረከተችውን አስተዋጽኦ ያህል…

https://www.fanabc.com/archives/281957


በ740 ሚሊየን ብር የተገነባው የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ከ740 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል ተመረቀ። በቦንጋ ከተማ የተገነባው ማዕከል የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እና የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመኒቴ (ዶ/ር) በተገኙበት ተመርቆ መከፈቱን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን መረጃ አመላክቷል። ማዕከሉ በዓመት ከ150 ሺህ…

https://www.fanabc.com/archives/281954


38ኛውን የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ከ1 ሺህ በላይ ጋዜጠኞች ሽፋን ይሰጣሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤን ከአንድ ሺህ በላይ ጋዜጠኞች ሽፋን የሰጡታል ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡ 38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ከየካቲት 8 እስከ 9 2017 ዓ.ም የሕብረቱ መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ ከተማ ይካሄዳል፡፡ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የአፍሪካ ህብረት ብሄራዊ የጉባዔ አመቻች…

https://www.fanabc.com/archives/281949


አርሜኒያ ሥራዎችን በዲጂታል ሥርዓት ለማዘመን የሚደረገውን ጥረት እንደምትደግፍ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አርሜኒያ በሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተጀመሩ ሥራዎችን በዲጂታል ሥርዓት ለማዘመን ለሚደረገው ጥረት ድጋፍ እንደምታደርግም አስታወቀች። የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የአርሜንያ አምባሳደር ሳክ ሳርጊሲያን ጋር ተወያይተዋል። በውይይታቸውም ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) የኢትዮ-አርሜንያ ወዳጅነት ዘመናትን የተሻገረ መሆኑን አውስተዋል፡፡ ሁለቱ ሀገራት ሰፊ የታሪክ፣ የሃይማኖት እና…

https://www.fanabc.com/archives/281945


"በኮሪደር ልማት ተከታታይ የምሰል አቅርቦታችን አምስተኛው የኦሮሚያ ክልል ነው።

የኦሮሚያ የኮሪደር ልማት ሥራ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ከተሞችን ዳግም የማነጽ ተግባር ላይ ኢላማ ያደረገ ፕሮጀክት ነው።

ፕሮጀክቱ ከተሞችን ለሥራና ኑሮ ምቹ ብሎም ሳቢ በማድረግ የከተማ ነዋሪዎችን የኑሮ ደረጃ ያሻሽላል።

የከተሞች ቦታዎችን ለማጽዳት እና የትራፊክ ፍሰትን ለማሻሻል በመንገዶች ዳር እና ዳር ያሉ ያልተፈቀዱ ግንባታዎችን ማስወገድ የፕሮጀክቱ ቁልፍ ገጽታ ነው።

ይኽ ጥረት ለእግረኞችም ሆነ ለተሽከርካሪዎች ደኅንነት እና የተሳለጠ ጉዞ አስተዋፅዖ ያበረክታል።

እንቅፋቶችን ከማስወገድ ባለፈም ፕሮጀክቱ አረንጓዴ ስፍራዎች ማልማትን እና የመኪና ማቆሚያ ግንባታዎችን ያካተተ ነው።

ይኽም የተሻለ ዘላቂነት ላለው በሚገባ ለታቀደ የከተማ ከባቢ ልማት ከፍ ያለ አስተዋጽዖ ይኖረዋል።

ይህም የምስል አቅርቦት በክልሉ ውስጥ የገጠር ኮሪደሮች ልማትንም ያካትታል።"

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት


313 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 313 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ተመላሾቹ 208 ወንዶች፣ 92 ሴቶች እና 13 ጨቅላ ህጻናት መሆናቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝም ተገልጿል።


ፋና 80 ምዕራፍ 2 የፍጻሜ ውድድር

ነገ እሑድ 8 ሰዓት ይጠብቁን


የዕለቱ የምንዛሪ ዋጋ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ






ከ641 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ ሁለት የመጠጥ ውሃ ልማት ስምምነቶች ተፈረሙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከ641 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጭ የመጠጥ ውሃ ግንባታ እና የማማከር ኮንትራት አስተዳደር ስራዎች የውል ስምምነቶችን ፈረመ ። የመጀመሪያው ስምምነት የተፈረመው በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና የሰርጃ የግንባታና አጠቃላይ የንግድ ስራዎች ፒ ኤል ሲ እና ቢጌታ ቢዝነስ ፒኤል ሲ በጋራ በመሆን ነው። በሚኒስቴሩ…

https://www.fanabc.com/archives/281935



18 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.