Postlar filtri


ለጠ/ሚው መልእክት የህወሀት ምላሽ

ሰሞኑን በጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ አህመድ በትግሪኛ ቋንቋ የተላለፈውን መልእክት የህወሓት ከፍተኛ አመራር ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር «ማስፈራሪያ» ነው አሉ። ወይዘሮ ፈትለወርቅ ጦርነት አንፈልግም፥ ያለንን ጥያቄ ግን እናቀርባለን ነው ያሉት።

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስቴር ለትግራይ ክልል ሕዝብ በተለይም ለትግራይ ልሂቅ በማለት በትግርኛ ላሰራጩት መልእክት ምላሽ የሰጡት የህወሓት ከፍተኛ አመራር ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረ እግዚአብሔር፥ የጠቅላይ ሚኒስቴሩ መልዕክት በጥሩ ቃላት የቀረበ እንኳን ቢሆንም የትግራይን ሕዝብ ለማስፈራራት ያለመ ሲሉ ኮንነውታል። ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አሕመድ በጽሑፍ መልእክታቸው ባለፉት 100 አመታት ከማዕከላዊ መንግሥት ጋር በተለያዩ ምክንያቶች ባጋጠሙ ቅሬታዎች፥ የትግራይ መሬት የጦርነት ምድር ሆኖ ቆይቷል ያሉ ሲሆን የህወሓት ጽሕፈት ቤት ሐላፊ የሆኑት ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር ግን በምላሻቸው፥ የትግራይ ሕዝብ ባለፉት መቶ ዓመታት ወራሪዎችን መክቷል፣ ጨቋኞችን ታግሏል እንጂ የሆነ አካል ላይ ጦርነት የከፈተበት አጋጣሚ የለም ሲሉ ተናግረዋል።ከዚህ በተጨማሪ የህወሓት ከፍተኛ አመራር ወይዘሮ ፈትለወርቅ፥ ያሉንን ጥያቄዎች እናቀርባለን ይህ ደግሞ ጦርነት መሻት አይደለም ብለዋል።

ወይዘሮ ፈትለወርቅ «ልዝብ የሚመስል ግን ደግሞ በውስጡ ተጠንቀቁ የሚል ማስፈራርያ ያለው ስለሆነ ወደጦርነት ያስገባል የሚል ስጋት በሕዝብ ዘንድ ፈጥሯል። ይህ ሆን ተብሎ የተደረገ ነው። ሕዝብ እንዲሸበር እየተደረገ ነው። ይህ በትግራይ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለው በደል አካል አድርገን ነው የምንወስደው። የትግራይ ሕዝብ ይህ አይገባውም፣ ማስፈራራት አይገባውም። በመላው ትግራይ ያለው ሁኔታ ለጦርነት የሚጋብዝ ነገር የለም። መብታችን ይከበር፣ ማንነታችን ይከበር፣ በፕሪቶሪያ ውል መሠረት ሁሉ ነገር ይፈፀም ማለት ግን ጥያቄያችን ነው። ይህ ግን ወደ ጦርነት የሚያስገባ አይደለም» ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ 50 ዓመት የምስረታ በዓሉን ሊያከብር ቀናት የቀሩት ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ፥ በታሪክ የከፋ የተባለ ክፍፍል ላይ ይገኛል። የምስረታ በዓሉን ለማክበር ሁለቱ የህወሓት ቡድኖች የየራሳቸውን የተለያዩ ዝግጅቶች እያደረጉ ሲሆን፥ የየራሳቸውን የተለያዩ መፈክሮችም ይዘው ቀርበዋል። በትናንትናው ዕለት በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ክንፍ በመጪው የካቲት 11 የሚከበረው የህወሓት ምስረታ 50ኛ ዓመት ለማክበር ዝግጅት ላይ መሆኑን ሲገልጽ፤ በሌላ በኩል ደግሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን የሚመሩት ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ፥ የካቲት 11ን ለማክበር ኮሚቴዎች ተቋቁመዋል ብለዋል። በዚሁ መድረክ ስለወቅታዊ ሁኔታ የተናገሩት ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ፥ የትግራይ ፖለቲካዊ ሁኔታ በከፋ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ እና በሆነ ቅፅበት ግጭት ሊነሳ ይችላል ሲሉ ተደምጠዋል።

አቶ ጌታቸው «በመጥፎ ሁኔታ ውስጥ ነን ያለነው። በሆነች ደቂቃ በአንድ ሰው ስህተት ወደ ግጭት የምንገባበት ዕድል የሰፋ ነው። እየሄድን ያለነው ወደ ጥፋት ስለሆነ ቢያንስ ይህ በዓል ቆም የምንልበት እናድርገው ነው እያልን ያለነው» ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አሕመድ ባለፈው ሰኞ ለትግራይ ብለው አስተላልፈውት በነበረ መልእክት የትግራን ልሂቃን የውስጥ ችግራቸው እንዲፈቱ እና ቀጥሎም ከፌደራል መንግሥቱ ጋር እንዲነጋገሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ዘገባው የዶይቼ ቬለ ነው




ቴዲ አፍሮ ለጋሽ መሐሙድ አህመድ ስጦታ አበረከተ

#FastMereja I ተወዳጁ ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ለአርቲስት መሀሙድ አህመድ የስሙ የመጀመሪያ ፊደል «M» ያለበትን በወርቅ የተጌጠ ከዘራ እንዳበረከተለት ለፋስት መረጃ የደረሰው መልዕክት ያሳያል።


ትራንፕ በጋዛ ጉዳይ በግብጽ ላይ ተጽእኖ ለማሳደር የህዳሴ ግድብን ጉዳይ እየተጠቀሙበት እንደሚገኙ ተገለጸ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራንፕ የጋዛ ነዋሪዎችን ከአካባቢው በማስወጣት እንደ ግብጽ ባሉ የጎረቤት ሀገራት ለማስፈር ያቀረቡትን ሀሳብ ግብጽ እንድትቀበላቸው ለማድረግ የህዳሴ ግድብን ጉዳይ እንደ መደለያ እየተጠቀሙበት እንደሚገኝ ተገለጸ።

ባሳለፍነው ሳምንት የፕሬዝዳንተ ትራንፕ ከፍተኛ ባለስልጣናት በካይሮ ተገኝተው የጋዛ ነዋሪዎችን ከአከባቢው እንዲለቁ በማድረግ በግብጽ እና ሌሎች ሀገራት ለማስፈር ባቀረቡት እቅድ ዙሪያ መምከራቸው ተጠቁሟል።

የትራንፕ አስተዳደር ባለስልጣናት በግብጽ ላይ ተጽእኖ በማሳደር እቅዱን እንዲቀበሉት ለማድረግ የህዳሴ ግድብን ጉዳይ እንደ መደለያ ማቀረባቸውን ዘኒውአረብ ድረገጽ ምንጮቹን ዋቢ በማረግ ባቀረበው ዘገባ አመላክቷል።

የአሜሪካን ከፍተኛ ባለስልጣናት በካይሮ በነበራቸው ቆይታ ከግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ እና ከሀገሪቱ የደህንነት ቢሮ ሃላፊ ሃሰን ራሽድ ጋር “ግብጽ ከኢትዮጵያ ጋር አለመግባባት ውስጥ በገባችበት የህዳሴ ግድብ” እና "አወዛጋቢ በሆነው የጋዛ ነዋሪዎችን ማስለቀቅ” ዙሪያ መክረዋል ሲል ዘገባው አስታውቋል።

በህዳሴ ግድብ ዙሪያ በግብጽና በኢትዮጵያ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት አሜሪካ ጣልቃ የምትገባው እና የምትሳተፈው ግብጽ በጋዛ ጉዳይ የትራንፕን እቅድ የምትቀበል ከሆነ ብቻ ነው በሚል የአሜሪካ ባለስልጣናት ጉዳዩን በቅድመ ሁኔታነት ማስቀመጣቸውን ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ ዘገባው አመላክቷል።

የግብፅ ባለስልጣናት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጋዛ ነዋሪዎችን ወደ ጎረቤት ሀገራት የማስፈር ዕቅድ እንዳልተቀበሉትና "ሙሉ በሙሉ ውድቅ ማድረጋቸውን" ዘገባው አሰታውቋል።

ዘገባው አዲስ ስታንዳርድ ነው


#የቤተ መንግስቱን ግድግዳ ሰንጥቆ ገብቶ…


በ1ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ በሮም ቤተ መንግስት የተወለደች፣ ንጉሡ አባቷ ጣዖት የሚያመልክ፣ እስከ ወጣትነቷ ድረስ ክርስቶስን ልታውቅ የምትችልበት አጋጣሚ ያልነበራት፣ ይሁንና ስለክርስቶስ ፍቅር በሰማዕትነት ያረፈች እናት ናት ቅድስት ኦርኒ፡፡ "ኦርኒ" ማለት በምሥራቃውያን ልሳን "ሰላም" ማለት ነው:: ቅድስቲቱ አርበኛ የዘመነ ሐዋርያት የቤተ ክርስቲያን ፍሬ ስትሆን ተወልዳ ያደገችውም በቀድሞው የሮም ግዛት ውስጥ ነው:: ንግሥት እናቷ ምንም ክርስቲያን ብትሆንም የሚደርስባትን መከራ በመፍራት ስለ ክርስትና ልትነግራት አልደፈረችም፡፡ ዘወትር ስለልጇ በስውር ከመጸለይ ግን አልቦዘነችምና ድንቅ ምላሽ አግኝታለች፡፡


ጣዖት የሚያመልከው አባቷ ሰው እንዳያያት ለብቻዋ ቤተ መንግስት ሠርቶ 12 ሞግዚቶችን መድቦ ፍቅረ ጣኦት እንዲያድርባት፣ ጣዖት ከፊቷ አቁሞ ለዘመናት በስውር አቆያት፡፡ የሚያስተምራት ፈላስፋ ከቀጠረላት በኋላም መልኳን እንዳያየው በር ላይ ሆኖ ነበር የሚያስተምራት፡፡ የመዳን ምክንያት የሚፈልግልን እግዚአብሔር ግን ይህን የንጉሱ አካሔድ ተጠቀመበት፡፡ በሚገርም ሁኔታ መምህሯ ጠንካራ ክርስቲያን ደግ ሰው ነበርና በምን መንገድ ሃይማኖትን ሊያስተምራት እንደሚችል ሲያስብ አንድ ቀን ቅድስት ኦርኒ ራዕይ እንዳየች ነገረችው፡፡ ራዕዬዋ የቤቷ መስኮቶች ተከፍተው በስተምሥራቅ ነጭ ርግብ የወይራ ዝንጣፊ ይዛ ገብታ ከማዕዷ ላይ አስቀምጣው ትወጣለች፡፡ እርሷን ተከትሎ ቁራ በምዕራብ ገብቶ ማዕዷ ላይ እባብ ጥሎይወጣል፡፡ በ3ኛው ደግሞ ንስር ገብቶ አክሊል አስቀምጦላት ወጣ፡፡


ቅድስቲቱም እየገረማት አረጋዊ መምህሯን "ተርጉምልኝ" አለችው፡፡ እርሱም:- ርግብ-ጥበብ መንፈስ ቅዱስ፣ ዘይት-ጥምቀት፣ ቁራ-ክፉ ንጉሥ፣ እባብ-መከራ፣ ንስር-ድል ነሺነት ልዑላዊነት፣ አክሊልም-ክብረ ሰማዕታት ነው" በማለት ክርስቲያን ሆና ይህ ሁሉ እንደሚደረግ ነግሮ ተሰናበታት፡፡ እርሷም ስትጸልይ የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ ካጽናናት በኋላ አስተምሮ ያጠምቃት ዘንድ ሐዋርያው ቅዱስ ጢሞቴዎስን ልኮላታል፡፡ ሐዋርያውም የቤተ መንግስቱን ግድግዳ ሰንጥቆ ገብቶ፣ ለሰማያዊ ሙሽርነት የሚያበቃ ትምህርት አስተምሮ አጥምቋት ሔዷል፡፡ በክርስቶስ ፍቅር የተነካቸው ቅድስት ኦርኒም የአባቷን ጣዖታት ቀጥቅጣ ሰብራ እውነተኛውን አምላክ ማማለክ በመጀመሯ ከአባቷ ጋር ተጣላች፡፡ ንጉሱ አባቷ በእንስሳት ጅራት ላይ ጸጉሯን አስሮ በማስጎተት ሊገድላት እንስሶቹን ሲይዛቸው ደንብረው እጁን ገንጥለው መሬት ላይ ጥለው ገደሉት፡፡ ቅድስት ኦርኒ ግን ወደ ፈጣሪዋ ጸልያ አድርሳ አባቷን ከሞት አስነሳችው፤ እጁም ተመለሰለት፡፡


በዚህ ታላቅ ተአምር ምክንያትም በዚያች ዕለት ብቻ አባቷና 30,000 የከተማው አሕዛብ አምነው ተጠምቀዋል፡፡ ቅድስት ኦርኒ ኃይለ መንፈስ ቅዱስ ታጥቃ ክርስትናን ሰብካለች፡፡ የክርስትና ጠላት የነበረው ንጉሡ ዳኬዎስ፣ ልጁና ሌሎች 2 ነገሥታት ክርስትናን እንደትተው ለጣኦትም እንድትሰግድ በእሳት በማቃጠል፣ ለአራዊት በመስጠት፣ በግርፋትና በጦር ፈትነዋታል፡፡ እርሷ ግን ሁሉን በክርስቶስ ኃይል ድል ነስታለች፡፡ ድንቅ ተአምራት ያደረገችው ቅድስት እናት በመጨረሻም ጥር 30 በሰማዕትነት አርፋለች፡፡ በዘመነ ስብከቷ አስተምራ ካሳመነቻቸው ባሻገር 130,000 የሚያህሉ ሰዎች ለሰማዕትነት እንዲበቁም ምክንያት ሆናለች፡፡ ገዳማውያን አባቶችና እናቶቻችንን በመርዳት የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444




ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የዶ/ር አንዱአለም ዳኘን ህልፈት ተከትሎ መሰራት ባለባቸው ስራዎች ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳለፈ

የዶ/ር አንዱአለም ልጆች ለከፍተኛ ትምህርት ሲደርሱ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በነጻ እንዲማሩ፤

ባለቤቱ ከትምህርት ዝግጅት አንጻር በሲቪል ምህንድስና 2ኛ ዲግሪ ያላት እና ጥሩ አቅም ያላት በመሆኑ በዩኒቨርሲቲው የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በሲቪል ምህንድስና ትምህርት ክፍል የምትቀጠርበት ሁኔታ እንዲመቻች፤

ዶ/ር እንዱአለም በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ታሪክ የመጀመሪያውን ቀዶ ጥገና የሰራው እሱ በመሆኑና ክፍሉን እስከ ህልፈቱ ድረስ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ የነበረ በመሆኑ የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ዋርድ በስሙ ዶ/ር አንዱአለም ዳኘ ቀዶ ጥገና ዋርድ ተብሎ እንዲሰየም፤

የዶ/ር አንዱአለምን የአገልጋይነት ጥግ እንዲሁም ለሙያው የተሰጠ ተምሳሌታዊነቱን በቋሚነት ለመዘከርና ማስተማሪያ እንዲሆን በጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግቢ ሃውልት እንዲቆምለት፤

በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጁ School of Medicine ውስጥ በስሙ BDU Talent Scholarship እንዲቋቋም፤

ለ40ኛ ቀኑ መታሰቢያ የሚደርስ ስለ ዶ/ር አንዱአለም የህይዎት ታሪክ የሚዳስስ መጣጥፍ እንዲዘጋጅ የወሰነ ሲሆን ይህ ውሳኔም ቀድሞ በዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት በኋላም ለዩኒቨርሲቲው ሴኔት ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ይሁንታን አግኝቶ በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡


ጊዮን ሆቴል የሚገኘው ግሮቭ ጋርደን ለወንዝ ዳር ልማት መፈረሱን ባለቤቱ አርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ ገልጿል።
#FastMereja


ለ15 ቀን ለኢትዮጵያ እንዲጸለይ ታወጀ

#FastMereja I በመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ባሉት ቀጣናዎች፣ ክልሎች እና አጥቢያዎች በሙሉ አገራችን ኢትዮጵያን አስመልክቶ ከየካቲት 1 ጀምሮ እስከ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በጌታ ፊት ጸሎት እንዲደረግ በመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር መሪዎች ጉባኤ ተወስኗል::


#የስጋ ሞታቸውን ለምነው ያገኙት ቅዱስ አባት


በሀገራችን በኢትዮጵያ ወንጌል አንዲስፋፋ ትልቅ አስተዋጽኦ ካደረጉ አጋጣሚዎች የተስዓቱ ቅዱሳን መምጣት ነው፡፡

በአክሱማዊው ሥርወ መንግሥት በምጽዋና ቀይ ባሕር አድርገው የገቡት ዘጠኙ ቅዱሳን በቅድሚያ የጊዜውን ቋንቋ ግዕዝ ከተማሩ በኋላ በርካታ ቅዱሳን መጻሕፍትን ከተለያዩ ቋንቋዎች ወደ ግዕዝ ተርጉማል፡፡ ከእነዚህ ሀገራችንን በወንጌል ብርሃን እንደ ፀሐይ ካበሯት ቅዱሳን አንዱ ታላቁ አባት አባ ጽሕማ ናቸው፡፡ የትውልድ ሀገራቸው አንጾኪያ ሲሆን አቡነ ጽሕማ የተባሉት ጺማቸው በጣም ረጅም ስለነበረ ነው፡፡ አባ ጽሕማ ገዳም እየገደሙ፣ በዓት እያበጁ፣ ከሣቴ ብርሃን አባ ሰላማ የመሠረተውን የክርስትና ሃይማኖት በከፍተኛ ሁኔታ አስፋፍተዋል፡፡ ገዳማትን አስፋፍተው የወንጌልን ብርሃን በሀገራችን ላይ አብርተዋል፡፡


ትግራይ ዓድዋ አካባቢ የሚገኘው ደብረ ሐተታ የሚባለው ገዳማቸው ትልቅ በረከት ያለበት ስፍራ ነው፡፡ ጻድቁ በጸለዩበት ስፍራ የሚገኘው ፈዋሽ ጸበላቸው  አሁንም ድረስ በርካቶችን ከጭንቀት የሚገላግል ነው፡፡ የተፈጥሮን ሕግ በሻረ መልኩ ይህ ጸበል በጋ ሲሆን መጠኑ ይጨምራል፣ ክረምት ላይ ደግሞ ይቀንሳል፡፡ ሌላው አስገራሚ ነገር በጸበሉ አካባቢ ሣር ወይም እርጥብ ነገር ፈጽሞ አለመኖሩ ነው፡፡ በሰማዕትነት ያረፉት አቡነ ጽሕማ ጌታችን ከሞት ቢያስነሳቸውም እርሳቸው ግን እንደገና ልሙት ብለው ለምነው ነው ያረፉት፡፡  በገዳሙ ውስጥ መካነ መቃብራቸው ካለበት ትልቅ ተራራ ሥር ውስጥ ለውስጥ ወጥቶ የሚመጣው ሙቀት ያለው እስትፋስ ለአስምና ለቁርጥማት መድኃኒት ነው፡፡ በርካታ ሰዎችም ከHiv ኤድስ ድነዋል፡፡


በአንድ ወቅት አቡነ ጽሕማ ኢየሩሳሌም ደርሰው ሲመለሱ የሞተ ሰው ቢያገኙ በበድኑ ላይ የነበሩትን ተባዮች ወደሳቸው ሰውነት አስተላልፈው ተባዮቹ ሰውነታቸውን ሲመገቡ ኖረዋል፡፡ ተባዮቹም ወርቃማ ክንፍ ያላቸው ሆኑ፡፡ እነዚያ ተባዮች ዛሬም ድረስ በዓመት አንድ ጊዜ መስከረም 21 ቀን ላይ ጻድቁ ሰማዕትነት ወደተቀበሉበት ቦታ እየበረሩ ሲሄዱ በግልጽ ይታያሉ፣ ድምጻቸውም ይሰማል፡፡ ከዚያም ይሰወራሉ፡፡ አቡነ ጽሕማ ከገዳማቸው ወጥተው አርድእቶቻቸውን ለመጠየቅ "ወርዒ" በተባለው ቦታ አባ ፊልሞና ገዳም ደርሰው፣ ወንጌልን እየሰበኩ ሲመለሱ ሽፍቶች “አትስረቁ” የሚለን ይህ ደግሞ ማነው ብለው ስለገደሏቸው ለወንጌል ክብር ሰማዕትነት ተቀብለዋል፡፡

ይሁንና ጌታችን ጻድቁን አባት ከሞት አስነሣቸው፡፡ እርሳቸውም ወደገዳማቸው ተመልሰው ለቀናት ሲጸልዩና ለገዳዮቻቸው ምሕረትን ሲለምኑ ቆይተው ከጌታችን ታላቅ ቃልኪዳን ከተቀበሉ በኃላ እባክህ ወዳንተ ውሰደኝ ብለው እንደገና በሰላም ዐርፈዋል፡፡ ገዳማውያን አባቶችና እናቶቻችን የዚህን ዓለም ክብር ንቀው የሰማያዊውን መንግስት ክብር ሽተው “ሊሔዱ ጌታቸውንም ሊያዩ ይወዳሉ፡፡” አቡነ ጽሕማ በመጨረሻ ጥር 19 ቀን ካረፉ በኃላ በወቅቱ የነበረው ደገኛው ንጉሥ ዐፄ ገብረ መስቀል ተዝካራቸውን አድርጎላቸዋል፡፡ ጻድቁም በአካለ ነፍስ ተገልጠውለት እርሱም ኅዳር 30 ቀን እንደሚያርፍ ነግረውትና ባርከውት ዐርገዋል፡፡ ጥር 26ም መታሰቢያቸው ይደረጋል፡፡ ገዳማውያንንነስንደግፍ በዓቸውን ስናጸና በረከታቸውን እናገኛለን፡፡



ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444




የኢትዮጵያ አየር መንገድ መግለጫ

ዛሬ ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ሕንፃ ውስጥ ወደ በረራ ይዞ መግባት ከሚከለከሉ ቁሳቁሶች መካከል ከመንገደኞች የሚሰበሰብ የሲጋራ መለኮሻ (ላይተር) ጊዜያዊ የማስቀመጫ ስፍራ ውስጥ ጭስ በመከሰቱ ለመንገደኞች ደህንነት ሲባል ሕንፃው ለጊዜው አገልግሎት አቋርጧል።

በመሆኑም በዛሬው ዕለት ወደ ሀገር ውስጥ መዳረሻዎቻችን የምትጓዙ መንገደኞቻችን በዓለም አቀፍ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በኩል ወደ በረራችሁ እንድትሳፈሩ ከታላቅ አክብሮት ጋር እያሳሰብን ከነገ ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በተለመደው የሀገር ውስጥ ተርሚናል አገልግሎት መስጠት የምንቀጥል መሆኑን እናስታውቃለን። ለተፈጠረው መጉላላት መንገደኞቻችንን ይቅርታ እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ


ከአዲስ አበባ የሚወጡ 4 የፍጥነት መንገዶች ለመገንባት ጥናት እየተደረገ ይገኛል

ከአዲስ አበባ በተለያዩ መስመሮች የሚወጡ 4 አዳዲስ የፍጥነት መንገዶችን ለመገንባት የሚያስችል ጥናት እየተደረገ ይገኛል፡፡

ከአዲስ አበባ ደሴ ፣
ከአዲስ አበባ ጅማ ፣
ከአዲስ አበባ ደብረማርቆስ እና
ከአዲስ አበባ ነቀምት በሚዘልቁት መንገዶች ላይ ነው፡፡

አራቱን የፍጥነት መንገዶች ለመገንባት የሚያስፈልገው ወጪ የሚሸፈነው በመንግስትና የግል አጋርነት ትብብር ነው፡፡

ከፍጥነት መንገዶቹ መካከል የአዲስ ጅማ እና አዲስ ደብረ ማርቆስ ፕሮጀክቶች ለገንዘብ ሚኒስቴር የመንግስት የግል አጋርነት ቦርድ የቀረቡ ሲሆን ቀሪዎቹም በቅርቡ ይቀርባሉ ተብለው ይጠበቃል ።

ፕሮጀክቶቹም በገንዘብ ሚኒስቴር የመንግስት የግል አጋርነት ትብብር ቦርድ ከጸደቁ በኋላ ወደ ቀጣይ ስራ ይገባሉ።


ወደ ማረሚያ ቤት እንዳይገቡ  የተከለከሉ ነገሮች እና መዘዛቸው

1. በማረሚያ ፖሊስ አባላት ዘንድ፣

በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የፖሊስ አባላት የዲስፕሊን አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 3/2003 አንቀጽ 31 ቁጥር 24 በሕገ ወጥ መንገድ  አባልና ሰራተኛ ከታራሚ ጋር ወይም አባል እርስ በርስ በመመሳጠር ወደ ማረሚያ ቤት እንዳይገቡ የተከለከሉ ነገሮችን  ማስገባት፤ ለሌሎች መተባባር፣ ድርጊቱ ሲፈፀም እያዩ ለአስተዳደር አለማሳወቅ፣ ከፍተኛ ጥፋት መሆኑ በግልጽ ተመላክቷል፡፡
ወደ ማረሚያ ቤት እንዳይገቡ የተከለከሉ ነገሮች
 ሀሽሽ፣
 የሞባይል ቀፎ፣
 ሲም ካርድ፣
 ሲጋራ፣
 አልኮል መጠጥ፣
  ፈንጅ ፣
 የጦር መሳርያ፣
 ተቀጣጣይ ነገሮች፣
 ስለታም ነገሮች …ወዘተ ማስገባት ወይም አስገብቶ መገኜት ሲሆን፣ ይህ ጥፋት በፈፀመ የማረሚያ ፖሊስ አባል ላይ የሚወሰድ እርምጃ፡- በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በከፍተኛ ዲስፕሊን የሚያስጠይቅ፣ጥፋት ነው፤ ጥፋቱም ከስራ ማሰናበት እስከ ፍርድ ቤት ድረስ የሚሄድ ጥፋት ይሆናል፡፡

2. በሕግ ታራሚዎችና በቀጠሮ እስረኞች ዘንድ፣
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የሕግ ታራሚዎችና የቀጠሮ እስረኞች የተሻሻለ የሥነ ስርዓት ጥፋት ቅጣት አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 5/2009 በክፍል 02 አንቀጽ 11 ቁጥር 35 የተከለከሉ ነገሮችን (ጫት፣ ተቀጣይ ነገር፣ ስልክ፣ ሲም ካርድ ፣ሲጋራ፣ ጋንጃ፣ ቡሪ፣ አንጋዳ፣ አልኮል መጠጥና …ወዘተ) ወደ ማረሚያ ቤትና ማረፊያ ማዕከል ለማስገባት መሞከር ወይም የገባውን መጠቀም የሚያስከትለው የቅጣት አይነት
 ለ4 ወር እንዳይጎበኝ መከልከል ወይም
 ለ3 ወር ለብቻ ለይቶ ማሰር ወይም
 ከ5 ወር ከ1 ቀን አስከ 6 ወር ለሚደርስ ጊዜ ከሚያገኘው ገቢ 1/3ኛውን በመቀነስ ሥራ ማሰራት ወይም ማግኘት ከሚገባው የአመክሮ እስራት 3/4ኛውን መከልከል፡፡

ቁጥር 36 የተከለከሉ ነገሮች (አደንዛዥ እጽ፣ ጦር መሳሪያ እና ተቀጣጣይ ነገሮች ወደ ማረሚያ ቤት እና ማረፊያ ማዕከል ለማስገባት መሞከር ወይም አስገብቶ መገኘት ወይም ሌሎች እንዲያስገቡ መተባበር፣ ጉዳት ማድረስ (በወንጀል ያለው ተጠያቂነት እንደተጠበቀ ሆኖ የሚያስከትለው የቅጣት አይነት
 ለ4 ወር እንዳይጎበኝ መከልከል ወይም
 ለ3 ወር ለብቻ ለይቶ ማሰር ወይም
  ከ5 ወር ከ1 ቀን እስከ 6 ወር ለሚደርስ ጊዜ ከሚያገኘው ገቢ 1/3ኛውን በመቀነስ ሥራ ማሰራት ወይም ማግኘት ከሚገባው የአመክሮ እስራት 3/4ኛውን መከልከል፡፡

ቁጥር 37 የተከለከሉ ነገሮች (ሀሺሽ፣ ፈንጂ፣ እና ተቀጣጣይ ነገሮች…ወዘተ) ወደ ማረሚያ ቤት እና ማረፊያ ማዕከል ለማስገባት መሞከር ወይም ማስገባት ወይም የገባውን መጠቀም የወንጀል ተጠያቂነት እንደተጠበቀ ሆኖ የሚያስከትለው የቅጣት አይነት
 ለ4 ወር እንዳይጎበኝ መከልከል ወይም
 ለ3 ወር ለብቻ ለይቶ ማሰር ወይም 
 ከ5 ወር ከ1 ቀን እስከ 6 ወር ለሚደርስ ጊዜ ከሚያገኘው ገቢ
 1/3ኛውን በመቀነስ ሥራ ማሰራት ወይም ማግኘት ከሚገባው የአመክሮ እስራት 3/4ኛውን መከልከል፡፡ የሚሉት ይገኙበታል፡፡

በመሆኑም አባላት እና ሰራተኞችም ሆኑ የህግ ታራሚዎች፣የቀጠሮ እስረኞች፣ ጠያቂ ቤተሰቦች ወይም ማናቸውም በዚህ ጸያፍ ስራ ላይ የሚሰማራ ሁሉ አባላትና ሰራተኞችን ከስራ ከማፈናቀል ጀምሮ እስከ ማሰሳር ሊያደርስ የሚችል ጥፋት ሲሆን ለታራሚዎች እና ለቀጠሮ እስረኞች ደግሞ በፍርድ ቤት ከተወሰነባቸው ውሳኔ ወይም ከተጠረጠሩበት ወንጀል ተጨማሪ ጥፋት የሚሆን በመሆኑ ለተጨማሪ ቅጣት እንዲዳርጉ የሚያድርግ  ስህተት መሆኑ ታውቆ አስፈጊላው ሁሉ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል፡፡

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን
ጥር 27/2017 ዓ.ም




በማረሚያ ቤት ውስጥ ፎቶ ተነስተዋል በተባሉት ታራሚዎች ዘንድ ተንቀሳቃሽ ስልክ በፍተሻ መገኘቱን የፌደራል ማረሚያ ቤት አስታወቀ

ከሰሞኑ በማረሚያ ቤት የአየር መንገድ ደህንነትን አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል ተብለው በወንጀል ተከሰው ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው የሚከታተሉ እነ ጆን ዳንኤል ከማረሚያ ቤት ሆነው ለቀውታል በተባለ ፎቶ ዙሪያ ብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን የማረሚያ ቤቱን አስተዳደር ጠይቆ ምላሽ አግኝቷል።

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዋና ዳሬክተር አቶ ገረመው አያሌው ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ስልኩ በፍተሻ ተገኝቷል።

ይህን ባደረጉ አካላት ላይ የማጥራት ስራ ተሰርቶ ጥፋተኛው ላይ በአሰራሩ መሠረት በህግ አግባብ ተመጣጣኝ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም አቶ ገረመው ለብስራት ተናግረዋል።


የሉሲ ቅሪተ-አጽም በአውሮጳ ቤተ-መዘክር ለዕይታ ሊቀርብ ነው

በሰው ልጆች አፈጣጠር ሣይንሳዊ ምልከታ 3.18 ሚሊዮን ዓመት እድሜ እንዳለው የሚገመተው የሉሲ ወይንም ድንቅነሽ ቅሪተ-አጽም አውሮጳ ውስጥ ለዕይታ ሊቀርብ ነው ። በሰሜን ምሥራቅ የኢትዮጵያ ክፍል አፋር ውስጥ ከግማሽ ምእተ ዓመት በፊት የተገኘው ይህ ቅሪተ-አካል ከዚህ ቀደም ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለዕይታ ተወስዶ ነበር ። አሁን በአውሮጳ፤ ቼክ ዋና ከተማ ፕራኅ ብሔራዊ ቤተ-መዘክር ለመጀመሪያ ጊዜ ለዕይታ ይቀርባል ተብሏል ።


በCDC እና USAID የበጀት ድጋፍ በኮንትራት የተቀጠሩ ሠራተኞች ውል እንዲቋረጥ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

ከአሜሪካ መንግሥት በCDC ወይም USAID አማካይነት በተገኘ የበጀት ድጋፍ የሚከናወን ማንኛውም ስራም ሆነ ክፍያ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ከJanuary 24 ቀን 2025 ጀምሮ እንዲቋረጥ ማሳሰቢያ ደርሶናል ሲል ጤና ሚኒስቴር ለሁሉም ክልሎች በበተነው ደብዳቤ ተመልክተናል። በCDC እና USAID የበጀት ድጋፍ በኮንትራት የተቀጠሩ ሠራተኞች ውል እንዲቋረጥ ተወስኗል።


በእሳት አደጋ እናት አባት እና የ8 ወር ህፃን የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወታቸው አለፈ

#FastMereja I አደጋው የደረሰው ምዕራብ ሸዋ ዞን ጉደር ከተማ አስተዳደር ነው። እናትና አባት እድሜው አመት ከ8 ወር ከሆነው ህፃን ልጃቸው ጋር በቤንዚን በተፈጠረው የእሳት ቃጠሎ አደጋ ህይወታቸው ማለፉን የጉደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት አረጋግጧል።

ቅዳሜ ጥር 24 ቀን 2017 ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ በጉደር ከተማ አባገዳ ቀበሌ ውስጥ አቶ ዮናስ ደጀኔ የተባለ የባለ ሶስት እግር ባጃጅ አሽከርካሪ ቤንዚን በጄሪካን ቀንሶ ቤት ውስጥ ሲያስቀምጥ በድንገት በመኖሪያ ቤቱ የእሳት አደጋ መፈጠሩን ፖሊስ ጠቁሟል።

ቃጠሎው ለአንድ ሰዓት የቆየ ሲሆን በመኖሪያ ቤቱ ላይ ከፍተኛ ውድመት እንደደረሰም ተገልጿል ። አቶ ዮናስ የተባለው የባጃጅ አሽከርካሪ እና ባለቤቱ ወይዘሮ ብርቱካን የተባለችው እናት ከእነ ልጃቸው ህይወታቸው ወዲያዉኑ ማለፉ ተነግሯል። አቶ ዮናስ ባለቤቱን እና ልጁን ከቃጠሎ ለማትረፍ ሲሞክር ህይወቱ አልፏል፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎች እንዲሁም ፖሊሶች ግለሰቦቹን ከእሳት ለመማውጣት የሞከሩ ቢሆንም ሳይሳካለቸው መቅረቱን የሟች የወይዘሮ ብርቱካን ንጉሴ ወንድም አቶ ደበሬ ንጉሴ ለብስራት ሬዲዮ ሲናገሩ ተሰምተዋል።


በተለመዶ የጣራና ግድግዳ እየተባለ የሚጠራው የቤትና ቦታ ግብር ያለቅጣትና ወለድ የሚከፈልበት ጊዜ እየተጠናቀቀ በመሆኑ ግብር ከፋዮች ከወዲሁ እንዲከፍሉ ተጠየቀ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተለመዶ የጣራና ግድግዳ እየተባለ የሚጠራ የቤትና ቦታ ግብር የሚከፍሉ ግብር ከፋዮች ግብሩ ያለቅጣትና ወለድ የሚከፈልበት ጊዜ እየተጠናቀቀ መሆኑን በመገንዘብ ከወዲሁ ግብራቸውን እንዲከፍሉ ተጠየቀ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የገቢ አወሳሰንና አሰባሰብ ዳይሬክተር አቶ ወንድማገኝ ካሳዬ እንደገለፁት በመዲናዋ 429 ሺህ 829 ግብር ከፋዮች የቤትና ቦታ ግብር ክፍያ እንዲፈፅሙ ይጠበቃል፡፡

ይሁንና እስካሁን ባለው ሂደት 228 ሺህ 222 ግብር ከፋዮች የቤትና ቦታ ግብር መፈፀማቸውን በመግለፅ ይህም የዕቅዱ 51 በመቶ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አክለውም የቤትና ቦታ ግብራቸውን ከከፈሉ ግብር ከፋዮችም 2 ነጥብ 24 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡

የቤትና ቦታ ግብር በተለምዶ የአፈር፣ የቤትና ጣሪያ በሚሉና መሰል ስያሜዎች እስከ የካቲት 30 ድረስ የሚሰበሰብ የግብር አይነት መሆኑ ተገልጿል።

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.