ንባብ ለ ሕይወት dan repost
አንዲት አሮጊት እናት ዘወትር በረባው ባልረባው የሚጨቃጨቁ እና የሚጣሉ ሁለት ወንድ ልጆች ነበራት፡፡ አለመግባባቶቻቸውን በምክር እና በተግሳፅ ለመፍታት ብዙ ሞከረች ግን ቀላል አልሆነላትም። እናም ስለ መበደል እና መጥፎ ተግባር እንዲሁም በቅራኔ መለያየት ስለሚያመጣው ነገር በተግባራዊ ምሳሌ ልጆቿን ለማስተማር ወሰነች፡፡
አንድ ቀን ልጆቹን አንድ ጥቅል ጭራሮ እንዲያመጡላት ጠየቀቻቸው፡፡ ይህን ካደረጉ በኋላ ጥቀል ጭራሮውን እንደታሰረ በእያንዳንዳቸው እጅ ላይ በማስቀመጥ የታሰረውን ጥቅል ጭራሮ እንዲሰብሩት አዘዘች፡፡ እነሱ በሙሉ ኃይላቸው ሞከሩ ነገር ግን መስበር አልቻሉም ፡፡
በመቀጠልም ጥቅሉን ፈታችና፤ ጭራሮውን በተናጠል በተናጠል ወስዳ እንደገና በልጆቹ እጅ ላይ አደረገች፡፡ ልጆቹም በቀላሉ ይሰብሯቸዋል ጀመር፡፡ ከዚያም እንዲህ አለች
“ልጆቼ ፣ አንድ አስተሳሰብ ካላችሁ እና እርስ በእርስ ለመተባበር ከተስማማችሁ፤ ጠላቶቻችሁ በቀላሉ የማያሸንፋቹና የማትበገሩ ጠንካራ ትሆናላችሁ። ግን በመካከላችሁ መለያየትና መከፋፈል ካለ በቀላሉ ልትሰበሩ ትችላላችሁ፡፡ ስለዚህም ህብረታቹን አጠንክሩና ጠላትን አስደንግጡት"
ልጆቹ ግን የሰሙ አይመስልም።
***
የዚህች አሮጊት እናት ስም ማን ነው?
እናንብብ እንወያይ ነጻ እውንጣ
ንባብ ለህይወት