•
የአባይ ዳር ፍቅር
#ገጣሚ ብሩክ የገኒ ልጅ (ብሩኬ)
ከአባይ ፏፏቴ እግድም ዳር ቤቷ
ታጫውት የለም ወይ ያቺ ልጅ ካንጀቷ
ስቃ ስታስቀኝ ሳቋን ብውድላት
የታደማት አይኔ ቀልቤ ሸፈተላት
ፍቅሯን ስታወጋኝ በአባይ ዳር ጨዋታ
ውስጤን ስታሞቀው በከንፈር ሰላምታ
የወንዙ መግነጢስ እያስተሳሰረን
በሰመመን መንፈስ ስሎ ሲሰውረን
በመውደድ ወላፈን ሀሴት ስንፈጥም
ቃል ስንገባባ ልባችን ሲገጥም
ኧረግ አባይ ፈካ ፍቅር ስናጣጥም
ሳንተያይ ውሎ መሽቶ እዳይነጋ
ፎጣዬን ለብሼ ስበር ወራጁጋ
ቆማ አገኛታለው ጥለቷን ጣል አርጋ
ከእቅፌ ገብታ በራ ስትሸጎጥ
ራስ ይላል ናፍቆቴ ያቃጠለኝ ረመጥ
ያቺ ልጅ ላንድ ቀን ያልመጣች እንደሆን
ጭንቀት በሆዴ ላይ ብሶት ያሳርፋል
ልቤም አይችልልኝ አባይም ያኮርፋል
✍@Lanchisel
°
°
JOIN US👇👇
@getem_besamuel
@getem_besamuel
የአባይ ዳር ፍቅር
#ገጣሚ ብሩክ የገኒ ልጅ (ብሩኬ)
ከአባይ ፏፏቴ እግድም ዳር ቤቷ
ታጫውት የለም ወይ ያቺ ልጅ ካንጀቷ
ስቃ ስታስቀኝ ሳቋን ብውድላት
የታደማት አይኔ ቀልቤ ሸፈተላት
ፍቅሯን ስታወጋኝ በአባይ ዳር ጨዋታ
ውስጤን ስታሞቀው በከንፈር ሰላምታ
የወንዙ መግነጢስ እያስተሳሰረን
በሰመመን መንፈስ ስሎ ሲሰውረን
በመውደድ ወላፈን ሀሴት ስንፈጥም
ቃል ስንገባባ ልባችን ሲገጥም
ኧረግ አባይ ፈካ ፍቅር ስናጣጥም
ሳንተያይ ውሎ መሽቶ እዳይነጋ
ፎጣዬን ለብሼ ስበር ወራጁጋ
ቆማ አገኛታለው ጥለቷን ጣል አርጋ
ከእቅፌ ገብታ በራ ስትሸጎጥ
ራስ ይላል ናፍቆቴ ያቃጠለኝ ረመጥ
ያቺ ልጅ ላንድ ቀን ያልመጣች እንደሆን
ጭንቀት በሆዴ ላይ ብሶት ያሳርፋል
ልቤም አይችልልኝ አባይም ያኮርፋል
✍@Lanchisel
°
°
JOIN US👇👇
@getem_besamuel
@getem_besamuel