+++ እናታችን ጽዮን! +++
አስቀድሞ ነቢዩ ዳዊት በቃልኪዳኗ ታቦቱ ፊት ዘመረ ፤ ይህቺ ታቦት ከቅድስት ድንግል ማርያም ውጪ ማን ሊሆን ይችላል? ታቦቷ በውስጧ የኪዳኑን ጽላት ይዛለች ፤ ቅድስት ድንግል ግን የዚህን ቃልኪዳን ባለቤት ተሸክማለች። የቀደመው ጽላት ውስጥ ሕግ ተጽፏል ፤ የኋለኛይቱ ታቦት ውስጥ ያለው ጽላት ደግሞ ወንጌልን ይዟል። የመጀመሪያዋ ጽላት የእግዚአብሔር ድምፅ ተሰምቶበታል ፤ እውነተኛዋ ጽላት ደግሞ አካላዊው ቃል አድሮባታል። የቀደመችይቱ ታቦት ከውስጥ እና ከውጭ በወርቅ ያጌጠች ያሸበረቀች ናት ፤ እውነተኛዋ ታቦት ቅድስት ድንግል ማርያምም በውስጥም በውጭም በድንግልና ጌጥ ያሸበረቀች ናት። የቀደመችይቱ ታቦት በምድራዊ ወርቅ የተዋበች ያጌጠች ናት ፤ እውነተኛዋ ታቦት ቅድስት ድንግል ማርያም ደግሞ በሰማያዊ ጌጥ ያጌጠች ናት። (ቅዱስ አምብሮስ)
በቀደመው ጊዜ ፤ ታቦቷ የተቀደሰች ናትና ፤ ካህኑ በታቦቷ ፊት እንዳገለገለ እንዲሁ ዮሴፍም በድንግል ማርያም ውስጥ ያለውን ጌታውን ለማገልገል ተነሥቷል። ሙሴ እግዚአብሔር የጻፈባቸውን ጽላት እንደተቀበለ ፤ ዮሴፍም የዓለማት ፈጣሪ የእግዚአብሔር ልጅ ያደረባትን ንጹሕ እውነተኛ ጽላት ተቀብሏል። (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ )
+++
ሰላማዊቷ ጽዮን ሆይ! ለአሥራት ሀገርሽ ስለ ሰላሟ ከልጅሽ ዘንድ አማልጂ!
+++
[Reference: The Blessed Virgin in the Fathers of the First Six Centuries by Thomas Livius, London: Burns and Oates Limited,1893; PP. 77 & 383]
ስብሐት ለእግዚአብሔር
ዲያቆን ደረጀ ድንቁ
ኅዳር 20 2016 ዓ.ም