ኢጃት ለሕፃናት ድጋፍ ለማድረግ ተጨማሪ የመግባቢያ ስምምነቶች ተፈራረመ።
| ጃንደረባው ሚዲያ | የካቲት 2017 ዓ.ም|
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጠቅላይ ቤተ ክህነት የማኅበራት ማደራጃ መምሪያ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ከመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ፣ መንበረ ፓትርያርክ ቅ/ቅ ማርያም ገዳም እና ደብረ ገሊላ አማኑኤል ሰንበት ትምህርት ቤቶች ጋራ ለጋራ ሥራ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ::
በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ስር ካሉት 23 ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነው ጃን ቂርቆስ ከሰኔ 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ከመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ እና ከገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ሰንበት ትምህርት ቤቶች ጋር በመተባበር ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው 100 ሕፃናት የገንዘብ፣ የአልባሳት፣ የህክምና፣ የስልጠና እና የመሳሰሉ ድጋፎችን ሲያደርግ ቆይቷል። የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማም የሕፃናቱ አካላዊ እድገት፣ ጤና፣ የአዕምሮ መጎልበት፣ መንፈሳዊ እድገት አንዲሁም ማኅበራዊ ግንኙነት መዳበር ነው፡፡
በእነዚህ ሁለት አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ላይ ፕሮጀክቱ የሕፃናቱን ሁለንተዊ እድገትን ከማስጠበቅ አኳያ አበረታች ውጤት ስለተገኘበት በያዝነው 2017 ዓ.ም. ደግሞ ተደራሽነቱን በማስፋት ከመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ፣ መንበረ ፓትርያርክ ቅ/ቅ ማርያም ገዳም እና ደብረ ገሊላ አማኑኤል ሰንበት ትምህርት ቤቶች ጋር በመተባበር ለ 230 ሕፃናት ለሶስት አመት የሚቆይ ድጋፍ ለማድረግ በኢትዮጵያዊው ጃንደረባው ትውልድ ማህበር እና በሰንበት ትምህርት ቤቶቹ መሀከል የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል።