#🚩የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት
Ethiopian Labor Market Information System
(E-LMIS)
1- E-LMIS ላይ ለመመዝገብ ምን ያስፈልገናል?
ሲስተሙ ላይ ለመመዝገብ በቅድሚያ በስልክ አልያም በኮምፒውተር
lmis.gov.et ብሎ በመግባት ሙሉ መረጃዎችን ማስገባት፣ በመቀጠል አቅራቢያ ወዳለ ወረዳ በመሄድ የባዮሜትሪክስ አሻራ መረጃ መስጠት።
📌ምንም አይነት ክፍያም የለውም!
2- E-LMIS ላይ ምን ያህል አገልግሎቶች ይገኛሉ?
የውጪ ሃገር የሥራ ስምሪትን ጨምሮ ከሃያ ሶስት በላይ ሰርቪሶች ይገኛሉ። ሰርቪሶቹ ከሥራ ዕድል፣ ከስልጠናና ከመረጃ ጋር የተያያዘ አገልግሎት በተለያየ ይዘት ይሰጣሉ።
3- E-LMIS በስራ ዕድል ፈጠራ ምን ምን አገልግሎቶችን አካቷል?
የውጪ ሃገር ስራ ስምሪት፣ የሃገር ውስጥ ስራዎች፣ የሪሞት ስራ ዕድሎች ተካተው ይገኛሉ። ተደራጅተው መስራት ለሚፈልጉ የኦንላይን ኢንተርፕራይዝ አገልግሎት ተካቶበታል።
ለመመዝገብ :
https://kebenajobs.com/job/ministry-of-labor-and-skills-march-02-25/ 🎥 ዩቲዩብ ፡:
https://www.youtube.com/channel/UCiIzqvMmVHMH9g61rc9nX7Q