#የፌደራል
ጠቅላይ ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ 127313፣160867፣159451፣141081፣76909 እና በሌሎች የሰበር ውሳኔዎች ላይ አንድ ተከሳሽ የዐ/ህግ ምስክሮች ከተሰሙ በኃላ ወይም ተከላከል ከተባለ በኃላ በተከታታይ ቀጠሮ ካልቀረበ የቀረበበት የወንጀል ክስ በሌለበት የማይታይ ወንጀል ቢሆንም ፍ/ቤቱ ተከሳሽ የመከላከል መብቱን በራሱ እንደተወው ተቆጥሮና አልቀረበም በሚል ሰይሞ በቀጥታ ውሳኔ መስጠት እንጂ በሌለበት የሚታይ ጉዳይ አይደለም በማለት መዝገቡን መዘጋት እንደሌለበት አስገዳጅ የህግ ትርጉም ተሰጥቷል።
ይሁን እንጂ አንድ ተከሳሽ በዋስ ሆኖ ጉዳዩን በመከታተል ላይ እንዳለ የዕለት ከዕለት ሰራውን ለመስራት ከክልሉ ውጭ እንደሄደ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወይም በሌላ ወንጀል ተጠርጥሮ ታስሮ በቆየበት ሁኔታ እንዲከላከል ብይን የሰጠው ፍ/ቤት ተከሳሹ የክርክሩን አዝማሚያ ካየ በኃላ ሆን ብሎ ከፍትህ ለመሸሽ ሲል እንደቀረ ወይም እንደጠፋ በመቁጠርና ከላይ የተጠቀሱትን የሰበር ውሳኔዎችን በመጥቀስ በቀጥታ የጥፋተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ ቢሰጥ ተከሳሽ በየትኛው የህግ ድንጋጌ የመከላከል መብቱን ሊያስከብር ይችላል ? ተከሳሽ በራሱ ባልሆነ ጥፋትና ከእርሱ አቅም በላይ በሆነ ምክንያት በችሎት ባለመቅረቡ የተነሳ በህገ-መንግስቱ አንቀፅ 20(4) ስር የተመለከተውን የመከላከል መብት እንዲያጣ ማድረጉስ ተገቢ ነው ? የሰበር ውሳኔዎችስ በመሰል scenario ጊዜ ፍ/ቤቶች ተግባራዊ እንዲያደርጉ ይገደዳሉ ወይ(454/97 አንቀፅ 2(4) አንፃር )? መሰል በቂ ምክንያት ያላቸው ተከሳሾች በመሰል scenarios መብታቸው በተጣበበ ጊዜ መብታቸውን የሚያስከብሩበት የወንጀል ስነ-ስርዓት ድንጋጌስ አለ ወይ?
የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 197፣198፣199 ድንጋጌዎች ተፈፃሚነታቸው በሌለበት ተብሎ ለተሰጠ ውሳኔ እንጂ ተከሳሽ ሙሉ ክርክሩን እንዳደረገ ወይም መብቱን በራሱ እንደተወው ተቀጥሮ አልቀረበም በሚል ለተሰጠ ውሳኔ ተፈፃሚነት የላቸውም። ከላይ የተሰጡት የሰበር ውሳኔዎች ከመሰል ችግሮች አንፃር unconstitutional decisions ሊባሉ የሚችሉ አይደሉም ወይ? በዚህ ረገድ በቅፅ -7 በሰ/መ/ቁ 29325 የተሰጠው የሰበር ውሳኔ ከላይ ከተሰጡት የሰበር ውሳኔዎች አንፃር ሲታይ የተሻለ ችግር ፈችና በህገ-መንግስቱ የተመለከተውን የመከላከል መብት ሰፋ ባለ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ቢሆንም ከላይ ከተጠቀሱት የሰበር ውሳኔዎች ጋር የሚቃረና ሁሉም በ5 ዳኛ የተሰጡ ውሳኔዎች ከመሆቸው አኳያ ተግባራዊነቱን አስቸጋሪ አድርጎታል።