ግራ ቀኙ ኢትዮጵያውያን ሆነው በውጭ ሀገር ሕግ መሰረት በዛው ሀገር ጋብቻ በመካከላቸው እንደተደረገ በመግለጽ አንደኛ አመልካች ጋብቻ እንዲፈርስ እንዲሁም የጋራ ንብረት ክፍፍል እንዲደረግ ዳኝነት ሲጠይቅ ጉዳዩ የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን የሚመለከት በመሆኑ አቤቱታውን ተቀብሎ የመዳኘት ስልጣን ያለው በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 5 (1) (ሀ) እና 11 መሰረት የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ነው።