አብዛኞቹ ሴቶች ለምን እንደተፈቀሩ ምክንያት ይፈልጋሉ፡፡ ፍቅር ግን ምክንያት አያሻዉም.... ይህቺን ጽሁፍ ያንብቧት፡፡
ልጅቷ፡- ለምን ወደድከኝ? ለምን አፈቀርከኝ?
ልጁ፡- ምክንያቱን መናገር አልችልም፤ ነገር ግን የእውነት እወድሻለው፡፡
ልጅቷ፡- ምክንያትህን እንኳን መናገር ሳትችል እንዴት እወድሻለው፤ አፈቅርሻለው ለማለት ቻልክ?
ልጁ፡- እውነት ለምን እንደወደድኩሽ አላቅም ግን እንደምወድሽና እንደማፈቅርሽ ማረጋገጥ እችላለው፡፡
ልጅቷ:- ማረጋገጥ? አይሆንም፤ ለምን እንዳፈቀርከኝ ምክንያቱን ነው የምፈልገው፡፡ የጓደኛዬ ፍቅረኛ ለምን እንዳፈቀራት ነግሯታል፤ አንተ ግን ምክንያትክን አታቀውም፡፡
ልጁ፡- እሺ እሺ በቃ እነግርሻለው፡፡ ምክንያቱም ቆንጆ በመሆንሽ፤ ለጆሮ በሚለሰልሰው ድምፅሽ፤ ስለምትንከባከቢኝ፤ መልካም አሳቢ ስለሆንሽ፤ በሚያምረው ፈገግታሽ፤ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴሽ ምክንያት አፈቅርሻለው፡፡
ልጅቷ በልጁ ምላሽ በጣም ረካች፤ እጅግም ደስ አላት፡፡
እንዳለመታደል ሆኖ ከቀናቶች በኀላ ልጅቷ አደጋ ደርሶባት ኮማ ውስጥ ገባች፡፡ መንቀሳቀስ አትችል፤ ማውራት አትችል፤ መሳቅ አትችል፤ ዝም ብቻ፡፡
ልጁ ደብዳቤ ፅፎ እያለቀሰ ከጎኗ አስቀምጦት ወጣ፡፡ ደብዳቤውም እንደዚህ ይላል፡፡
"የኔ ውድ በሚለሰልሰው ድምፅሽ ምክንያት አፍቅሬሻለው፤ አሁን ግን ማውራት ትችያለሽ? አትችይም፤ ስለዚህ ላፈቅርሽ አልችልም፡፡
ስለምትንከባከቢኝ እና ስለምታስቢልኝ አፍቅሬሻለው፡፡ አሁን ግን ይህን ማድረግ አትችይም፤ ስለዚህ ላፈቅርሽ አልችል፡፡
በፈገግታሽ ምክንያት አፍቅሬሻለው፤ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴሽ ምክንያት አፍቅሬሻለው፡፡ አሁን መሳቅ ትችያለሽ? መንቀሳቀስ ትችያለሽ? አትችይም፡፡ ስለዚህ ላፈቅርሽ አልችልም፡፡
ፍቅር እውነት ልክ እንዳሁኑ ምክንያት ካስፈለገው ከአሁን በኀላ አንቺን ላፈቅር የምችልበት አንድም ምክንያት የለኝም፡፡
ፍቅር ምክንያት ይፈልጋል? አይፈልግም፡፡ ስለዚህ ዛሬም እንደትናንቱ ካለምንም ምክንያት አፈቅርሻለው፡፡ ከዘላለሙ ፍቅሬ ጋር ሁሌም ያንቺ ብቻ ነኝ፡፡"
ዳሌሽን አይቶ ያፈቀረሽ ዳሌሽ የከሳ እለት የእሱም ፍቅር አብሮ ይከሳል፡፡ ያጎጠጎጡ ጡቶችሽን አይቶ ያፈቀረሽ ቀን ጥሏቸው የወረዱ እለት የእሱም ፍቅር አብሮ ይወርዳል፡፡ አንተም እንደዛው ወንድሜ ሀብትህን አይታ ያፈቀረችህ ጋዝናህ ባዶ የሆነ ቀን የእሷም ልብ ለፍቅር የማይሆን ባዶ ዋሻ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡ ፈጣሪ እውነተኛ ፍቅርን ይስጠን፡፡