#ማሚላ )
-----
እንዳ'ንቺ ነው እንጂ....
-------
በሰማይ ሞገድ ላይ ደራሽ ሕልምን መንዳት ፣
በነገ ዋቢነት ትላንትን መደምሰስ ዛሬን በውል መክዳት ፣
በትንቢት ሐረጋት ተንጠላጥሎ ማበብ ፣
በ'ይኾናል' ግዞት ሰርክ መንጠባጠብ !
------
እንዳ'ንቺ ነው እንጂ....
------
የአበሳን ንጋት በነገ ትከሻ አሰባጥሮ ማደር ፣
በመከራ ወጀብ የተገፋ ገላን ወደምናልባት በር ዘውሮ ማንደርደር ፣
በወና አድማስ ላይ በቅንጦት መዋኘት ~ በየአጽናፋቱ በደራ ቄንጥ መቅዘፍ ፣
በተራበ አንዠት ስለነገ ማየል ኃያል ቅኔ መዝረፍ !
------
እንዳ'ንቺ ነው እንጂ ....
-------
እንባን ከውል ማሳት ፣
ባለቀሱ ቁጥር ከቆዳ ንጣፍ ላይ ክምር እድፍ ማንሳት ፣
የሕሊናን ካስማ ከስምረቱ መንቀል የነፍስን ጥያቄ በምኞት መመለስ ፣
የቅዠትን ታንቡር በ'መኾን' መከለስ !
-------
እንዳ'ንቺ ነው እንጂ...
-------
ጠኔ በሞቀ ልክ 'ጾምኩኝ' ብሎ መጽደቅ ፣
ልቡናን ሲስቱ ለምስጋና መውደቅ ፣
ለመሮጥ አቅም ሲያንስ በኩራት መራመድ ፣
እንባ ካጸደቀው ለምለም ስር ተጽፎ ሳቅን መለማመድ !
----
እንዳ'ንቺ ነው እንጂ...
-----
በከሰመ መድረክ ሕዳሴን መቀኘት ፣
ዘንድሮን ተሙቶ ከርሞ ላይ መገኘት ።
-----
እንዳ'ንቺ ነው እንጂ....
-----
እንዳ'ንቺ ነው እንጂ....
-------
በሰማይ ሞገድ ላይ ደራሽ ሕልምን መንዳት ፣
በነገ ዋቢነት ትላንትን መደምሰስ ዛሬን በውል መክዳት ፣
በትንቢት ሐረጋት ተንጠላጥሎ ማበብ ፣
በ'ይኾናል' ግዞት ሰርክ መንጠባጠብ !
------
እንዳ'ንቺ ነው እንጂ....
------
የአበሳን ንጋት በነገ ትከሻ አሰባጥሮ ማደር ፣
በመከራ ወጀብ የተገፋ ገላን ወደምናልባት በር ዘውሮ ማንደርደር ፣
በወና አድማስ ላይ በቅንጦት መዋኘት ~ በየአጽናፋቱ በደራ ቄንጥ መቅዘፍ ፣
በተራበ አንዠት ስለነገ ማየል ኃያል ቅኔ መዝረፍ !
------
እንዳ'ንቺ ነው እንጂ ....
-------
እንባን ከውል ማሳት ፣
ባለቀሱ ቁጥር ከቆዳ ንጣፍ ላይ ክምር እድፍ ማንሳት ፣
የሕሊናን ካስማ ከስምረቱ መንቀል የነፍስን ጥያቄ በምኞት መመለስ ፣
የቅዠትን ታንቡር በ'መኾን' መከለስ !
-------
እንዳ'ንቺ ነው እንጂ...
-------
ጠኔ በሞቀ ልክ 'ጾምኩኝ' ብሎ መጽደቅ ፣
ልቡናን ሲስቱ ለምስጋና መውደቅ ፣
ለመሮጥ አቅም ሲያንስ በኩራት መራመድ ፣
እንባ ካጸደቀው ለምለም ስር ተጽፎ ሳቅን መለማመድ !
----
እንዳ'ንቺ ነው እንጂ...
-----
በከሰመ መድረክ ሕዳሴን መቀኘት ፣
ዘንድሮን ተሙቶ ከርሞ ላይ መገኘት ።
-----
እንዳ'ንቺ ነው እንጂ....