ግጥም በሙከረም dan repost
እስከመጨረሻው ይነበብ❗❗❗
ምንም ቃላት የማይገልፀው ጀግንነት ፣ የሀቂቃ ወንድማማችነትና መተሰሳብ በዚህ ታሪክ ላይ ይንፀባረቃል !!!!
-----------------------
በካሊድ (ረዲየሏሁ ዓንሁ) የሚመራው እና በሰሀባዎች የተዋቀረው የጦር ሰራዊት በአውላላ ሜዳ ላይ በሮማውያን ወታደሮች ተከቧል።
በዚህ ተስፋ አስቆራጭ ቅፅበት ላይ በመካ በረሃዎች ያደገው ዒክሪማ አስደንጋጭ ውሳኔ ወስኖ ሰይፉን ከወገቡ እየታጠቀ፦ «ለሞት ቃል ኪዳን ሚገባ ካለ ይከተለኝ»
400 የነብዬ ሙሐመድﷺ
ጀግኖች 500,000 ሮማውያንን ሊፋለሙ ከዒክሪማ ጎን ተሰለፉ።
የሙስሊሞቹ የጦር መሪ ካሊድ ዒክሪማን ሊከለክለው ጠጋ አለ። የጀግንነት ግርማው ከፊቱ የሚታየው ዒክሪማ፦ «ካሊድ ዞር በልልኝ ብዬኻለሁ! አንተ ለራስህ ከነቢ ጋ የብዙ ዘመቻ እድል ገጥሞኻል።
በቀደመው ዘመን እኔ እና አባቴ ነቢን ﷺ ብዙ ተዋግተናቸዋል፤ ዛሬ ነፍሴን ሰውቼ ያጠፋሁትን ላካክስ።
እኔ ከነቢ ﷺ ለመጋፈጥ ብዙ ዘመቻዎችን ተሳትፊያለሁ። ታድያ ዛሬ ሮም ከፊቴ ብትቆም እምፈራ ይመስልሃልን? ወላሂ አይሆንም» ወንድ ልጅ ወሰነ።
400 የሞት ባለሟሎች ከሜዳው የተሰለፉትን እልፍ አእላፍ ሮማውያንን ሊገጥሙ ተንደረደሩ። ኩነቱን ከዙፋኑ ላይ ሁኖ የሚከታተለው የሮሙ ጦር መሪ ተምዘግዛጊውን ዒክሪማ በቀስት እንዲመታ ትዕዛዝ አስተላለፈ።
በጦር አዛዡ ትዕዛዝ በርካታ የቀስት ፍላፃዎች ወደ ዒክሪማ ይዘንቡ ጀመር። ከላይ ሚወነጨፉ ፍላፃዎች የዒክሪማን ፈረስ አደካክመው ጣሉት።
ዒክሪማ ከወደቀው ፈረሱ ላይ ዘሎ ወረደ። በመጣበት ሞራላዊ ፍጥነት ለቅፅበት ሳያንገራግር ከፊቱ የተሰለፉትን ሮማውያን ሰልፍ እያተራመሰ ከመሀከላቸው ተከሰተ።
በአላህ መንገድ የመዘዛትን ሰይፍ እየለካ የከሀዲያኑን አንገት እና ወገብ ይሰፍር ጀመር። ይህን ጀግንነት ከዳር ሁነው የሚመለከቱት ባለሟሎቹ የሞራል ስሜት ቢገፋቸው የአላህን ልቅና ከጦር ሜዳው እያስተጋቡ ትርምሱን ተቀላቀሉ።
የአላህ ሰንደቅ ከፍ ብላ እንድትውለበለብ ዒክሪማ ገደለ፣ ተጋደለ...በመጨረሻም ለኩፋሮች ያቀመሳትን የሞት ፅዋ ቀምሶ ሸሂድ ሊሆን ከሜዳው ላይ ወደቀ።
የወደቀው በወደቀበት ሲየቃስት፣ የሞተው ሬሳው በአቧራ ሲላወስ በፈረሶች ጩኸት የሚተራመሰው ጦር ሜዳ ገበያውን አድምቆታል።
በዚህ መሀል የነቢ ﷺ መድረሳ ምሩቃኖች የጦር ሜዳውን በተክቢራት እያናወጡ የሮማውያኑን ሰራዊቶች ቁልቁል ያሳድዷቸው ጀመር።
የነቢ ﷺ ሙሪዶች ድል ቀናቸው። ጦርነቱን አሸንፈው ሮምን በሀፍረት ካሳደዱ በኋላ የሸሂዶችን አፀደ ስጋ ለመሰብሰብ ከሜዳው ተበተኑ።
ካሊድ በሜዳው ከተዘረሩት የሙታን ገላዎች የዒክሪማን እያፈላለገ ሲዘዋወር ድንገት ከሁለት የጀነት ሙሽሮች መሀል ተጋድሞ ሲጣጣር ደረሰ።
ሀሪስ፣ ዒክሪማ እና ዐያሽ ከገላቸው ደም እየፈሰሰ የጀነት ማረፍያዎቻቸውን እየተጠባበቁ ነበር።
የበረሀው ሀሩር ላንቃውን ያደረቀው ሀሪስ ከአሸዋ ላይ ተኝቶ እያጣጣረ ውሀ እንዲሰጠው ጠየቀ። ውሀውም ተቀድቶ ቀረበለት።
ሀሪስ ውሀውን ሊጠጣ ከከንፈሩ ሲያስጠጋ ከጎኑ የተጋደመውን ዒክሪማን ተመለከተ፦«ውሀውን ለዒክሪማ ስጡት መጀመርያ» የወንድምነት ፋንታ
ውሀው ወደ ዒክሪማ ተወሰደ። ዒክሪማ ውሀውን ሊጠጣ ቀና ሲል ከጎኑ የተጋደመውን ዐያሽን ተመለከተው።
«ቀድማችሁ ዐያሽ ጋ ውሰዱ» ብሎ ውሀውን ሳይቀምስ መለሰው። ውሀው በመጨረሻም ከዐያሽ ዘንድ ደርሶ ሲሰጠው፦ «ውሀውን ቀድሞ ለጠየቃችሁ ወንድሜ ስጡት» ብሎ መለሰላቸው።
ውሀዋ ተመልሳ ከሀሪስ ዘንድ ተወሰደች፤ ሀሪስ ሙቷል። ዳግም ከዒክሪማ ዘንድ መጣችለት ግና ሩሑ የለችም። ከዐያሽ ዘንድም ውሀዋ ስትወሰድ ዐያሽም ጓደኞቹን ተከትሎ ገላው ቀዝቅዟል።
ረዲየላሁ ዐንሁም አጅመዒን
_
ምንጭ፦
صور من حياة الصحاب
--------------------
👑 @mengeshaye 👑