ጣፋጭ ውጥረት| "Sweet Spot of Stress"
በፈረንጆቹ 'Our Individual Zone of Optimal Functioning (IZOF)' ይባላል፤ በግርድፉ ሲተረጎም "ተግተን የምንተገብርበት የግል የውጥረት ልኬታችን" እንደ ማለት ነው!
በቀን ተቀን የስራ እና የህይወት ውጣውረዳችን ውስጥ አነሰም በዛ ውጥረት ያጋጥመናል...ዋናው ቁምነገር ግን በተፈጠረው እና በእኛ ግብረመልስ መካከል ያለውን ሚዛን ማስጠበቅ ላይ ነው።
ጭንቀትን ልክ እንደ ፊኛ እናስበው፡-
- በጢቂቱ የተወጠረ ፊኛ አየር ላይ እንደማይንሳፈፈው ሁሉ ውጥረት የሌለበት ኑሮ አሰልቺ የህይወት ተሳትፎ ነው።
- ያለማቋረጥ ፊኛን በአየር ብንሞላው ደግሞ እንደሚፈነዳው፡ የማያቋርጥ ጭንቀት ወደ ተስፋ መቁረጥ ያመራናል።
- በልኩ የተወጠረ ፊኛ በአየሩ ላይ እንደሚንሳፈፈው ሁሉ ጤናማ የሆነ ውጥረት እንድንነሳሳ፣ እንድናከናውን፣ እንድንተጋ እና እንድናድግ ይረዳናል።
አሁን ጥያቄው "የእኛ ጤናማ የውጥረት ልክ እስከ ምንድን ነው? እናውቀውስ ይሆን ወይ?" ነው።
ጤናማ የሆነ ውጥረት ወደፊት ለመግፋት፣ ወደላይ ለማደግ ብሎም መልካም ውጤትን ለመውለድ አስፈላጊ ነው፤ ይህም ማለት እድገት የሚፈጠርበት፣ ፈጠራ የሚበለፅግበት፣ እና የመቋቋም አቅም የሚገነባበት ልኬት ነው እንደ ማለት ነው።
ለማደግ የግድ መለጠጥ አለብን ነገር ግን እስክንበጠስ መሆን የለበትም!
ስለዚህ ጣፋጭ የሆነው ውጥረት፦ የማደጋችን መንስኤ፣ የውጤታማነታችን ጥንስስ ነው...የእኛን ምርጥ ውጤታማነት ማምጣት ከፈለግን በምቾቱ ቀጠና (Comfort Zone) ሳይሆን በውጥረቱ መንገድ መጓዝ ግድ ነው!
ጥበብ እና ማስተዋል ለሰው ልጆች ሁሉ!
ሣሙኤል ተክለየሱስ (ዓለም አቀፍ የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)
@melkam_enaseb