ከ2017 አእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
✞ እንደ ኤልሳቤጥ ላመስግንሽ ✞
እንደ ኤልሳቤጥ ላመስግንሽ
ፊትሽ ወድቄ ልሳለምሽ
የጌታዬ እናት የእኛ እመቤት
አዛኝ ነሽ ከልብ ፍጹም የዋህት
ርኀራኄሽ ያስደንቀኛል
ስለ ኃጢአቴ ምልጃሽ ይቀድማል
የሰላምታሽ ድምፅ ደስ ያሰኘኛል
ከትካዜዬም ያሳርፈኛል
/አዝ = = = = =
ድምፅሽ ሲሰማኝ ልቤ ይረካል
ሃዘኔ ቀርቶ ፊቴ ይፈካል
በእናትነት አንቺን ለሰጠን
ቸሩ አምላካችን ይክበር ይመስገን
/አዝ = = = = =
የሁሉ እመቤት የሁሉ አጽናኝ
የአበዉ መድኀኒት ከአምላክ አገናኝ
ዛሬም በልቤ ደስታን ጨምረሽ
እንደ ኤልሳቤጥ ሰላም ልበልሽ
/አዝ = = = = =
ከሴቶች መካከል መርጦ ቀድሶሻል
ትዉልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉሻል
በልዩ ወዳሴ ያመሰግኑሻል
ድንግል ንግሥታችን በቀኙ ቆመሻል
/አዝ = = = = =
የሰላሞታሽ ድምፅ ልቤ ሲሰማ
ነፍሴ ደስ አላት ቀለለ ሸክሟ
ድንግል ለክብርሽ ስንበረከክ
እጅሽ ይዘርጋ ለመባረክ
👉 ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═══✞╗
✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
╚✞═══●◉❖◉●═══✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ