ቦርንማውዝ ከ ሊቨርፑል !
በሁለቱ ክለቦች ካለፉት 11 የፕሪሚየር ሊግ ግንኙነቶች ቦርንማውዝ 10ሩን ተሸንፏል።
ሊቨርፑል ከበርንማውዝ ጋር ካደረጋቸው ካለፉት 15 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ 10ሩ ላይ ቢያንስ 3 ጎል ሲያስቆጥር በአጠቃላይ ደግሞ 46 ጎሎችን አስቆጥሯል።
በርንማውዝ በ11 የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን ላይ ያለ ሽንፈት በመጓዝ የክለቡ ሪከርድ ላይ ይገኛል (7 አሸንፎ ፣ 4 አቻ በመውጣት)።
ዘንድሮ በርንማውዝ አሁን በደረጃ ሠንጠረዡ ከነሱ በላይ ካሉ ቡድኖች ጋር ባደረጓቸው 9 ጨዋታዎች 15 ነጥቦችን አግኝተዋል። በዚህ ሂደት አርሰናልን ፣ ኖቲንግሃም ፎረስትን፣ ማንቸስተር ሲቲን እና ኒውካስልን አሸንፈዋል (አሸነፉ 4፣ አቻ 3 ፣ 2 ሽንፈት)
ጀስቲን ክላይቨርት ባለፉት 12 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች 12 ጎል+አሲስት አስመዝግቧል ፣ ይህም ከዛ ባለፉት 42 ጨዋታዎች ካደረገው አንድ ብልጫ አለው።
ዳንጎ ኦውታራ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ለበርንማውዝ 10 የፕሪሚየር ሊግ የጎል ተሳትፎዎች አሉት፣ 6 ጎል እና 4 አሲስቶች።
ይቀጥላል...
SHARE"
@MULESPORT