Postlar filtri


ከነገ ጀምሮ በሚኖረው የመማርማስተማር ሂደት ተማሪ ሞባይል ይዞ መገኛት የተከለከለ ይሆናል። በቀጣይ ሳምንት በሚኖረው የመማር ማስተማር ሂደት በሁሉም ትምህርት አይነት ክፍለ ጊዜ በጠረጴዛ ላይ የመማርያ መፃሃፍ ገልፆ መማር ግዴታ ከመሆኑ ጋር መፃሃፍ ይዞ የማይገኝ ተማሪ ከክፍል በማስወጣት አቴንዳንሱን የማይያዝለት ስለ ሚሆን ከወዲሁ በወጣላቹህ መፃሃፍ መውሰጃ ሰአት ና ቀናት እንድትወስዱ ።


በሁሉም ክፍል ደረጃ የመማርያ መፃሃፍት ያልወሰዳቹህ ተማሪዎች የመፃሃፍ መውሰጃ ሰአት በሚከተለው መልኩ እንደሚሆን እናሳውቃለን። በያ እለቱ ጡዋት ከ2:00 ጀምሮ ከሳአት ከ10:00 ጀምሮ መክሰኞ ቀን ለ9ኛ ክፍል ተማሪዎች እሮብ ቀን ለ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ሀሙስ ቀን ለ11ኛ ክፍል ተማሪዎች አርብ ቀን ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚሰጣቹህ ይሆናል። በሁሉም ትምህርት አይነት መፃሃፍት የሚሰጣቹህ እንደሚሆን እናሳውቃለን።


ቀን 24/06/17 በ2017 የት/ት ዘመን በት/ቤታችን ውስጥ በመማር ላይ ያላቹህ ተማሪዎች በሙሉ። በቅዳሜ ቀን 22/06/17 የወላጆች ስብሰባ ላይ በተለያያ ምክንያት ወላጆቻቹህ ያልመጡ ተማሪዎች በነገው እለት መክሰኞ ጡዋት ከ2:00 እስከ 2:30 ት/ቤት እንዲገኙ አድርጉ።ይህንን ድጋሚ የተሰጠውን ከቅጣት ነፃ የወላጆች ጥሪ ሀላፊነት ያልተወጣ ተማሪ ከእሮብ ጀምሮ የወላጆች ጥሪ በቅጣት እንደሚሆን እያሳወቅን ቀናት በጨመረ ቁጥር ቅጣቱም አብሮ እየጨመራ እንደ ሚሄድ ከወዲሁ እናሳውቃለን።


ማስተወቂያ ቀን 10/06/2017
በ2017 የት/ት ዘመን ከ9 - 12 ኛ ክፍል በት/ቤታችን የ2ኛ ሴሚስተር ተማሪ ለሆናቹህ በሙሉ።

በቀን 22/06/2017 (ቅዳሜ) እላት በት/ቤታችን የ2ኛ ሴሚስቴር የመጀመርያ ዙር የተማሪ ወላጆች ስብሰባ ስለ አለ የተማሪ ወላጆች በእለቱ ከ2:00 ቀደም ብለው በት/ቤቱ ጊቢ ውስጥ እንዲገኙ በማድረግ ሀላፊነታቹሁን እንድትወጡ ጥብቅ መልእክት እያስተላላፍን ሀላፊነታቸውን ባልተወጡ የተማሪ ወላጆች የተለመደውን ተጠያቂነት እንደሚኖር ከወዲሁ እናሳውቃለን።

ማሳሳብያ: በክፍል ውስጥ መልእክቱ የተነገራቹህ ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ላልተገኙ ጓደኛ ተማሪዎች (የተማሪ ወላጆች) እና ለራሳቹህ ተጠሪ ወላጆች መልእክቱን በሚገባ ባላማድረስ ከሚመጣ አላስፈላጊ የወላጆች ቅጣት ውሳኔዎች ወላጆቻቹሁን እንድትታደጉ መልእክታችን ነው።


ማስተወቂያ ቀን 19/06/2017
በተለያያ ምክንያት የ1ኛ ሴሚስተር ፈይናል ፈተና ያመለጣቹህ እና ማማልከቻ ከማስረጃ ጋር ያስገባቹ ተማሪዎች በቀን 20/06/2017 ማላትም በነገው እለት ሀሙስ ቀን ከጡዋቱ 2:00 ጀምሮ በዲጋሚ ለመጨረሻ ጊዜ ፈይናል ፈተና እንድትወስዱ ከወዲሁ እናሳውቃለን።

ማሳሳብያ: ት/ቤቱ በዲጋሚ ያዘጋጀውን ፈይናል ፈተና ተፈትኖ ለማያጠናቅቅ ተማሪ ይህ እድል የመጨረሻ ስለ መሆኑ ከወዲሁ እናሳውቃለን።


ማስታወቂያ ቀን 07/6/17 ለአጠቃላይ ተማሪዎች ከሰኞ ቀን 03/6/17 ጀምሮ 2ተኛ ሴሚስቴር ትምህርት የሚጀመርበት Day one class one መሆኑን አሰውቀን ለመማር እንድትመጡ ማሳወቃችን ይተወቃል። በመሆኑም በቀጣይ ሳምንት የሚኖረው የመማር ማስተማር ሂደት ከ9 እስከ 11ኛ ክፍል በክፍል ሀላፊ መምህራን አማካይነት 12ኛ ክፍል በያ ሰብጀክት መምህራን አማኳይነት የተማሪ አቴንዳንስ ማያዝ እንደምጀምር አውቃቹህ ከወዲሁ የሚጠበቅባቹሁን አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ በመማር ማስተማሩ ሂደት ላይ ንቁ ተሳታፊ በመሆን ለውጤታቹህ ማማር መሰረት እንድትይዙ ደግመን እናሳውቃለን።


ማስታወቂያ ቀን 03/6/17 ለአጠቃላይ ተማሪዎች ከዘሬ ሰኞ ቀን 03/6/17 ጀምሮ 2ተኛ ሴሚስቴር ትምህርት የሚጀመርበት Day one class one መሆኑን አውቃቹህ ለመማር እንድትመጡ እናሳውቃለን።


ለ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ

መምህራን ዘሬ ቀን 20/5/17 መክሰኞ እለት ከሰአት 9:00 ጀምሮ በተፈተናቹት ፈይናል ፈተና የመጣቹሁትን ውጤት እና ከመቶ ያላቹሁን ውጤት ስለ ሚያሳዩዋቹህ ከተጠቀሰው ሰአት በፊት እንድትገኙ።




1ኛ አንድ ተማሪ ለምንም አይነት ምክንያት ትምህርት ቤቱ ባላዋቀው መንገድ ሞባይል ይዞ በፈተና ክፍል ውስጥ ወይም በጊቢ ውስጥ ከታየ በመጀመርያ ሞባይሉ ይቀማል። በመቀጠል ከዚህ በፊት ሞባይሉን ተቀምቶ የተማሪ ወላጆች በወሰኑት 1000 ብር ቅጣት ከፍሎ የተመላሰለት ከሆናና ሞባይል ይዞ የመጠው ለሁለተኛ ግዜ ከሆነ በምዝገባ ወቅት ተማሪና ወላጅን በአስፈረምነው መመርያ መሰረት ወይም በተለያያ ጊዜ የተማሪ ናወላጅ ስብሰባ ላይ አስቀድመን በአስረደነው መሰረት ሞባይሉ የሚወረስ ይሆናል። ነገር ግን ከዚህ በፊት ሞባይል ያልተያዘበቸው ተማሪዎች ከሆነ ሞባይል ይዘው የተገኙት ሁሉም ፈተና ከተጠናቀቃ ቦሃላ በሉት ቀናት በምዝገባ ወቅት ተማሪና ወላጅን በአስፈረምነው መመርያ መሰረት በ1000 ብር ቅጣት ሞባይላቸው የሚመላስላቸው ይሆናል። ከሞባይል ፈይናል ፈተናውን መልስ ስሰሩ እጅ ከፍንጀ የተያዙ ተማሪዎች ከላይ የተጠቀሱት የሞባይል ቅጣት አይነቶች እንደያደረጃቸው የሚያገኛቸው ስሆን በተጨማሪም የፈይናል ፈተናው ትምህርት አይነት ምንም አይነት ውጤት ቢያመጣ በፈተና ና ሚዘና ኮሚቴ ተመርምሮ ጥፈተኛ ሆኖ ከተገኛ ዜሮ ልሰጠው ይችላል። ስለዚህ ከትንሽ እሰከ ትልቅ ሞባይል ይዞ መገኛት የተከለከላ ነው። ሌላው ፈተና ለተማሪዎች ከተሰጣ 30ደቂቃ ቦሃላ የሚመጣ ተማሪ የማይፈተን መሆኑን ና ፈተና ለተማሪዎች ከተሰጠ ከ 30 ደቂቃ በፊት ከፈተና ክፍል ለመውጣት መፈለግ ለተማሪዎች ያልተፈቀዳ በመሆኑ ተረጋግታቹህ ፈተና እንድትሰሩ እያልን ከወዲሁ እናሳውቃለን። ለመልካም ውጤት መልካም የፈተና ቀናት ይሁንላቹህ።


ጥብቅ ማስታወቂያ ለሁሉም ክፍል ተፈተኝ ተማሪዎች በሙሉ። በነገው እለት በሚጀረው የ2017 አንደኛ ሴሚስቴር ፈተና ክፍል ውስጥ ተማሪዎች ልጠቀሙወቸው የማይገባ ስነምግባር ስለ ማስተወስ።




                ቀን:13/05/2017
✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍

ለ2017 ተማሪዎች በሙሉ

የአንደኛ ወሰነ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና የተማሪዎች ድልድል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇















20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.