ትንሽ ስለ ሰሌ:
"ትንሽ ስለ ሰሌ" ልበለው እንጂ ስለ እኔም ነው፤ ምክንያቱም ሰሌ በእኔ የሕይወት መንገድ ውስጥ ብዙ ነው፡ አሻራው አይለቅም፡፡
አንዳንድ ሰዎች በሕይወታችን ልክ እንደ milestone ከኋላ የመጣነውን ርቀት ከፊት ደግሞ ምን ያህል ርቀት እንደሚቀረን ጠቋሚዎች ናቸው፡ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ ሰለሞን ነው፡ ስለትጋቱ፣ ለእግዚአብሔር ስለነበረው ቅናትና፣ ቤተሰቡን እንደ አይኑ ብሌን ስለማየቱ ለሁሉም የተገለጠ ስለሆነ ምንም ማለት አያስፈልገኝም፡ ነገር ግን በእኔ ሕይወት ዘወትር እያሰብኳቸው እንድኖር የምገደዳቸውን ነገሮች ጥሎብኝ አልፎአል፡ በመሰረቱ ሰለሞን በሕይወታቸው አሻራውን የጣለባቸው ሌሎች ብዙዎች እንደሚኖሩ ጥርጣሬ የለኝም።
ከሰሌ ጋር የተዋወቅነው የሃያሦስት አመት ልጅ ሆኜ በምሥራቅ መሰረተ ክርስቶስ የ ሀ መዘምራን ቡድን ውስጥ ሳለሁ ነበር፡ ወዲያው ነበር ንግግሩ ረገጥ ያለና ቃላቶቹ ጠጠር ያሉ መሆናቸውን ያስተዋልኩት፡ ሰሌ በጣም ትጉህና ከልቡ የተሰጠ ሰው ከመሆኑ የተነሳ ወዲያው ነበር የመዘምራን ቡድናችን መሪ የሆነው፡ መሪ ብቻ ሳይሆን እንደ አባትም ነበር፡ ካረፈድን በር ላይ ቆሞ ገና ከሩቅ ሲያየን በየስማችን እየጠራን “አትሮጡም እንዴ" እያለ ነበር የሚያስገባን፡፡
በደንብ ስንግባባና ጠለቅ ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን መነጋገር የጀመርን ጊዜ ነበር ነገረ-መለኮት ትምህርት ቤት እንድገባ ያበረታታኝና ETCን የተቀላቀልሁት፡ ETC ገብቼ እንኳን ከአስተማሪዎቼ በላይ ይከታተለኝ የነበረው እርሱ ነበር፡፡
አንድ ቀን ወደ መዝሙር ጥናት ሲመጣ እስካሁን የማስታውሳት ውብ ቡናማ ሳምሶናይት ይዞ መጣ፡ እኔም ከቀረቤታዬ የተነሳ እንደማያደርገው እያወቅሁኝ “ሰሌ እስቲ ይህችን ሳምሶናይት ስጠኝ” ብዬ ጠየቅሁት፡ ከሳምሶናይቷ በላይ የማልረሳውን መልስ ነበር የመለሰልኝ፣ እንዲህ ሲል፤
“እኔ ካሁን ካሁን ብትቀደድብኝ ምን እሆናለሁ ብዬ እየተጨነቅሁ ነው አንተ ስጠኝ ትለኛለህ?”
ለዓንድ ነገር መጨነቅ ያለብኝ ሳይቀደድ በፊት መሆኑን አስተምሮኝ አልፎአል።
አጥቢያ ቤተክርስቲያኔ ለሙሉ ጊዜ አገልጋይነት ስትጠራኝ በዋነኛነት እንዲያናግረኝ የተመደበው ሰሌ ነበር - በዚያ ወቅት የአጥቢያችን ሽማግሌ ነበር፡ በተቀጠርኩበት ቀን ቢሮ ስገባ ቤተክርስቲያን ለሙሉ ጊዜ አገልግሎት እንዳገለግል እንደምትፈልግ ሲነግረኝ አይኑ በእንባ ተሞልቶ ነበር፡ ምክንያቱ ይገባኛል፡ ብዙ አብረን ስላሳለፍንና ከነበረን ቅርርቦሽ የተነሳ ልብ ለልብ ስለምንተዋወቅ ቤተክርስቲያን በዚያ እድሜዬ ለዚህ ትልቅ አገልግሎት ስትጠራኝ ከነበረው ደስታ የመነጨ ነበር።
በግምት የሃያ አምስት አመት ወጣት በሆንኩበት ጊዜ በአጥቢያችን የተዘጋጀውን የፋሲካ አዳር አድረን ጠዋት ወደቤታችን ስንበተን እኔና እርሱ ከገርጂ መገናኛ ድረስ በእግራችን እየተጫወትን እናዘግም ነበር፡ ሐሳቡ እንዴት እንደመጣልኝ ባላውቀውም “ሰሌ እስቲ ምከረኝ” ብዬ ከልቤ ጠየቅሁት፡ ሰሌ ሲጫወትም ይጫወታል ሲመክርም ከልቡ ነበር የሚመክረው፡ ከገርጂ እስከ መገናኛ ድረስ ነበር የሚንቆረቆር ምኩሩን ያጠጣኝ፡ በተለይ እርሱ ካለፈበት የሕይወት መንገድ በመነሳት የለገሰኝ ምክሮች ወርቆች ነበሩ፡ ከመከረኝ ምክር ሁሉ የማልረሳት ግን “ይልዬ የትኛውም ነገር ቸኩለህ ከሚበላሽብህ ዘግይተህ ቢቀርብህ ይሻላል” የምትለዋ ናት።
የመዘምራን ቡድናችንን እንደ ተቀላቀለ ነበር ለሚጠይቀው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄ ሁሉ መልስ እሰጠው የነበረው፡ ምንም ያንሳ ምን ብቻ እኔ ጋር መልስ አይጠፋም ነበር፡ ብልህ ስለነበር አንድ ቀን እሁድ ማለዳ ሻይ ጠጥተን ለአምልኮ እየገባን ልክ ከግቢው በር ስንደርስ እንዲህ ብሎ ጠየቀኝ፤
“ይልዬ አዳምና ሔዋን ግን መንግስተ ሰማይ ይገባሉ እንዴ?”
የዛን ቀን ጌታ ረድቶኝ ነው መሰል አድርጌ በማላውቀው መልኩ “ኧረ እኔ አላውቅም” አልኩት፡ እርሱም መለስ አድርጎ በሚራራ ዓይን በእንግሊዝኛ አፍ፤
“Now you became matured” አለኝ፡
ሰው አለማወቁን ሲያውቅ አንድ የመብሰል ምልክት ነው እንደማለቱ ነበር።
ሰሌ የትኛውንም ነገር “እንካ ሥራ” ተብሎ ቢሰጠው ከእርሱ በኋላ ሌላ ሰው የተሻለ አድርጎ እንዳይሰራው አድርጎ ነበር የሚሰራው፡ በነበርንበት አጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ለገንዘቡ ለጉልበቱና ለጊዜው ሳይሳሳ የሚለፋ ወንድም ነበር፡፡
በአጥቢያአችን፣ ምናልባት ካልተሳሳትኩ ደግሞ በፕሮቴስታንቱ ማህበረሰብ ዘንድ ሰርግ ማለት ጋብቻ ማለት እንጂ ድግስ ማለት እንዳልሆነ ያሳየን ሰለሞን ይመስለኛል፡ ሰርጉ እሁድ ሲሆን የተደረገው ከበዛ የወሰደው አሥራ ስምንት ደቂቃ ብቻ ያህል ነበር፡ ይኼ የሚያሳየው ሰሌ ምን ያህል ትራፊ ለሆነው ነገር ሳይሆን እንቡጥ ወይም አንኳር ለሆነው ነገር ግድ የሚለው ሰው መሆኑን ነው።
ሰሌ የትኛውም አውድ ውስጥ ገብቶ ለመቀላቀል የማይቸግረው ሰው ነበር፡ አጥቢያችን ውስጥ ከሊቅ እስከደቂቅ ሁሉ የሚወደውና ሁሉንም ደግሞ የሚወድ ውድ ሰው ነበር፡ እጅግ ብዙ የምለው ነገር ነበረኝ ነገር ግን ከላይ እንደጠቆምኩት ስለ ሰሌ ሳይሆን ስለ እኔ እንዳይመስልብኝ ብቻ ትቼዋለሁ፡፡
አንዳንድ ጊዜ እንዲህ አይነት ሰዎች ገና ብዙ የሚሮጡት ሩጫና የሚዋጉት ውጊያ እያለ ለምን ከእጃችን ላይ አፈትልከው እንደሚያመልጡን አይገባኝም፡ ሁላችንም ብንሆን በሰው አቆጣጠር ሰሌ ያለጊዜው እንደሄደ ነው የምናስበው፣ ነገር ግን ከጊዜ ውጭ ሆኖ ጊዜን የፈጠረና ጊዜን የሚቆጣጠረው ጌታ ለምን ይህን እንዳደረገ እርሱ ብቻ ነው የሚያውቀው።
ከአምስት ቀን በፊት በዓልጋ ላይ እያለ ከአንድ ወንድም ጋር አይተነው ነበር፡ በአይኔ ያየሁትን ለማየት ቢከብደኝም ሰሌ በቀኝ እጁ በእርሱ ትክክል እንድንቆም ስለፈለገ ወደ ግድግዳው እያሳየን "እዛ ጋር ቁሙልኝ" አለ፡ ከዛም እንዲህ አለ፤
"አሁን እዚህ የምታዩት ሰው የደከመ፣ ቆዳው የተሸበሸበ፣ ሽበት የወረሰው ሰው ነው"
እውነት ለመናገር ግን ያለው ሁሉ ትክክል ቢሆንም የመንፈሱን ጥንካሬ ለመግለጽ ግን ቃላት ያንሰኛል፡ ምንም እንኳን ስለሥጋው ድካም ቢናገርም ከቆሮንጦስና ከሮሜ ደብዳቤዎች እየጠቀሰ ስለ ትንሣኤ ይናገር የነበረው እውነት ግን ውስጡ ምን ያህል እንደ ካሌብ ጠንካራ እንደነበር ነው የሚያሳየው: ምንም እንኳን ውጫዊው ሰውነቱ ቢደክምም የውስጥ ሰውነቱ ግን ብርቱ ነበር፡፡
የእዚያኑ ቀን ነበር አንድ እህት ሰሌ ምን እንዳለ ለሌሎች ሰዎች ስትናገር አጠገባቸው ስለነበርሁ ጆሮዬ ጥልቅ ብሎ የገባው፡
"ወገኖች ቀድሜአችሁ ወደክብር ልገባ ነው"
አለ ብላ ስትነግራቸው ሰማሁና፣ ለራሴ እንዴት ያለ መታደል ነው አልኩኝ።
በዚህም ይሁን በዚያ ሁላችንም ሰሌ የሄደውን መንገድ ከመሄድ አንቀርም፡ ስለዚህ ወገኔ ሆይ ለሰሌ አታልቅስ፣ ካለቀስህ ለራስህ አልቅስ፡ ሰሌ መልካሙን ገድል ተጋድሎ ሩጫውን ጨርሶ ሄዷል፡ በሥጋ ስለተለየን ብናዝንም እንደ እውነቱ ግን እድለኛ ነው።
እኔና አንተ አሁን ያልሞትነው በኋላ ስለምንሞት መሆኑን አትርሳ።
ብንሞትም በሕይወት ብንኖርም ስለ ሁሉ ነገር ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን።
✍ ይልቃል ዳንኤል
@nazrawi_tube