በኢስላም ንጉስም ብትሆን ስትሞት ነጭ ከፈን እንጂ ሌላ ለብሰህ አትቀበርም!
ዛሬ በ 73 አመታቸው መሞታቸው የተገለፀው እና በህዝባቸው ዘንድ እጅግ ተወዳጅ እንደነበሩ የሚነገርላቸው የተባበሩት አረብ ኢምሬትሶች ፕሬዝደንት ሼይኽ ከሊፋ ቢን ዛይድ (አላህ ይዘንላቸው) ሰርዓተ ቀብራቸው ተፈፅሟል::
እጅግ የሃብታም ሃገር መሪ ሆነው ቢቆዩም ሲሞቱ ግን እንደማንኛውም ተራ ሰው ባለ ሶስት ነጭ ከፈን ተጠቅልለው ሰላተል ጀናዛ ተሰግዶባቸው አፈር ውስጥ ተቀብረዋል::
በኢስላም ሁሉም ሰው እኩል ነው:: ንጉስም ሁን፣ የሃገር መሪ፣ ባለስልጣን፣ ባለሃብት ፣ምሁር ፣ደሃ፣ጥቁር ሁን ነጭ ስትሞት የአቀባበርህ ሁኔታ ላይ የምትበላለጥበት መንገድ የለም:: ሃብታም ግድግዳ ውስጥ ደሃ አፈር ውስጥ የሚቀበርበት የቀብር ስነ ስርዓት በኢስላም የለም::
በኢስላም ስትሞት ሃብታም ወይንም መሪ ስለሆንክ ዘመናዊ ሙሉ ሱፍ አልያ የተሽቀረቀረ ሙሉ ልብስ ፣እጅግ ውድ እና ዘመናዊ የሬሳ ሳጥን፣እና ሌሎች አጀባዎች ወዘተ.... እንዲኖርህ አይጠበቅም::
የሃገር መሪ ስለሆንክ ታላላቅ የሃገራት መሪዎች እስኪመጡ ፣ ህዝብ አስክሬኑን እስኪሰናበተው፣ የቀብር ስነ ስርዓቱ ለማከናወን የአደባባይ ድግስ እና የሽኝት ፕሮግራም እስኪካሄድ አስክሬኑ ሳይቀበር ይቆይ የሚባል መርህ በኢስላም የለም::
ማንም ሰው ከሞተ ቶሎ አጥቦ፣በነጭ ከፈን ሸፍኖ እና ገንዞ ሰላተል ጀናዛ በመስገድ ወደ ቀብር ወስዶ መቅበር በኢስላም የተደነገገ ነው::
"የሰው ልጆች ሁሉ እንደማበጠሪያ ጥርስ እኩል ናቸው" የሚለው የነብያችን (ሰዓወ) የእኩልነት አስተምህሮ በህይወት እያሉ ብቻ ሳይሆን ሞተንም ቢሆን በቀብር ስርዓታችን ላይ አንዱ ከአንዱ የሚበላለጥበት መንገድ የዘጋ ነው::
ለሞቱት አላህ እዝነቱን ይላክላቸው
abu dawd
@nidatube