የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር👏


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Din


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮንና ስርዓትን የጠበቁ ያሬዳዊ መዝሙሮች ግጥማቸውን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ።@abnat19

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Din
Statistika
Postlar filtri


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ከ15 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

10+10×0+10=???


📕'https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk' rel='nofollow'>✞ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከሐዋርያቱ ጋር የገሊላ ክፍል በሆነችው በቃና በሰርግ ቤት ተገኝቶ ውሃውን ወይን ጠጅ ያደረገበት የሰርግ ደግሶ የነበረው  ማን ነበር ?
     


የሚሸጥ አዲስ ክራር
📍አዲስ እና ለአገልግሎት በጣም የሚፈለግ ክራር ነው።
📌ዋጋ:-5000 ብር
📞ስልክ:-0991725654/ 0717640964
📲በቴሌግራም :-@abnat19
📌ገዢ ብቻ ያናግረን።




ናሁ ሰማን ዜማ(Nahu seman zema) dan repost
✧ፀዓዳ ነው ሠላም✧

ፀዓዳ ነው ሠላም/2/      ፀዓዳ ነው ሠላም/2/
በደሙ የገዛን መድኃኔዓለም    "   "   "   "   "
በገናናው ፍቅሩ አባት ለልጆቹ  "   "   "   "   "
መባረክ ያውቃሉ ያማሩት እጆቹ"   "   "   "   "
      
✥•┈┈•●◉አዝ◉●•┈┈•✥

ፀዓዳ ነው ደጅሽ/2/           ፀዓዳ ነው ደጅሽ/2/
መሶበ-ወርቅ ማርያም መና ነው ልጅሽ "   "   "
ከደጀ ሠላምሽ በፍቅር አድጌ    "   "   "   "
አንብቤ ፊደልን ከፍ አለ መዕረጌ  "  "  "  "
      
✥•┈┈•●◉አዝ◉●•┈┈•✥

ፀዓዳ ነው ውበቷ/2/  ፀዓዳ ነው ውበቷ/2/
የፀሃይ እናቱ ምስራቅ አዛኚቷ   "  "  "
ፀሃይ ተጎናጽፋ ተጫምታ ጨረቃ  "  "  "
አየናት በክብር ፅዮን አሸብርቃ   "  "  "

 ✥•┈•●◉ ናሁ ሰማን-ዜማ ◉●•┈•✥
╭━─━─━─≪✠≫─━─━─━╮
    ✞ @Nahuseman256
    ✞ @Nahuseman256 ✞        
╰━─━─━─≪✠≫─━─━─━╯


ናሁ ሰማን(Nahu seman) dan repost
✧የቅዱስ ሚካኤል ተወዳጅ መዝሙር✧


1.✧የምሕረት መልዓክ
2.✧ከዓለም ባህር ውስጥ
3.✧አማላጅ ነው ሚካኤል
4.✧ይስአል ለነ
5.✧የኃይላት አለቃ
6.✧ፈተና ቢገጥማት
7.✧ሚካኤል ሐመልማለ ወርቅ
8.✧ቅዱስ ሚካኤል እረዳቴ
9.✧በደብረ ምሕረት
10.✧ምድር አበራች
11.✧አድገናል ከደጁ
12.✧ኦ ሚካኤል
13.✧ከሚካኤል በቀር
14.✧​​ድረስ ሚካኤል አጽናኝ
15.✧እረድተሀል እና ባሕራንን
16.✧ሊረዳኝ መጣ
17.✧ሚካኤል ስለው  ስሙን
18.✧ኦ ቅዱስ ሚካኤል
19.✧ባሕራንኒ ይቤ
20.✧​​በበረሃው በሃሩሩ
21.✧የአፎምያ እረዳት
22.✧ሚካኤል ስዩም
23.✧የእኛ አባት ሚካኤል
24.✧ሚካኤል ይለ'ይብኛል
25.✧ሚካኤል ወረደ
26,✧ብዙ ልጆች አሉት
27.✧ኃያል ኃያል
28.✧ይበራል በክንፉ
29.✧የእግዚአብሔር መልዓክ
30.✧ቅዱስ ሚካኤል
31.✧ፈጥኖ ደረሰልኝ
32.✧የስሙ ትርጓሜ
33.✧መና አውርዶ
34.✧አለና ሚካኤል
35.✧ለኔ ያደረገው ሚካኤል

የንግስ ዝማሬ ማግኝት ከፈለጉ የyoutube አካውንታንት ይቀላቀሉ

https://youtube.com/@nahu-seman-zema25?si=yzKlfLRL5bpFSiZ_

꧁  ይ🀄 ላ 🀄ሉ ꧂

❕ የመዝሙራቱን ስም(ርዕስ) በመንካት መዝሙሩን ከነ ግጥሙ ያግኙ




ናሁ ሰማን(Nahu seman) dan repost
🌷እንኳን አደረሰን

"ዘኢያስተርኢ ኅቡዕ እስመ አስተርአየ ለነ::
እሳት በላዒ አምላክነ::"


=>"ጌታ ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ:: እነሆም ሰማያት ተከፈቱ:: የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ: በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ:: እነሆም ድምጽ ከሰማያት መጥቶ:- 'በእርሱ ደስ የሚለኝ: የምወደው ልጄ ይህ ነው' አለ::"
(ማቴ. ፫፥፲፮)


ናሁ ሰማን(Nahu seman) dan repost
✝እንኳን አደረሳችሁ

አቡነ ሐራ ድንግል ጥር 11 ዕረፍታቸው ነው
 ✝️ከአቡነ ሐራ ድንግል በዓለ ዕረፍት በረከት ያድለን።✝




✧ ሃሌ ሃሌ ✧
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ/፪×/
ተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ/፪×/
ተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ/፪×/
#ትርጉም
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ
አምላክ ሆይ ሕዝቦችህ ዳኑ በጥምቀትህ
አምላክ ሆይ ሕዝቦችህ ዳኑ በልደት


 ✥•┈•●◉ ናሁ ሰማን-ዜማ ◉●•┈•✥
╭━─━─━─≪✠≫─━─━─━╮
    ✞ @Nahuseman256
    ✞ @Nahuseman256 ✞        
╰━─━─━─≪✠≫─━─━─━╯


✧ በወንጌሉ ያመናችሁ ✧

በወንጌሉ ያመናችሁ/2/
እንኳን ለብርሃነ  ጥምቀቱ አደረሳችሁ/2/
  
የጠፋዉ ስማችን ከ ክብራችን ጋራ
ይኸዉ ተመለሰ ባምላካችን ስራ
ባርነት ፈታልን ልጆቹ ልንባል
የድንግል ማርያም ልጅ በ ዩርዳኖስ ቆሞል

ጨለማዉ ተገፎ ሠይጣን ተሸንፎ
በጌታ መገለጥ ዓለም ሁሉ አርፎ
ሲጠመቅ በ ዉሀ በእደ ዩሀንስ
የእዳችን___ታየ ሲደመሰስ

ከ ክብሩ የተነሳ ተራሮች ዘለሉ
ደመና ጥላ ቆጥሮ ሲታዘዙ ዋሉ
የሚወደዉ ልጄ ደስም ሚለኝ በርሱ
የሚል ድምፅም ሰማን ሲናገር ቅዱሱ

ይፈር ዛሬ እንግዲ ተዋርዳል ጠላት
ክሳችን ላይ ቆማል ያለም መዳኒት
እረቂቁ በዝቶ ሲመጣ ወደ ምድር
ሸክማችን ተጣለ የተጫነን ቀንበር

 ✥•┈•●◉ ናሁ ሰማን-ዜማ ◉●•┈•✥
╭━─━─━─≪✠≫─━─━─━╮
    ✞ @Nahuseman256
    ✞ @Nahuseman256 ✞        
╰━─━─━─≪✠≫─━─━─━╯


✧ጥምቀተ ባህር✧

ጥምቀተ ባህር ዮርዳኖስ ነያ(፪)
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ(፪)

                   ጌታችን ሲጠመቅ ባሕር ምን አለች
                    አልችለውም ብላ ወደ ኋላ ሸሸች
                    ብርሃነ መለኮት በወንዙ ሲሞላ
                     ዮርዳኖስም ሸሸ ሄደ ወደ ኋላ

አብ በመጣ ጊዜ ደመናውን ጭኖ
መንፈስ ቅዱስ ታየ በርግብ አምሳል ሆኖ
ለልጁ ምስክር ሊሆን ፈለገና
ቃሉን ተናግረ ሆኖ በደመና
                               
ጌታችን ሲጠመቅ በሠላሳ ዓመት
                ባህር ኮበለለች ግዑዟ ፍጥረት
                ሰማይ ተከፈተ ሆነልን ፀአዳ
                ምስጢረ ሥላሴ ታወቀ ተረዳ

እልል በይ ዮርዳኖስ የጥምቀት መገኛ
የፅድቅ መሰላል የድህነት መገኛ
ቀላያት አብርህት ብዙዎች እያሉ
እንደምን ተመረጥሽ ዮርዳኖስ ከሁሉ


 ✥•┈•●◉ ናሁ ሰማን-ዜማ ◉●•┈•✥
╭━─━─━─≪✠≫─━─━─━╮
    ✞ @Nahuseman256
    ✞ @Nahuseman256 ✞        
╰━─━─━─≪✠≫─━─━─━╯


✧ዮሐንስኒ ያጠመቀ✧

ዮሐንስኒ ያጠመቀ/፪×/
በሄኖን/፬×/በማዕዶተ ዮርዳኖስ

እዩት ትህትናው ያጠመቀ
ፅድቁን ተመልከቱ
በባሪያው እጅ ሆኖ
የጌታ ጥምቀቱ

✥•┈┈•●◉አዝ◉●•┈┈•✥

አንተ መናኙ ሰው ያጠመቀ
ቅዱስ ባህታዊ
በእጅህ ተጠምቆ
ኢየሱስ ናዝራዊ

✥•┈┈•●◉አዝ◉●•┈┈•✥

ተሰውሮ ሳለ ያጠመቀ
ካለም ተለይቶ
አዋጁን ስሙ አለ
በጉን አሳይቶ

✥•┈┈•●◉አዝ◉●•┈┈•✥

ንስሐ እየገቡ ያጠመቀ
እየተናዘዙ
በዮሐንስ ስብከት
ለእግዚአብሔር ተገዙ

✥•┈┈•●◉አዝ◉●•┈┈•✥

የሰማዩን ጌታ ያጠመቀ
ምድራዊ ሲያጠምቀው
ሚስጢር ተገለጠ
ዓለም ሁሉ አወቀው

 ✥•┈•●◉ ናሁ ሰማን-ዜማ ◉●•┈•✥
╭━─━─━─≪✠≫─━─━─━╮
    ✞ @Nahuseman256
    ✞ @Nahuseman256 ✞        
╰━─━─━─≪✠≫─━─━─━╯


✧መጻ ቃል ✧

መጻ ቃል እም ደመና ዘይብል/፪×/
መጻ ቃል እም  ደመና ዘይብል/፪×/
ዝንቱ ውዕቱ ወልድየ  ዘአፈቅር
መጣ ቃል  ከደመና እደዚክ የሚል/፪×/
የምወደው የማፈቅረው ልጄ ይህ ነው
   
አደም የለው የእዳ ፅፈት
በዮርዳኖስ ሲወርድ እሣት
በክርስቶስ ተሽሮልን
የልጅነት ክብር አገኛን
መጣ ቃል  ከደመና እደዚክ የሚል/፪×/
የምወደው የማፈቅረው ልጄ ይህ ነው


ባህር አይታው ኮበለለች
ታላቅ ንጉስ መጣ እያለች
ተራሮችም እደኩርማ
መሰከሩው የሡን ግርማ
መጣ ቃል  ከደመና እደዚክ የሚል/፪×/
የምወደው የማፈቅረው ልጄ ይህ ነው


ከእግዚአብሔር ዘንድ መወለድክ
ክርስትና ሞልቶ ክብርክ
ሊቀ ካህን ስራዬህ
አደረገክ በአለ ሟልህ
መጣ ቃል  ከደመና እደዚክ የሚል/፪×/
የምወደው የማፈቅረው ልጄ ይህ ነው


የትትና አስተማራይ
ሠማይ ምድሩን ሁሉን መሪይ
በፍጡሩ በዮሐንስ
ተጠመቀ የእግዚአብሔር ልጅ
መጣ ቃል  ከደመና እደዚክ የሚል/፪×/
የምወደው የማፈቅረው ልጄ ይህ ነው
 ✥•┈•●◉ ናሁ ሰማን-ዜማ ◉●•┈•✥
╭━─━─━─≪✠≫─━─━─━╮
    ✞ @Nahuseman256
    ✞ @Nahuseman256 ✞        
╰━─━─━─≪✠≫─━─━─━╯


✧እግዚኡ መራ✧

እግዚኡ መራ ዮርዳኖስ ዘአብጽሃ/፪×/
ወበ ህየ ዮሐንስ/፪×/ፍጽመ ተሰብሃ
#ትርጉም
ጌታውን መራና ዮርዳኖስ አደረሰው/፪×/
በዚያች ዕለት ዮሐንስ/፪×/በፍፁም ደስ አለው


 ✥•┈•●◉ ናሁ ሰማን-ዜማ ◉●•┈•✥
╭━─━─━─≪✠≫─━─━─━╮
    ✞ @Nahuseman256
    ✞ @Nahuseman256 ✞        
╰━─━─━─≪✠≫─━─━─━╯


✧ከክርስቶስ ፍቅር✧

ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን ማነው/፪×/
መከራ ችግር ስቃይ ወይስ መሰደድ ነው/፪×/
አንፈራም አንሰጋም አንጠራጠርም/፪×/
እግዚአብሔር ከኛ ጋራ ይኖራል ለዘለዓለም/፪×/
የሰማይ ቤታችን አማኑኤል የሠራው/፪×/
ግነቡ ነጹህ ውኃ መሠረቱ ደም ነው/፪×/
ሳይነጋ ተራምደን እንግባ በጠዋት/፪×/
በደሙ መሥርቶ ከሠራልን ቤት/፪×/
ከቶ የት ይገኛል እንዲህ ያለ ቤት/፪×/
የውኃ ግድግዳ የደም መሠረት/፪×/
የውኃ ግድግዳ የደም መሠረት/፪×/
ይኸው እዚህ አለ ያማኑኤል ቤት/፪×/

 ✥•┈•●◉ ናሁ ሰማን-ዜማ ◉●•┈•✥
╭━─━─━─≪✠≫─━─━─━╮
    ✞ @Nahuseman256
    ✞ @Nahuseman256 ✞        
╰━─━─━─≪✠≫─━─━─━╯


✧በፍቅር ተስቦ✧

በፍቅር ተስቦ ወረደ ለኛ ሲል
የፍቅሩን ፍፃሜ ገለፀ በመስቀል
ለኛ ያላረገዉ ከቶ ምን አለና
አፋችን ዝም አይበል እናቅርብ ምስጋና

ደስ ይበለን.....ሰማያትን ቀዶ
ታላቁ አባታችን
የዘመናት ንጉስ
እየሱስ ጌታችን
የኤፍራታዉ ህፃን
በዳዊት ከተማ
ተወልዶ ማደሩን
ምስራች ተሰማ

እንዳንተ ያለ...በሀጥያት ዉስጥ ወድቀን
ስኖር ተጎሳቁለን
አምላክ የኔ ጌታ
ከሞት ዉስጥ አዳንከን
ዝናዉን አዉረዉ
ለአህዛብ ሁሉ
እንደ እግዚአብሔር ያለ
ማንም የለም በሉ

ደስ ይበለን.....ወረደ ወምድር
ሰላሙን ሊሰጠን
ሰላም ለናንተ ይሁን
ብሎ ሰበከልን
በመሰስቀል ተሰቅሎ
እኛን የተቤዘን
ከሲኦል እስራት
በፍቅሩ የ ፈታን

ሃሌ ሉያ......... ምስጋና በሰማይ
ምስጋና በምድር
ሁሉን ቻይ ለሆነዉ
ለቸሩ እግዚአብሔር
ሃሌ ሉያ ለርሱ
ለነፍሳችን ጌታ
ዝማሬን አናቅርብ
ከጠዋት እስከ ማታ

 ✥•┈•●◉ ናሁ ሰማን-ዜማ ◉●•┈•✥
╭━─━─━─≪✠≫─━─━─━╮
    ✞ @Nahuseman256
    ✞ @Nahuseman256 ✞        
╰━─━─━─≪✠≫─━─━─━╯


✧እንዘ ስውር✧

እንዘ ስውር እምኔነ ይእዜሰ ክሱተ ኮነ
ተአምረ ወመንክረ ገብረ መድኃኒነ
በቃና/፪×/ዘገሊላ ከብካበ ኮነ
#ትርጉም
ከእኛ ተሰውሮ የነበረው የጌታ አምላክነት
በገሊላ ሠርግ ግልጽ ሆነ በአምላክነቱ ኃይል ውሃን ወደ ወይን ሲለውጥ።

 ✥•┈•●◉ ናሁ ሰማን-ዜማ ◉●•┈•✥
╭━─━─━─≪✠≫─━─━─━╮
    ✞ @Nahuseman256
    ✞ @Nahuseman256 ✞        
╰━─━─━─≪✠≫─━─━─━╯


✧ ተጠመቀ ጌታ ✧

ተጠመቀ ጌታ ኢየሱስ/፪×/ኧኸ
የሞትን ደብዳቤ ሊደመስስ/፪×/
ተጠመቀ በዩርዲያኖስ

የማይዳሰሰው እሰይ ተጠመቀ
ተዳሰሰ እንደ ሰው
ከላይ ከአርያም
ጥልቅ ፍቅር ሳበው
የእዳውን ደብዳቤ
ሊደመስሰለት
አንዱን ብግ ፍለጋ
መጣ ከሰማያት

✥•┈┈•●◉አዝ◉●•┈┈•✥

አብም በሰማያት
በደመና ሳለ
የምወደው ልጄ
እርሱን ስሙት አለ
መንፈስ ቅዱስ መጥቶ
በእርግብ አማሳል
ምስጢረ ስላሴ
ላለም ተገልፀጿል

✥•┈┈•●◉አዝ◉●•┈┈•✥

ያዳምና የሄዋን
የሞታቸው ጦማር
ይኸው ተቀደደ
ትመስክር ዮርዲያኖስ
የድነቱን አዋጅ
ሰማሁኝ ካባቴ
ይቀኛል ከእንግዲ
ላንተ መድሐኒቴ

✥•┈┈•●◉አዝ◉●•┈┈•✥

አምስት ሺህ ዘመን
አምስት መቶ አመት
ዲያቢሎስ አለሙን
ሲፈነጭበት
ማህተም አትሞ
ቢያስረን በስልጣኑ
በኢየሱስ ጥምቀት
ተፈታ ዘመኑ

 ✥•┈•●◉ ናሁ ሰማን-ዜማ ◉●•┈•✥
╭━─━─━─≪✠≫─━─━─━╮
    ✞ @Nahuseman256
    ✞ @Nahuseman256 ✞        
╰━─━─━─≪✠≫─━─━─━╯

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.