ሀለዋተ እግዚአብሔር / Existence of GOD /
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን !!!
እግዚአብሔር የማይመረመር ረቂቅ በዚህ ጊዜ ተገኘ የማይሉት ቀዳማዊ በዚህ ጊዜ ያልፋል የማይሉት ዳህራዊ ይህን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ የፈጠረ ዳግመኛም ዓለም ከመኖር ወደ አለመኖር አሳልፌ የሚኖር ኃይል ፈጥሮ የሚገዛ ጌታ ነው፡፡ ሰውን ፃድቅ ቢሉት ሀሰት፣ ሀብታም ቢሉት ድህነት፣ ኃያል ቢሉት ደካም ይስማማዋል እሱ ግን ሀብት የሌለበት ጽድቅ፣ ድህነት የሌለበት ባለጸጋ ድካም የሌለበት ኃያል ነው፡፡
@orthodoxtewahedon
ሀለዎተ ሀለወ ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙ መኖር ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሀለዎተ እግዚአብሔር ማለት የእግዚአብሔር መኖር ማት ነው፡፡
ስለሀለዎተ እግዚአብሔር ስንማር በፍጥረታት አዕምሮ የማይመረመር ረቂቅ እና በዓለም ሙሉ የሆነው አምላክ ለፍጥረቱ በፍጥረቱ እንዴት እንደሚገለጥ እንረዳለን፡፡
@orthodoxtewahedon
ሰው በተፈጥሮ በተሰጠው አእምሮ ፈጣሪውን የማመን ዝንባሌ ቢኖረውም የሰው እውቀት እጅግ ውስን በመሆኑ እግዚአብሔር በልዪ ልዩ መንገድ ራሱን ባይገልጽ ኖሮ በራሱ ተመራምሮ ማወቅ አይችልም ነበር፡፡ እግዚአብሔር በወደደው መልኩ ህልውናውን / አኗኗሩን / ለፍጥረታት የሚገልጥባቸው ነገሮች የሚከተሉት ናቸው
ሥነፍጥረት /የፍጥረት ስነ ስርዓት እና አሰራር /
የህሊና ምስክርነት
የሰው ልጅ የተፈጥሮ ዝንባሌ
በመግቦቱ
የቃለ እግዚአብሔርና የታሪክ ምስክርነት
ለዛሬ እግዚአብሔር በወደደ መጠን የተወሰኑትን ለማየት እንሞክራለን
@orthodoxtewahedon
ሥነፍጥረት /የፍጥረት ስነ ስርዓት እና አሰራር
ብዙ ህብረ ቀለም ያላቸው እንደ ሰው ሥራ ተሐድሶ ሳያስፈልጋቸው ዝንተ ዓለም ጸንተው የሚኖሩ ግዙፍና ረቂቅ ፍጥረታት ማራኪ ገጽታ ያላቸው ዓየነ ህሊና የሚመስጡ ውብ ፍጡራን ሁሉ የእግዚአብሔርን መኖር ያሳያሉ፡፡ መዝ 18፡1 ‹‹ ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ ሰማይም ጠፈር የእጁን ስራ ያወራል ›› ሮሜ 1፡20፣ ኢዮብ 12፡7-10 ፤ ዕብ 11፡3
አባታችን አብርሃም ጣዖት ከሚያመልኩት ተለይቶ ወጥቶ የፈጠረውን አምላክ ፍጥረታትን በመረመረ ጊዜ እግዚአብሔር ይፈልገው ለነበረው ለአብርሃም ተገለጠለት፡፡ አብርሃም ፍጥረታትን የፈጠረ ያስገኘ አምላክ እንዲገለጥለት ወዶዋልና የወደደውን አገኘ ስለዚህ የማይለወጥና የማይዛባ የሥነ ፍጥረት ሥርዓት ያለው ዓለም ለእግዚአብሔር መኖሩ ታላቅ ምስክር ነው፡፡ @orthodoxtewahedon
የህሊና ምስክርነት
ሕሊና ማለት በሰውነት ውስጥ የሚገኝ ግብረ ገባዊ የስሜቶች አካል ነው፡፡ ለምሳ የሰውነታችን የአካል ክፍሎች አንዱ የሆነው ዓይናችን አንዱን ነገር ከሌላው የመለየት ችሎታ ያለውን ያህል እንዲሁም ህሊናችን ክፉና ደግ አድራጎቶችን የመለየት ችሎታ አለው ስለዚህም ሰው በህሊናው አነሳሽነት መልካም ይሰራል ከክፉም ይርቃል፡፡ የህሊናውን ምክር ተላልፎ ቢሰራም ህሊናው እንዲፀፀት ያስገድደዋል ይወቅሰዋል ይህም በመሆኑ ቅዱሳን መጻሕፍትን ላላነበበ ሰው እንኳን ቢሆን ህሊናው የእግዚአብሔርን መኖር ይገልጻል ማለት ነው፡፡ @orthodoxtewahedon
እንዴት ቢባል አንድ ሰው ክፉን ማየትና መስማት ባልወደደ ጊዜ ዓይኑን እንደሚጨፍን ጆሮውንም እንደሚይዝ እና ሊሰማው እና ሊያየው ካለው ነገር እንዲከለከል፣ ሰው ከህሊናው ምክር ተከልክሎ ክፉ ቢደርግ ህሊናው ይወቅሰዋል ፣ ይጨነቃል አይኑን ጨፍኖ አላይም እንደሚል ህሊናውን ግን ሊያዘው እንደወደደው ሊያደርገው አይቻለውም በሰውነት ውስጥ ያለ ነገር ግን በሰውየው ፈቃድ የማይታዘዝ ህሊናችን ስለምንድን ነው ከኛም ላይ ሆኖ የሚመራን ማነው ብለን እንድንጠይቅ ያደርገናል በዚህም ጊዜ ሁሉን የፈጠረ ከኛ በላይ ሆኖ የሚመራ አምላክ እንዳለ እንረዳለን ስለዚህ ነው ሐዋርያው ጳውሎስ ለሮሜ በላከላቸው መልዕክቱ ሮሜ 2፡14-15 ‹‹ ህግ የሌላቸው አህዛብ ከባህሪያቸው የህግን ትዕዛዝ ሲያደርጉ እነዚያ ህግ ባይኖራቸው እንኳን ለራሳቸው ህግ ናቸውና እነርሱም ህሊናቸው ሲመሰክርላቸው አሳባቸውም እርስ በርሱ ሲካሰስ ሲያመካኝ በልባቸው የተፃፈውን የህግ ስራ ያሳያሉ፡፡›› ማለቱ ከዚህ የምንረዳው ለደጉም ሆነ ለክፉ እንደስራው ዋጋ የሚከፍልና ሳያዳላ የሚፈርድ ከሁሉ በላይ የሆነ አንድ አምላክ መኖሩ ነው፡፡
@orthodoxtewahedon
@orthodoxtewahedon
@orthodoxtewahedon
.
.
.
ይቆየን !!!