#ከንቱ_ነኝ
ከንቱ ነኝ የከንቱ ከንቱነኝ
ዋስትና መከታ እግዚአብሔር ካልሆነኝ
ተስፋ የሚሆነኝ ሕይወት የሚሰጠኝ
አምላኬ ብቻ ነው የሚያስተማምነኝ
እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚያስተማምነኝ
#አዝ
እኔ ንጉሥ ነበርኩ በክብር ያጌጥኩኝ
ሁሉን በምድር ላይ በጥበብ ፈጸምኩኝ
የዚህ ዓለም ደስታ ምንም አላዋጣኝ
በመጨረሻውም በሞት ተወሰድኩኝ (2)
#አዝ
ከጣይቱ በታች አዲስ ነገር የለም
ሰዎች ይደክማሉ እስከ ዘለዓለም
ጥበብን ፍለጋ ደክሜ ነበረ
ሁሉም ከንቱ ሆኖ በመቃብር ቀረ (2)
#አዝ
ከኔ አስቀድመው የከበሩ ሁሉ
አፈር ተጭኗቸው በመቃብር አሉ
እብደትና እውቀት ሁሉን አወኳቸው
ምንም ቋሚ የለም ሁሉም ከንቱ ናቸው (2)
#አዝ
ልቤን የጣልኩበት ተስፋ ያደረኩት
አልጨበጥ ብሎኝ አለሁኝ ስታክት
የጥበብም ብዛት ለትካዜ ሰጠኝ
እኔ በዚህ ምድር ጐስቋላ ፍጥረት ነኝ (2)
#አዝ
ልቤንም ፈተንኩት በደስታ ብዛት
የዚህን ዓለም ለውጥ ጣሙን አቀመስኩት
ሳቅም በልቤ ውስጥ ይፍለቀለቅ ነበር
ሁሉም ከንቱ ሆነ ገብቶ ከመቃብር (2)
ሊቀ መዘምራን
ይልማ ኃይሉ
👉 @yemariyam_lejoch👈
✍ለሀሳብ አስተያየትዎ📩
📩 @yemariyam_lejochbot
ከንቱ ነኝ የከንቱ ከንቱነኝ
ዋስትና መከታ እግዚአብሔር ካልሆነኝ
ተስፋ የሚሆነኝ ሕይወት የሚሰጠኝ
አምላኬ ብቻ ነው የሚያስተማምነኝ
እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚያስተማምነኝ
#አዝ
እኔ ንጉሥ ነበርኩ በክብር ያጌጥኩኝ
ሁሉን በምድር ላይ በጥበብ ፈጸምኩኝ
የዚህ ዓለም ደስታ ምንም አላዋጣኝ
በመጨረሻውም በሞት ተወሰድኩኝ (2)
#አዝ
ከጣይቱ በታች አዲስ ነገር የለም
ሰዎች ይደክማሉ እስከ ዘለዓለም
ጥበብን ፍለጋ ደክሜ ነበረ
ሁሉም ከንቱ ሆኖ በመቃብር ቀረ (2)
#አዝ
ከኔ አስቀድመው የከበሩ ሁሉ
አፈር ተጭኗቸው በመቃብር አሉ
እብደትና እውቀት ሁሉን አወኳቸው
ምንም ቋሚ የለም ሁሉም ከንቱ ናቸው (2)
#አዝ
ልቤን የጣልኩበት ተስፋ ያደረኩት
አልጨበጥ ብሎኝ አለሁኝ ስታክት
የጥበብም ብዛት ለትካዜ ሰጠኝ
እኔ በዚህ ምድር ጐስቋላ ፍጥረት ነኝ (2)
#አዝ
ልቤንም ፈተንኩት በደስታ ብዛት
የዚህን ዓለም ለውጥ ጣሙን አቀመስኩት
ሳቅም በልቤ ውስጥ ይፍለቀለቅ ነበር
ሁሉም ከንቱ ሆነ ገብቶ ከመቃብር (2)
ሊቀ መዘምራን
ይልማ ኃይሉ
👉 @yemariyam_lejoch👈
✍ለሀሳብ አስተያየትዎ📩
📩 @yemariyam_lejochbot