𝐑𝐢𝐨 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜✌️


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Din


...................꧁﷽꧂.....................

#ኢስላማዊ_መረጃዎች
#ኢስላማዊ_ታሪኮች
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረቱ_ታሪኮች
#አጫጭር_ዳዕዋዎች እና
#የተለያዩ_ሀዲሶችን_ያገኛሉ
#owner 👉 #riyad (#rio)
for any comment @rio_comment_bot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Din
Statistika
Postlar filtri


መስጂድ ጫማ የተወደሰበት ሰው ምን አይነት አዝካር /ዱዓ / ነው ማድረግ ያለበት? 😢


.
በነገራችን ላይ ጀነት ውስጥ ላጤ የለም 🥰

©rio once upon a time 😅


ምኞቶቻችንን ሌሎች እየኖሩት ይሆናል, ነገር ግን እኛም የሌሎችን ምኞት እየኖርን ነው.. ዱንያ ይች ናት 👌

502 0 11 1 44

.
በራህመትህ አነጋን....
በፍቃድህም ዐይናችንን ከፈትን....
ተውበት ማድረጊያም ሌላ እድል ሰጠከን::

አልሃምዱሊላህ ❤️

@rio_islamic


.
እንዲው እንደተዘናጋን አንተን ከመገናኘት በአንተ እንጠበቃለን 🙏


ሁሉም መድሃኒቶች መራራ ናቸው ቁርአን ሲቀር


@rio_islamic


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ፈጅር 🥰

@rio_islamic


የቱርክ እና የኮሪያ ፊልም ላይ ያየሽውን ዓይነት ወንድ ስትጠብቂ ቆመሽ ትቀሪያለሽ😌


ኢትዮጵያዊ መሆንሽንም እያሰብሽ ማለቴ እየተሳሰብን🤌❤️

1.5k 0 13 51 74

ሁሉም ሰው በያንዳንዷ ስራው የሚመነዳበት ቀን አለ ስራችሁን አሳምሩ 🙌


* በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ/ውጪ።

* ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል/በይ።

* ሰምቶ ማመን
ከተጎዱት መማር አስተዋይነት ነው🙌


.
አስር ብስራቶች ፈጅር ሶላትን በጀማዓ ለሰገደ ሰው 🙌

እነዚህ ብስራቶችን አንብቦ የፈጅር ሶላት የሚያመልጠው ሰው ይኖራል ብዬ አላስብም❗

▪ ብስራት ①
👉🏼 ለቂያም ለት ሙሉ ብርሃን


ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:

{ በጨለማ ወደ መስጂዶች የሚሄዱትን ለቂያም ለት ሙሉ ብርሃን እንደሚኖራቸው አበስራቸው። }

▪ብስራት ②
👉🏼 የፈጅር ሁለት ሱና ሶላቶች ከአዱንያና በውስጧ ካለው ነገር ይበልጣሉ።

ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:

{ የፈጅር ሁለት ሱና ሶላቶች ከአዱንያና በውስጧ ካለው ነገር ይበልጣሉ። }

▪ብስራት ③
👉🏼 ወደ መስጊድ በሚራመደው ልክ ምንዳ ይፃፍለታል።

ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:

{ ከቤቱ ወደ መስጂድ የወጣ ሰው… በሚራመደው እያንዳንዷ እርምጃ አስራ አጅር ይፃፍለታል… }

▪ብስራት ④
👉🏼 የመላኢኮች ምስክርነት


አሏህ እንዲህ ብለሏል:

{ ሶላትን ከፀሐይ መዘንበል እስከ ሌሊት ጨለማ ድረስ ስገድ፡፡ የጎህንም ሶላት ስገድ፡፡ የጎህ ሶላት (መላእክት) የሚጣዱት ነውና፡፡ }

▪ብስራት ⑤
👉🏼 ከእሳት መዳን


ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:

{ ከፀሐይ መውጣትና መግባት በፊት– ማለትም ፈጅርና አሱር – የሰገደ ሰው ጀሀነም አይገባም። }

▪ብስራት ⑥
👉🏼 አሏህን ማየት


ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:

{ ጨረቃዋ ሙሉ በነበረችበር አንድ ለሊት ነቢዩ (ሰ ዐ ወ) ዘንድ ነበርን። ነቢዩ (ሰ ዐ ወ) ጨረቃዋን ተመለከቱና እንዲህ አሉ: "እናንተ ይህን ጨረቃ ሳትጨናነቁ እንደምታዩት አሏህንም ታዩታላችሁ… ከቻላችሁ ከፀሐይ መውጣትና መግባት በፊት ባለው ሶላት አትሸነፉ። ማለትም ፈጅርና አሱር። }

▪ብስራት ⑦
👉🏼 የለሊት ሶላት ምንዳ


ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:

{ ኢሻ ሶላትን በጀመዓ የሰገደ የለሊቱን ግማሽ እንደቆመ ይቆጠራል። ፈጅርን በጀማዓ የሰገደ ሰው ደግሞ ለሊቱን ሙሉ በጀመዓ እንደሰገደ ይቆጠራል። }

▪ብስራት ⑧ 
👉🏼 የመላኢካዎች ዱዓ


ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:

{ ፈጅር ሶላት ሰግዶ በመስገጃው ላይ ቁጭ ያለ መላኢካዎች በርሱ ላይ ሰለዋት ያወርዳሉ። የነርሱ ሰለዋት: አሏህ ሆይ ማረው አሏህ ሆይ እዘንለት ነው። }

▪ብስራት ⑨
👉🏼 የሐጅና የዑምራ ምንዳ


ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:

{ የፈጅር ሶላትን በጀማዓ የሰገደና ፀሐይ እስትወጣ ቁጭ ብሎ ዚክር ያደረገ ከዚያ ሁለት ረከዓ የሰገደ ልክ እንደ ሙሉ የሐጅና ዑምራ ምንዳ ይሆንለታል።}

▪ብስራት ⑩
👉🏼 በአሏህ ከለላና ጥበቃ ስር


ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:

{ ፈጅር ሶላት የሰገደ ሰው በአሏህ ከለላ ስር ነው። በአሏህ ከለላ ስር ያለን ሰው ነክታችሁ አሏህ እንዳያሳድዳችሁ። አሏህ ያሳደደው ሰው ይደርስበትና ጀሀነም ውስጥ ይደፋዋል። }


አሏህ ሆይ የፈጅር ሶላትን አግራልን 🥰

#share
@rio_islamic


የረሂሙ እገዛ ለዚያች ነፍስ የጌታዋን መንገድ ላለመሳት እየተወላገደች ላለች 🥺


.
ያኔ በልጅነት መስጅድ ቁጭ ብለን በቂርአት እና በጨዋታ ያሳለፍናቸው ጊዜያት ምነኛ ያማሩ ነበሩ 🥰

@rio_islamic


☝️ከሻእባን ወረ የቻልከውን ከመፃም አትዘናጋ ‼️

ከእናታች አኢሻ رضي الله عنهاእነደተወራው የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم የሻእባን ወረን ሁሉንም ይፃሙት ነበረ
የሻእባነን ወረ የተወሰነውን ይፃሙ ነበረ
ሙስሊም ዘግቦታል 1156


ነገ ሐሙስ ነው የቻለ ይፁም ያልቻለ ያስታውስ 🙌


የአንዳንድ ሰወችን ያለፈ ወንጀል ደጋግመን እናነሳለን ምናልባትም እኮ ጌታቸው ምሮላቸዋል 🥺



They sayd
🗣- አጥንቱ ደክሟል
🗣:- ሽበት ወሮታል
🗣:-ሚስቱም መካን(መውለድ የማትችል ነች
.
አስታውስ ሰዎች በዘለፉት ጊዜ ተስፋን ለማስቆረጥ በተነሱ ጊዜ በጌታው ሲመካ 👌

እጁን ከፍ አደረገና🤲(فَهَبۡ لِی مِن لَّدُنكَ وَلِیࣰّا)ብሎ ለመነ

ብስራቱም ከተፍ አለ (یَـٰزَكَرِیَّاۤ إِنَّا نُبَشِّرُكَ بِغُلَـٰمٍ )

ልቡ በጌታው ላይ እምነትን ባሳረፈች ሰዐት ያመነው አካል አላሳፈረውም እጁን ዘርግቶ የለመነው ነገር መና አልቀረበትም ...

ቀልቡ ከአላህ ጋር ያስተሳሰረ ምክንያት እና ሰበቦችን አገራለት
አላህ ከእቅፉ እሱን ከመኸጀል አያቦዝነን 🙌


.
ለ ወንዶች ደግሞ .....

ቢክራ ያልሆነች ሴት ባጠቃላይ ባህሪዋ የተበላሸና " ሴሰኛ " ነች ማለት አይደለም ፡
እንደውም ከተቃራኒ ፆታ ጋር ግንኙነት ሳታደርግ ቢክራነቷ ሊወገድ የሚችልባቸው ሁኔታዎች አሉ ፡፡
ከነዚህ ውስጥ
👉የተለያዩ ስፖርቶችን መስራትና
👉ከባባድ እቃዎችን ማንሳት ይገኙበታል ፡፡

ደግሞም ከዚህ ቀደም ሀራም ግንኙነት የፈፀመች ብትሆንና ዛሬ ላይ ከወንጀሎቿ ሁሉ ፍፁም ተፀፅታ የተመለሰች ከሆነ ምንድነው ችግሩ ፡፡
ደም ካላየህ አይሆንልህም እንዴ ?
አዎ ነው ያልከው ( ? ) .... እንግዲያውስ ደም ከሆነ የምትፈልገው ዶሮ እረድ !😁😁

©repost

@rio_islamic

2.1k 0 17 35 80

ወንድሜ❤️‍🩹
በሕይወት መኖር ስኬት አይደለም ማሸነፍ አይደለም መሞትም መሸነፍ አይደለም ..

ማሰብ ያለብህ እንዴት ነው የምኖረው የሚለው ነው?በምን ሁኔታስ ነው አሟሟትህ?
ሱጁድ ላይ ሁኖ ሞተ እየፆመ ሞተ ቁርዓን እያነበበ ሞተ ለይል ሰላት እየሰገደ ሞተ .. .እኚህ. ሁሉ አጋጣሚ እንዳይመስሉህ የምትኖርበትን ሂወት ነው የሚገልፁልህ የምትሞተው በሂወትህ በተደጋጋሚ በምታዘወትረው ነገር ላይ ነው አኗኗርህን አሳምረህ አሟሟትህ እንዲያምር አላህን ጠይቅ🙌

2k 0 14 1 39

እንደ ቀልድ ችላ ያልናቸውን ሰወች የሆነ ጊዜ በተግባራችን የምናፍርበት ሁኔታ ዉስጥ ሆነው እናያቸዋለን
https://t.me/rio_islamic

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.