ሳሙኤል አለሙ-Samuel alemu


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


ሌላ መገኛዬ...
facebook.com/samialemu

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


ስንዝር አይሞላም ፥ የምኞቷ አድማስ
ትቢያ አይገኝም ፥ መንገዷ ቢማስ
ከንቱ ፍጥረት ናት ፥ መለመል አናት
ብለን ያማናት
ጠጋ ብንልስ
አጃኢባ ናት !

አንድ ቀን በርዶን
ቀሚሷ አሻፍዶን
ቤቷ ብንከትም
ለካ ነፍስ ናት ፆታ የላትም ።

ትሁት ስትሆን አንጀቷ አሳሳን
ስትስቅ ብናያት
ገላ ተረሳን ።

"ግቡ" አለችን ...
ጫማ ብናወልቅ
ከለከለችን ።
ውሃ ብንላት
እርጎ ሰጠችን ።
በአቦል ቡናዋ
ደግሞም በልቧ
አሳረፈችን ።
አስገረመችን !

ደሞ ይሄ ልቧ !
ጎልያድ ከጭፍራው ደርቦ የሚጥል
ነፍስን ከስጋ ደርሶ 'ሚነጥል
የዳዊት አቻ ፥ የእግዜር ቅምጥል ።
እንዳመጣልን...
አንዱን አንስተን
አንዱን ስንጥል
ገላም ሳይሞኝ ፥ ስጋም ሳይሰጋ
ሌት ስናወጋ
ነጋ !

ከእንግዲህ  ምን ቀረን ?
ከእንግዲህ ምን አጣን ?
"ወንዶች" ሆነን ገብተን ሰዎች ሆነን ወጣን ።

© Hab HD  


@Samuelalemuu


አንድ ሳቅ አላት

መስከረም ጥቅምት:
ከላፍቶ ዳገት - እንደሚነሳ፥
ልብ የሚያሳቅል - ቀልብ የሚነሳ፥
የጽጌ ሰሞን...
የአደይ አበባ - የጸደይ ሽታ...
አንድ ሳቅ አላት - አንድ ፈገግታ።

የናፍቆት አፀድ - የፍቅር ሰፈር፥
አንገት የሚስም - ልክ እንደከንፈር፥
እንደመልዐክ - በግራ በቀኝ፥
እያረበበ..
ከዘመን ክፉ - የሚደብቀኝ - የሚጠብቀኝ፥
አንድ ሳቅ አላት።

ከእሷ አፍ ብቻ - የሚስገመገም፥
በምድር እድሜ - የማይደገም፥
የማይቻለን - የሚቻልላት፥
አንድ ሳቅ አላት።

የሰማይ ደረት - ተሸነቆረ፤
እንደጣቃ ጨርቅ - ተተረተረ፤
ትርትሩ መሐል - ዐይኔ ቢከተኝ፥
ቅዱስ ቅዱሱን - አመላከተኝ፥
አመላከተኝ - ተስፋ መቅደሱን፤
አንድ ሳቅ አላት...
ከሆነ ቦታ - ስቃለች እሱን።

           [ ሚካኤል ምናሴ ]

@Samuelalemuu


ብየ አልነበር ..?
ጠይም መለሎ ጠይም ሳቅ ያለዉ
ዝግ ያለ አንደበት ጀሊል ያደለዉ
ብየ አልነበረ ..?
ደሞ እንደዋዛ እንዲሁ እንደቀልድ
መዳፌ መሀል የሳመኝ ስሞሽ
በአለንጋ ጣቱ የሰጠኝ ጥሎሽ
ጨፍጋጋ ዉሎ ከቀን የሚያሸሽ

የግጥም ሀድራ በአቅል ደግሶ
የለዛ ጉፍታ በላየ አልብሶ
ያቀማጠለኝ
(ምንስ አጉድሎኝ )

ብየ አልነበረ ..?
እሱኑ እሱን
ቀልበ ልስልሱን
የአቅሉን ጌታ
የሙሀባ አንባ የመዉደድ ዳሱን

በየ ዱአየ ..
አይኔ እሱን ባየ
ብየ አልነበረ..?

(ሰምቶኝ ነዉ መሰል
አይቶኝ ነዉ መሰል )

መርጦ ወደደኝ
ጀሊል አጣጋኝ
ከወደነፍሱ
ጀባኝ ጌትየ 
ጥንቱን  ልቤ ዉስጥ ላለቀዉ እሱ..!

                  [ Samiya Tuha ]


@Samuelalemu


እንኳን ለካራማራ የድል በዓል በሰላም አደረሳቹ🔥😍💪


@Samuelalemuu


አንዳንዴ
ጠላት ሲሆን ሳር ቅጠሉ
ተስፋ ሳጣ ሲዞር ሁሉ
በሀዘኔ
በሕመሜ ፣ በድቀቴ በመሀሉ
እየመጣሁ የማርፍባት
የምትቀርበኝ የምቀርባት
ያቺ ድንጋይ
እሷም ጠልታ የሰው ጠረን
እሷም ጠልታ የሰው ገላ
ገደል ገባች ተንከባላ

[ ሄኖክ በቀለ ]


@Samuelalemuu


ልፃፍሽ ወይ ግጥም?

አንቺ ውብ በራሪ፡
አንቺ ትንግርት ሀሳብ
አፈር ላይ በልቤ፡ ወድቄ ከምሳብ
ከኔ ዘንድ የመጣሽ
አንች ሀሳብ ምረጪ፡
ምንድን ይሁን እጣሽ?

ንገሪኝ...ልፃፍሽ?
ልግለጥሽ በግጥም?
ወይ ልቤ ደብቄሽ፡ ውበትሽን ላጣጥም?
ወይስ እንዳላየ፡ ልተውሽ በእንጥልጥል?
ከኔ የላቀ ሊቅ፡ ዐይኖቹን እስኪጥል
ያ'ፈር ላይ ኑሮዬን፡ አርፌ ልቀጥል?

አንቺ ውብ በራሪ
ክንፋም ተወርዋሪ
ሀሳብ ተናገሪ
ምን ላርግሽ? ወስኚ
መልክሽን ገጥሜው የኔ ብትሰኚ
የብርሃን ክንፍሽ፡ በቃል ይታሰራል
ልትሆኝ የነበረ፡
እጣ ፈንታሽ ሁሉ፡ ግጥም ሆኖ ይቀራል

ረቂቅ ነውና፡ የሀሳብ ፍጥረቱ
ፊደል ሲወስነው፡ በጠባብ ደረቱ
ውብ ቢሆን መናኛ፡ ድንቅም ቢሆን ከንቱ
እንዳከሳሰቱ፡ የሚያሳሳ የታል?
ያሰቡት ድንቅ ሁሉ፡ ሲፅፉት ይሞታል።

አንች ሀሳብ ያሰብኩሽ
ንገሪኝ ምን ላርግሽ?
ላኑርሽ? ሳልገጥም?
ታምርሽን በልቤ ፡ሰውሬ ላጣጥም
አውጥቼ አውርጄ፡ ላስብ ላብሰልስልሽ
በህልም በሰመመን፡ በምናብ ላድንቅሽ
ዝም ብዬ ላልቅስሽ? ዝም ብዬ ልሳቅሽ?
የሌቴን መከራ ፡ የቀኔን አበሳ
አስታወሼሽ ልርሳ?
አልል ልቤ ሳሳ
ስኖር የኖርኩብሽ፡ ስሞት ብትሞቺሳ?

አንች ሀሳብ ያሰብኩሽ
ንገሪኝ ልተውሽ? ጉጉቴን ገትቼ
ውበት ትንግርትሽን፡ ለሚገባው ትቼ
ስትበሪ አቅርቅሬ፡ ትቢያውን ቃርሜ
ሚስጥርሽን ባዕድ፡ ውበትሽን እርሜ
ላድርግ ልፀየፈው?
የሆንሽውን ሁሉ፡ የሆነ እስኪፅፈው
አንች ሀሳብ ክንፍሽን፡ ተስቤ ልለፈው... ?

ንገሪኝ? ሀሳቤ
ከግጥም ከልቤ
ወይ ደሞ ከመተው
ከየቱ ስልቻ፡ እጣሽን ልክተተው?
የት ላርግሽ ንገሪኝ፡ እኔ ልክ አላውቅም
መጠየቅ ብቻ ነው፡ የፀሐፊ አቅም።

#rediet_assefa

@Samuelalemuu


የገጠር ትልቅ ድስት ይባላል ሰታቴ!

(በእውቀቱ ስዩም)

ያኔ የዩንቨርስቲ ተማሪ እያለን አንድ ክልስ ጓደኛ ነበረን፤ ቶማስ ይባላል፤ አባቱ ጣልያን ሲሆን እናቱ ደግሞ ኢትዮጵያዊት ናት፤ ጠጉሩ የበቆሎ እሸት መነሳነስ ይመስላል፤ በክልስነቱ የሚሰነዘርበት አሉታዊ አስተያየት ምቾት አይሰጠውም ነበር፤አንድ ቀን፥ የአድዋ በአልን ለማክበር በተዘጋጀ ተውኔት ላይ እንደ ጀኔራል ባልዴሴራ ሆኖ እንዲጫወት ሲጠየቅ በጣም ተናደደ “ ሲጀመር የምታስቡትን ያክል ፈረንጅ አልመስልም! ብመስል እንኳ፥ ያንን በስባሳ ጄኔራል ሆኘ አልጫወትም! ከፈለጋችሁ ያጤ ምኒልክ አማካሪ የነበረውን ስዊዘርላንዳዊ ኢልግን ሆኘ መተወን እችላለሁ” ብሎ መለሰ:
:
ተውኔቱን የጻፈው እና ምኒልክን እና ባልቻን ደርቦ የሚጫወተው ተኮላ ግን ገገመ፤

“ እሺ ጄኔራል ባልዴሴራን ሆኖ መተወን ከደበረህ የጣልያኑን ንጉስ ኡምበርቶን ሆነህ ተጫወትልን ”

ቶማስ ንዴቱን መቆጣጠር አልቻለም ፤

“ እናትህን ንጉስ ኡምበርቶ ይርዳልህ! ሲጀመር አንተ የኡጋንዳውን ፕሬዚዳንት ኢዲ አሚንን ዳዳን እንጂ ምኒልክን አትመስልም! እኔ ንጉስ ኡምበርቶን ሆኘ የምተውነው አንተ የንጉሱን ዙፋን ሆነህ ከተጫወትክ ነው” በማለት አንባረቀ ፤


ቶማስ ብዙ ጊዜ ከጣልያን ጋር ግኑኝነት ያላቸውን ቃሎችን ላለመጠቀም ይጠነቀቃል፤ ለምሳሌ ማኪያቶ ላለማለት፥ ካፌ ገብቶ “እስቲ የቡና እና የወተት ብርዝ አምጡልኝ “ ብሎ ያዝዛል፤ “ጓንት” የሚለውን ቃል አይጠቀምም፤ “የእጅ ፓንት “ የሚለውን ቃል ይመርጣል፤

በግጥም ምሽት ላይ የሚያቀርባቸው ግጥሞች ባብዛኛው ለኢትዮጵያዊነቱ አጽንኦት የሚሰጡ ነበሩ፤

‘የገጠር ትልቅ ድስት ይባላል “ሰታቴ”
ጥርጥር የለኝም በኢትዮጵያዊነቴ”

የሚለው ስንኙ አይረሳኝም፤

የሆነ ጊዜ ላይ ሰይጣን ልጁን ሲድር ፥ ለሰርጉ ድምቀት ግቢያችን ውስጥ የብሄር ግጭት አስነሳ! የተወሰኑ ተማሪዎች በሁለት ብሄሮች ተቧድነው መሸካሸክ ጀመሩ፤ የዚህች ወግ ጸሀፊን ጨምሮ ብዙ ተማሪዎች ዶርማቸውን ቆልፈው መሸጉ፤ አመሻሽ ላይ ቶማስ ግጭቱ በርዷል ብሎ በመገት ወደ ካፌ እየተራመደ እያለ ፌሮና ድንጋይ የታጠቁ ጥቂት ተማሪዎች ወደሱ ሲሮጡ ተመለከተ፤ ባልበላ ጉልበቱ ትንሽ እንደሮጠ ስቴድየሙ አካባቢ ደረሱበት፤

ቶማስ እጁን ወገቡ ላይ አድርጎ ባጭር ባጭሩ እየተነፈሰ እንዲህ አለ፤

“ ወንድሞቼ ! እኔ ብሄር የለኝም ! እልል ያልሁ ጣልያን ነኝ ! እኔን በመደብደብ ኢትዮጵያን ከአውሮፓ ህብረት ጋር ደም እንዳታቃቧት"


@Samuelalemuu


እንኳን ለአድዋ የድል በአል በሰላም አደረሳቹ🇪🇹🔥💪

@Samuelalemuu


እዚህ ባልሆን
በዚህ ሰአት
ምናልባትም እንዲህ ባልሆን፣
ልሆን የምችለው
እሆነው የነበር የሆነ ሰው ይኖር ይሆን?

ትልቅ ምናልባት ነው
ማለቴ ምናልባት
መለኪያ ባልጨብጥ
አረቂ ባልጠጣ መለኪያውን ባልሰብር፣
የሆነች ቆንጆ ጋር
ጭማቂ እየጠጣሁ
እጇን እየዳበስኩ
አይንአይኗን እያየሁ ሊሆን ይችል ነበር።

ትልቅ ምናልባት ነው
ግን ከዚህ የሚሻል የሆነ 'እኔ' አይጠፋም፣
የሰውን ማንነት 'መሆኑ' አይገልፀውም።

ትልቅ ምናልባት ነው፣
ምናልባት ምናልባት
ሌላ ነበርሽ አሁን
የሆነ ቀን ለታ አንችን ባትሆኚ፣
የዛኑ ቀን ወጥተሽ እኔን ባታገኚ፣
ከህይወት ታሪክሽ ይቺ ቅንጣት ብትቀር፣
የያዝሽው ሲጃራ እጣን ይሆን ነበር፣

ትልቅ ምናልባት ነው...

[ FB; vector de morta ]



@Samuelalemu


ልብ ያልላልኩት )

አረግሽኝ እንጂ
የከውኑ የአለሙ አዲስ እንግዳ
ጀባሽኝ እንጂ
ሩጬ ማልሸሸው ማኣት ዱብዳ

አፍዝዞ ያደናገረኝ
አክላቁን ውሉን የሳትኩት
ድሮንስ ይሄን አልነበር
ደግሜ ደግሜ የኖርኩት

ሁሉንም አውቃቸዋለሁ
አኳኳን አከራረመሙን
ሰው ከሰው ይሰማል እንጂ
መለያ መጠሪያ ስሙን

መራቅሽ ያንሰፈሰፈኝ
ናፍቆትሽ ያንገበገበኝ
የማጀት የእልፍኜን ዝቆ
ለራቤ እስኪመግበኝ

አላውቅም የራሴ እንደሆን
ይህ ሁሉ የኔ እንደነበር
በልክሽ አቁሜ ስኖር
በሩሄ በጅስሜ ማገር

ቃላባይ ልብሽን አይቶ
መሄድሽ ጠልቆ ነገርኝ
ለነገ መንገድ ሚሆን
ብዙ ስንቅ እንደነበረኝ

[ አዲብ ]



@Samuelalemuu


ጀምበር ገባች ፥ መሸ
ያጸዳሁት ቤቴም ፥ መልሶ ቆሸሸ
አልጠፋም መብራቱ
አልተበላም 'ራቱ
አሁንም ክፍት ነው በርና መስኮቱ ።
ለቁር ተጋለጠ ፥ ጓዳዬ እንደ ውጪው
መቼ ነው የምትመጪው ?

መጽሐፍ ገለጥኩና መልሼ ዘጋሁት
ልጽፍ አሰብኩና ብዕሬን ወረወርኩት
መቆም መንጎራደድ
መቆም መንጎራደድ
መቆዘም መተከዝ ፥ በሐሳብ መሰደድ
ደርሶ ብንን ብንን
ደሞ ቁጭ ብድግ
ካንቺ ውጭ አላውቅም ምን እንደምፈልግ ።

ምኞት ነው ያለኝ  ፥ ዝም ብሎ ምኞት
ወይ የማያኖር ፥ ወይ የማያስሞት

ትመጫለሽ እያልኩ በጉጉት ከምኖር
ምናለ በሞትኩኝ ለአንድ ለስድስት ወር ።

By Hab Hd

@Samuelalemuu


.            ተንበርክኮ መድረስ
           ተጎንብሶ መንገስ
        አቀርቅሮ  ሹመት
   አሽቀንጥሮ ድሎት
                 ጸሎት

እስኪበሩ ማንከስ
   እስኪስቁ ማልቀስ
      እስኪይዙ ማጣት
           እስኪረቱ ችሎት
                             ጸሎት

By Rediet Aseffa


@Samuelalemuu



ስለሚገባው ፣ ሰው የማይገባው
በጽሑፍ አልቅስ ፣ ሆዱን አባባው።
“ንገረኝ” ሳይል የሰበረህን
“የት ጋ ነው?” ሳይል ስብራትህን
ያንተ ወጌሻ ፣ ስለሚያክምህ …
ግጥም ጻፍለት
ሥዕል ሳልለት ፣ ጸሎት ሲደክምህ🖤

[ Henok B ]


@Samuelalemuu


'የአባቴን ባድማ ፈሪ ገብቶ አረሰው
የጀግናውን ሽመል ሞኝ ተንተራሰው፣
እንዲያ እንዲያ ቢሆን ነው ሀገር የሚያለቅሰው።'
ትለኛለህ ምነው ?!
ልጅህ ደርሶ ሳለ አባባ የሚልህ
ልጅህ ደርሶ ሳለ ጀግናዬ የሚልህ
አንተም ወደ ትላንት ነገር ማንጠልጠልህ።

ያው እንደምታየው አሁን አንተና እኔ
አልፈጠረብንም አንዳች ሀሞት ወኔ!
የተረፈን አቅም የያዝነው ቁምነገር ፣
"ወዴት ልትሄድ ነው?!" ማለት ነው ይች አገር ።

[ አስካል ]


@Samuelalemuu


ይኸው ደሞ ክረምት ሆነ
ትዝታ ከደጅ አደረ፤
የአምናን መዝሙር
በአሁን አቅም
በክራሩ ደረደረ።

ናፈቀ አዲስ መስከረም፤
ተመኘ ፍካት ልጅነት፤
በመጸው ልብ በፅጌ ወር፤
የዐደይ እንቁ መሸመት።

ቢጫ ዕንቁ፣
የማር ሰፈፍ፣
ህቱም ጸጋ፤

የአበባ ልብ፣
ምዑዝ ጠረን፣
ነይ በዝናም፤
ነይ ክረምቱን፤
ስለ ወቅትሽ፤
ስለ ወቅቴ ፤
በሙላህ ሆነን
እናውጋ።

ነይ ሐምሌን ክረሚ፤
ነይ ጳጉሜን ታገሺ፤
የመጠበቅ ልክ፤
የመክረምን አቅም፤
ከዘመን ተዋሺ።

የወንዙን ሙላት ዕይ፤
ማለፊያ ፍለጋ የከፋፈተውን
የአፈር ገላ ለይ።

ቅመሺው አየሩን፤
ቀዝቃዛውን ንፋስ፤
ቀላል እንዳይመስልሽ፤
ይሔንን ቁር አልፎ
መስከረም ዜማሽን
ካንቺ ጋ መደነስ።

( ወቅትሽ ላይ መነስነስ....!)
ኹለን ወር አውቃለኹ፤
አንቺ አታውቂም እንጂ፤
ነይ እስኪ ነሐሴ
የደረሰ ተስፋ
የጨለመን ሌሊት፤
ከትዝታ ጋራ
ማሳለፍ ልመጂ።

የአፈር ቀለም ይንካሽ፤
ሰው ሰው
ይሽሽተት ገላሽ፤
ከ ዓመት እስከ ዓመት
እንዳትሰወሪ ...
ግጥም እፅፋለኹ
ቃሌ ነው መታያሽ።

ወንዙን ተከትለሽ
ሂጂ ከባህሩ፤
ያስቀመጥኩት ዕንባ፤
ከዚያ ነው መገኛው
በቀደመ ክብሩ።

ዕንባ ክብር አለው፤
አለው ቅድስና ፤
ይሄንም ቅመሺ
እንደኔ ኹኚና።

ሰው መሆን ቻይበት፤
ታናሽ የመሰለሽ
ይሔ ቤተ አምልኮ፤
መለኮት አለበት።

ማን እንደሆንሽ ዕይ፤
ቃልን ተሸከሚ፤
በእኔ እድሜ ቁመት
ክረምቱን አዝግሚ ።

ነይ ወንጌል ድገሚ፤
ነይ ሃሌ ዘምሪ፤
ቤተ ውበትሽን፤
በጉባኤ ምሪ፤
ነይ ፅጌን ሞሽሪ።

ነይ ከኔ ክረሚ ፤
ነይ ከኔ ክረሚ
ቁሩን አሳልፉሽ
መፀው ላይ አዝግሚ።


[ መንበረ ማርያም ሃይሉ ]


@Samuelalemuu


ከስጋ ጎደልኩ - ነፍሴ በለጠኝ
አቅል ከቀልቤ ከ'ጄ አመለጠኝ
ገና ሳስብህ አቁነጠነጠኝ ።
-
አንዳች ውብ ብርሀን በላዬ አረፈ
ልቤ እንደ ቡራቅ ተወነጨፈ ።
በፍቅርህ ልስከር
ልዙር ልሽከርከር
ሰማዩን ምድሩን ላስስ ልቃኘው
የትም ነውና የምትገኘው !

[ ሃብታሙ ሃደራ ]


@Samuelalemuu


〽️

ትደንሳለች ዛፍ ሥር
ንፉሱ ዳንሷን ያፈጥናል
«መገፋት» እዛ ቦታ ለይ
እንዴት አባቱ ውብሆኗል።
.
እጅ የለው ገሃድ የወጣ
አይታይ በአካል ሲመጣ
ሲነካት እጁን ታውቃለች
ሲደርሳት ትደንሳለች
ደ...ስ..ታ ...እዛ ነው ያለች ።
.
ነፋስ ጋር ጨዋታ ደራ
ዳሌዋ ቀሚሷን ፈራ
ተነሳ ጨርቋ ወደላይ
እሷ ግን አልገደዳትም
አእምሮ ደስታን ባየበት
እብድ ነው...እብድ ነው የትም ።
.
ወገቧን ሰፈረው ነፋስ
ለክቶ ቁጥሯን ገመተ
ከንፈሯን ሳይታይ ስሞ
ሳይገዛ ፍቅር ሸመተ
ደስ ሲል.. መዞሩ ጣማት
(እንደዛ ...እንደዛ መቅረት አማራት ።
.
ስጋዋ ከክር ቀጠነ
ለነፍሷ ትንሽ ወገነ
ሐሳቧ ባንድ ላይ ሾረ
አያውቀው ሳህን አንስቶ
አያውቀው ደስታ ሰፈረ
እፍ አለች ...እፍ እንደ ቅጠል
ዞረችው የመሬትን ገጽ
አርያም ደረሰ ልቧ
ሳትበር ከላይ ቤት መድረስ
ይህ ነበር...ይህ ነበር ግቧ ።
.
እዛው ናት እጇን ዘርግታ
ምድር ላይ በሐሳብ ጠፍታ
ቀሚሷ ቬሎን አስንቆ
ተልቆ
ጭኗ ላይ ያለው ንቅሳት
በጣቱ ሲቀሰቅሳት
ቀጥ አለች ፥ተወችው ዳንሷን
መለስ አረገች ቀሚሷን ።
.
ቁጭ አለች ከዛፉ ግርጌ
አሰበች ስለመዞሯ
ገረማት የነፋስ ልፋት...
(ሲያዞራት እሱም መዞሩ
አሁን ነው የገባት ነገሩ።)

[ ድረስ ጋሹ ]

@Samuelalemuu


እዚህ..
ከራስ ቅሌ ጣሪያ ሥር...
እንደሚፈርስ ትልቅ መንደር ፥ ቡልዶዘር እንደዋለበት፥
ወይ ደሞ:
እንደ ሰፊ ድግስ ቤት ፥ ንጉስ ልጁን የዳረበት፥
እዚህ...
የልቤን ዳስ የሞላውን፥
እስክስታና እዬዬውን፥
ፍርስርሱን ድርምስምሱን፥
ጩኸትና ትርምሱን፥

ለመድሁና፡

ሲንኮሻኮሽ አሸልቤ ፥
ተስማምቼ ከቱማታው ፥ ተላምጄ ከድለቃው፥
ዝም! ሲል ነው የምባትት ፥ ፀጥ! ሲል ነው የምነቃው።

#ሚካኤል_ምናሴ

@Samuelalemuu


ከዚህ ወድያ አልወድሽም
(በእውቀቱ ስዩም)

ከዚህ ወድያ አልወድሽም
የለም እወድሻለው ገና
ማፍቀር አጭር ቢሆንም
መርሳት ረጅም ነውና።

 
@Samuelalemuu


ቃላት እንደ መደርደር፤
ተረክ እንደ መሰደር፤
ቀላል አይምሰልሽ፣
ደህና ውሎ ማደር!
.
ዝም እንደማለት. . .
ከምናብ ብቻ እንደ መዶለት፣
በፈሪ ልብ እንደማፈግፈግ፣
ከሞቀ መዳፍ እንደ መለፈግ፣
መዳከር፣መመንመን፣
መከስመን፣መጠውለግ፣
ቀላል አይምሰልሽ. . .
የነፍስን ቦታ በአንድ ዕድሜ መፈለግ!
.
ይኼን ስልሽ. . .
ብረት አልምሰልሽ፣
የማልዝግ፣የማልሰበር፣
የማልነ'ካ፣የማልቆፈር፣
ሰማይ አልምሰልሽ!
ዐውቃለሁ...እመስላለሁ፣
እወድቃለሁ፣እጎዳለሁ፣
እኔም ይከፋኛል፣
መቼም ሰው አይደለሁ?


[ ፈይሠል_አሚን ]


@Samuelalemuu

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.