╔════════════════╗
ዐብዱላሂ ጋሊብ አብደላህ አል-በርጉሲ
╚════════════════╝
"እርሱ ማስተር ማይንዳችን ነበር" በማለት የፍልስጤም ሙጃሂዶች ያንቆለጳጵሱታል። የእስራኤሉ የስለላ ተቋም "ሞሳድ" "ባለጥላው መሪ!" በማለት ይጠራዋል። እስራኤላውያንን ቁም ስቅል ያሳየ፣ ጭንቅላቱን በሚገባ የተጠቀመ የጦር ሊቅ፣ የሞሳድ ኤጀንቶችን ያደናገረ ጀግና የጦር መሪ እንደነበር ራሳቸው ይመሰክራሉ።
ፅዮናዊቷ እስራኤል የአን ነክባን ጥቃት በሰነዘረችበት ጊዜ ነበር የጂሃድ እንቅስቃሴውን በይፋ የተቀላቀለው። ዳር-ያሲን የምትባል ከኢየሩሣሌም አቅራቢያ የምትገኝ ፀጥተኛ መንደር ላይ ከበባ አድርገው ዕድሜና ፆታ ሳይለዩ ፊት ለፊት ያገኙትን ሁሉ በጥይት ቆሉት፡፡ በስለትና በመጥረቢያ ጨፈጨፉት፡፡ ለማምለጥ የሚሞክረውን መግቢያ መውጫውን ዘግተው በመጠበቅ ደፉት፡፡ 256 ነዋሪዎች ላይ ጭፍጨፋ አድርገው አንድም እንዳልተረፋቸው እርግጠኛ ሲሆኑ ቤት ንብረቱ ላይ የፍየልና የግመል ማደሪያ፣ የጥራጥሬ ማከማቻ ሳይቀር እሣት ለቀቁበት፡፡ ፍልስጤማውያን ይህን ቀን ´አን-ነክባ’ ይሉታል፡፡ በታላቅ ምሬትም ያስታውሱታል፡፡ የኃዘንና የዕልቂት ቀን ማለት ነው፡፡
አብደላህ አልበርጉሲ በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ከደቡብ ኮሪያ በማእረግ ተመርቋል። በጁዶ ካራቴ ከፍተኛ ማዕረግን አጊኝቷል። ተቀጣጣይ ፈንጅዎችን መስራት ለሱ ምግብ እንደማብሰል ቀላል ነው። በኮምፒውተር ሃኪንግ ኤክስፐርት ነው። ከዛሬ ሀያ አመታት በፊት ነበር በጠቅላይ ሚኒስትር ናታንያሁና በእስራኤል ቱባ ባለስልጣናት በተመራ ኦፕሬሽን በመናፍቃን ጥቆማ በቁጥጥር ስር የዋለው።
እጃቸውም እንደገባ በደስታ ፈነደቁ። ውስኪያቸውን እየተራጩ እርስ በርስ እንኳን ደስ አላችሁ ተባባሉ። በመጠጥ ሰክረው በደስታ ስሜት ተናጡ። ጠቅላይ ሚኒስትር ናታንያሁ በዚያው ለሊት ለሚስታቸው በቀጥታ ደውለው እንዲህ በማለት እንደተናገሩ ጋዜጦች ከተቡ
"አስቸጋሪውና የሙጃሂዶቹን ማስተር ማይንድ፣
ባለ ጥላውን መሪ ያዝነው!.. አዎ በትክክል ይዘነዋል! እርሱ መሆኑንም አረጋግጠናል.." በማለት ደስታቸውን እየፈነጠዙ ለሚስታቸው አጋሯት።
67 ጊዜ የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበታል። 5200 ዓመታት በእስር እንዲያሳልፍም ተወስኖበታል። እግርና እጁ ተጠፍሮም ለአመታት ብቻውን ጨለማ ቤት አሳልፏል። ጭካኔ የተሞላበት ስቃይንም አስተናግዷል። ሚያዝያ 2012 ለ28 ቀናት ባካሄደው የእስር ቤት የረሃብ አድማ ሁሉም እስረኞች እንዲፈቱ ምክንያት ሆኗል። በእርግጥም እሱ ስለኢስላምና ሙስሊሞች ሲታገል የኖረው ሕይወቱን ለስቃይ የዳረገው ዐብደላህ አልበርጉሲ ነው።
ከቤተሰቡ ተገሎ በእስር ቤት ስቃይ መማቀቅ ከጀመረ ዘንድሮ ሀያ አመቱን ይዟልል። አላህ ከግፈኞች ነጃ ይበለው።
═════════════════
ይህ የዩቱዩብ አድራሻችን ነው ሰብስክራይብ ያድርጉ
👇👇👇👇
https://youtube.com/channel/UCPgxFIQ_qZ2XHM1di_y_xoA
═════════════════
ለሌሎችም ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን እናስፋ
╔═══════════════╗
http://t.me/sehkaliderashid
http://t.me/sehkaliderashid
╚═══════════════╝