👉 የአሜሪካና ግብረ አበሮቿ የአላህን ቅጣት ለመከላከል መታተር ።
አሜሪካ ክንዷን ለማሳየት በፍሊስጢን ምድር ላይ በጦር ጀቶቿ የምትወረውራቸው የነበሩ ቦንቦች ይፈጥሩት የነበረ አይነት እሳት ዛሬ በአላህ ትእዛዝ በተፈጠረ የቁጣ እሳት እየተናወጠች ነው ። ይህን ለመከላከል ግብረአበሮቿ ያለ የሌለ ሀይላቸውን ቢጠቀሙም የአላህን ቁጣ ሊያስቆሙ አልቻሉም ። ሎስ አንጀለስ ከነያዘችው ነገር እየነደደች ነው ። ይህን የአላህ ቅጣት አላህ የፈለገው ቦታ እስኪደርስና አላህ በቃ እስከሚለው ማንም ማስቆም አይችልም ።
የዚህ መራራ ፅዋ እንድትጋት ያደረጋት ምድርን እኔ ነኝ የማስተዳድረው ያልፈለኩትን አጠፋለሁ ማንም አያስቆመኝ የሚለው ትምክህቷ ነው ። በሷ የግፍ በትር ደካሞች ሲሰቃዩ ፣ ሰሚ የሌለው የይድረሱልኝ ዋይታ ድምፅ ሲያሰሙ ከላይ ሆና እስኪ ማን ነው ስትል እንደነበረው ዛሬ በተራዋ በፍትህ በትር እየተገረፈች ነው ። ይህ ክስተት ለአእምሮ ባልተቤቶች ብዙ ሚስጢር የያዘ አስተማሪ ክስተት ነው ። ማን አለብኝ ባዮች ቆም ብለው ማስተዋል ከቻሉ ብዙ ይማሩበታል ። የፍጥረተ ዐለሙ አስተናባሪ የሀያሎች ሀያል የሆነው አላህ ከያዘ አያያዙ የበረታ ነው ። አዘናግቶ ሊዛቸው ዝም ሲላቸው የሌለ የሚመስላቸው ዐቅለ ቢሶች በተዘናጉበት ዪዛቸዋል ።
በአሜሪካ ላይ የወረደው መቅሰፍት በሷ አይነት እብሪት ከተሞሉት የራቀ አይደለም ። ምላሳቸውንና እጃቸውን ካልሰበሰቡ በዚሁ በትር መገረፋቸው አይቀርም ። አሁን አሜሪካ ላይ ባለው ነገር መደሰት ባይቻልም ፍትሀዊ የሆነው አምላክ የሚገባቸውን እየሰጣቸው መሆኑን ማመን ግድ ይላል ። መደሰት አይቻልም ያልኩት የአላህ ቁጣ ሲመጣ ግፈኞቹን ብቻ ለይቶ ስለማይመታ ነው ።
በምድር ላይ ግፍ ሲሰራ ግፈኞቹን ተዉ ብሎ የሚያስቆም ከሌለ ዱንያ ላይ መቅሰፍቱ ሲመጣ ሁሉንም ያጠፋል ። አላህ አኼራ ላይ የሚለየው ቢሆንም ለዚህ ነው አላህ በሚቀጥለው በተከበረው ቃሉ ለይታ የማትመታዋን ፈተና ተጠንቀቁ የሚለን : –
« وَاتَّقُوا فِتْنَةً لَّا تُصِيبَنَّ الَّذِينَ ظَلَمُوا مِنكُمْ خَاصَّةً وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ »
الأنفال ( 25 )
" ከናንተም ውስጥ እነዚያን የበደሉትን ብቻ ለይታ የማትነካን ፈተና ተጠንቀቁ ፡፡ አላህም ቅጣቱ ብርቱ መኾኑን እወቁ ፡፡"
አሁንም አሜሪካን በተለይ ሉስ አንጀሎስን ወደ አመድነት እየቀየረ ያለው የቁጣ እሳት ለይቶ አይደለም እያጠፋ ያለው ። በመሆኑም የአላህን ሀያልነትና ረቂቅ ስራ አመላካች የሆነውን መቅሰፍት የምናየው በእዝነትና በቀደር አይን ሲሆን በሸሪዓ አይን ካየነው ሀያላን ነን ባዮች ከአላህ የእጃቸውን ማግኘታቸው እሰይ ያሰኘናል ። ለማንኛውም የምእራባዊያን እብሪት ትርፉ ክስረት መሆኑን የሚነግራቸው ቢያገኙ ጥሩ ነበር እንላለን ።
https://t.me/bahruteka