በአማርኛችን፦
አንድ የቀዶ ጥገና ባለሙያ አንድ ድንገተኛ ታማሚ ስለመጣ ከሆስፒታል አስቸኳይ ጥሪ ተደወለለትና መጣ።
ቀዶ ጥገና ክፍል ውስጥ ከመግባቱ በፊት በር ላይ የታማሚው ልጅ አባት ጠበቀውና «ለምን ዘገየህ? ልጄ አደጋ ላይ ነው!፣ ትንሽ እንኳ ርኅራሄ የለህም?» አለና ጮኸበት።
ዶክተሩም ፈገግ አለና በተረጋጋ መንፈስ «ተረጋጋ! ሥራዬን ልሥራበት። ልጅህ በአላህ ጥበቃ ስር መሆኑን እወቅ!» አለና መለሰለት።
እኚህ አባትም «እንደት ልትረጋጋ ቻልክ? አሁን ይህ ያንተ ልጅ ቢሆን ኖሮ እንዲህ ትረጋጋ ነበር? ሌሎችን መምከር ቀላል ነው!» አሉት ለዶክተሩ።
ዶክተሩም ዝም አላቸውና ወደ ቀዶ ጥገና ክፍሉ ገብቶ ለሁለት ሰዓታት የቆዬ ቀዶ ጥገና ካካሄደ በኋላ ሲወጣ «አል-ሐምዱ ሊላህ! ቀዶ ጥገናው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። ልጅህ በጣም ደህና ነው። አሁን ሌላ ቀጠሮ ስላለብኝ ይቅርታ አድርግልኝና ልሄድ ነው ብሎት ምንም ጥያቄ ለማዳመጥ ሳይሞክር ሄደ።
ነርሷ ከቀዶ ጥገና ክፍሉ ስትወጣ «ይሄ ጨካኝ ዶክተር ምን ሆኖ ነው?» ሲል ጠየቋት እኚህ አባት።
እርሷም «ልጁ በመኪና አደጋ ሙቶበታል። አስቸኳይ የስልክ ጥሪውን መልሶ የመጣው ልጅዎ ያለበትን ሁኔታ ስለተረዳ ነው። እናም አሁን የርስዎን ልጅ ካዳነ በኋላ የልጁን ቀብር ለመታደም በአስቸኳይ መሄዱ ነው።» ብላ መለሰችለት!
♠
✔ bከዚህ ምን ትምህርት እንወስዳለን፦
አንተ ትክክል ነህ ማለት ሌሎች ተሳስተዋል ማለት አይደለም።
ህይዎትን ከሌሎችም አንፃር ለመመልከት እንሞክር‼
ልጅህ ሙቶ ሳትቀብር የሌላውን ልጅ ለማከም መምጣት ትልቅ ሞራል ይጠይቃል።
|