Postlar filtri


በሆሳዕና ከተማ ከእናት እጅ ታዳጊውን ነጥቆ ሊበላ የሞከረው  ጅብ በእናትየው ተጋድሎ ልጁ ማትረፍ ተቻለ

👉 ጅቡን የአካባቢው ማህበረሰብ ባደረገው ጥረት ተገድሏል

በሀዲያ  ዞን በሆሳዕና ከተማ በጀሎ ናራሞ ቀበሌ መንደር 16 ነዋሪ  ወይዘሮ  ደንባሌ አሥራት ጥር 11ቀን 2017  ዓ/ም  ከጧት 3 ሰዓት አከባቢ ሽላንሻ  ወንዝ ልብስ ለማጠብ  የ12 ዓመቱን ታዳጊ አሥከትላ ትሄዳለች።

ስራዋንም በመከወን ላይ እያለች አንድ ጅብ ወደ እነሱ  ይመጣል። በአጠገባ ከነበረች  ከሌላ ሴት  ጋር  በመሆን ይህንኑ ህፃን በመሀል አሥገብተዉ ቆመው  ጅቡን በፍርሀትም መመልከት ይጀምራሉ ።

ይህ ጅብ ማለፉ  ይቀርና በሁለቱም ሴቶች  መካከል  ያለውን ህፃን ዘሎ ቀኝ እግሩን ነክሶ በመያዝ ሊውሰድ ይሞክራል  የልጁ ወላጅ  እናትም ቀኝ እጁዋን  በጅብ  አፍ  ውሥጥ በመክተት የጅቡን ጓሮሮውን  በግራ እጇ አንቀ በመያዝ በላዩላይ ትወድቃለች 

በዚህ ሰአት  አብራቸው የነበረችው  ሴትም ከጅብ አፍ ህፃኑን  ነጥቃ በመውጣት ልጁን ታተርፈዋለች ።   በጩኸት የወጡ ስዎች ህፃኑን ሊበላ  የቋመጠውን ጅብ  ብዙም  ሳይሄድም ደርሰው  ተባብረው ገድለውታል።እናት ለልጅ እራሷን አሰልፋ  በመሥጠት የልጁን  ህይወት ለመታደግ መቻሏን ከሀዲያ ዞን  ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

4.8k 0 12 14 123

#ከዱር አውሬ የተላከ ደብዳቤ

በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ካሉ ከሶስቱ መጻሕፍተ መነኮሳት የመጨረሻው አረጋወ መንፈሳዊ ነው፡፡ ይህን መጽሐፍ የጻፈው ታላቁ ገዳማዊ ጻድቅ አባት አረጋዊ መንፈሳዊ ወይም ዮሐንስ ሳባ ነው፡፡ ይህ ታላቅ አባት እየቀደሰ እያለ በተገለጸለት ታላቅ ምስጢረ ምክንያት ነበር ዓለምን ትቶ የመነነው፡፡ እግዚአብሔር በዓለም ሆኜ ይህን ካሳየኝ ከዓለም ብሸሽ የበለጠ ለእርሱ እቀርባለሁ ብሎ፡፡

ገዳማውያን አባቶቻችን እንዲህ ናቸው ወደ ፈጣሪያቸው ለመቅረብ ዓለማዊ ክፋት ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ መገለጥም ምክንያት ይሆናቸዋል፡፡ ገዳማትን ስንደግፍም የእነዚህን አባቶች በረከት ነው የምናገኘው፡፡

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስ፣ ታዲያ አረጋዊ መንፈሳዊ በየጊዜው በዓለም ላለው ለታናሽ ወንድሙ መንፈሳዊ ደብዳቤ ይጽፍለት ነበር፡፡ ዓለምን እንዲተው ስላስወሰነው ምስጢር፣ ስለነበረበት፣ ስላለበት፣ በአጠቃላይም ስለ ገዳማዊ ሕይወት ነበር የሚጽፍለት፡፡

እነዚህን #”ከዱር አውሬ የተላከ ደብዳቤ” በሚል ርዕስ የሚጻፉ ደብዳቤዎች እኔ ሳልሞት ለማንም እንዳታሳይ ብሎ ቢያዘውም ወንድሙ ግን በመጽሐፍ መልክ ለማጻፍ ደብዳቤዎቹን ለጸሐፊ ሊሰጣቸው ሲል አጣቸው፡፡ ከአስራ ስንት ዓመታት በኋላ ግን ደብዳቤዎቹን መጀመሪያ ያስቀመጣቸው ቦታ አገኛቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ወንድሜ ሞቷል ብሎ አለቀሰ፡፡ በረከቱ ይደርብንና ይህን ታላቅ ጸጋ የታደለው አባት ነው እንግዲህ ራሱን በትሕትና የዱር አውሬ ብሎ የሚጠራው፡፡

ገዳማውያን አባቶች መሻታቸው አንድ ብቻ ነው፤ ወደ እግዚአብሔር መቅረብና ለሀገርና ለሕዝብ መጸለይ፡፡ ታዲያ ገዳማቸውን እናጽና፣ ድጋፍ እናድርግ ስንል በሌላ አባባል በረከት እንፈስ እያልን ነው፡፡



ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish


ተይዘዋል ‼️

በትላንትናው እለተ በኦሮቶዶክስ እምነት የቅዱስ ሚካኤል ታቦት ላይ ሲያሾፉ የነበሩት እነዚህ የአምቦ ተማሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል::

@sheger_press
@sheger_press


ደብረብርሃን አሳዛኝ የመኪና አደጋ‼️

ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ብርሃን ሲጓዝ የነበረ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ጠባሴ አካባቢ ሲደርስ መንገድ ስቶ በመውጣቱ የሦስት እግረኞችን ሕይዎት ቀጠፈ፡፡

ዛሬ ጠዋት 1 ሠዓት ከ30 ላይ በደረሰው የትራፊክ አደጋ÷ ልጆቿን ወደ ትምህርት ቤት ስትሸኝ የነበረች እናትን ጨምሮ የሦስት ሰዎች ሕይዎት ማለፉን የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

ከሟቾች በተጨማሪም በአደጋው የ1 ዓመት ከ7 ወር ሕጻንን ጨምሮ በ9 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን የመምሪያው የትራፊክ መረጃ ክፍል ኃላፊ ኮማንደር ኪዳኔ በቀለ አስታውቀዋል፡፡

የአደጋው መንስኤ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

አደጋውን ያደረሰው አሽከርካሪ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
#FBC

@sheger_press
@sheger_press


«የሒጃብ ጉዳይ ፍጹም አጀንዳ መሆን የማይገባው ሆን ተብሎ አጀንዳ እንዲሆን ተደርጓል። በፍጥነት እልባት እንዲሰጠው እናደርጋለን»

የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ፕረዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከሰልፉ በኃላ ተወክለው ለሄዱ 20 የሙስሊሙ ተወካዮች በጽ/ቤታቸው የሰጧቸው ምላሽ::

@sheger_press
@sheger_press


በመቐለ ከተማ በአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን በደል አስመልክቶ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል!

ፍርድቤት የትምህርተ ቤቱ በሂጃብ የተሸፈኑ ሴት ተማሪዎችን አላስተናግድም ማለቱነ በማገድ ለፈተና እንዲመዘገቡ ቢያዝም ትዕዛዙን በመተላለፍ እስካሁነ ተማሪዎቹ አልተመዘገቡም።

@sheger_press
@sheger_press


ትራምፕ ማምሻውን በኦቫሉ ቢሯቸው ለጋዜጠኞች "በብሪክስ አባል ሃገራት ላይ 100% ታሪፍ እንደሚጥሉ" ተናግረዋል::

ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ስትሆን የተለያዩ ምርቶችን ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንደምትልክ ይታወቃል::

@sheger_press
@sheger_press


በኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የቢሾፍቱ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ዙሪያ ተነሺ አርሶ አደሮች ተቃውሞ እያሰሙ መኾኑን አፍሪካን ኢንተለጀንስ ድረገጽ ዘግቧል።

አርሶ አደሮቹ ቅሬታ ያሰሙት፣ ከካሳ እና ከሠፈራ ዕቅድ ጋር በተያያዘ እንደሆነ ዘገባው ጠቅሷል።

መንግሥት ለማስፋፊያው የቀጠረው የሊባኖሱ አማካሪ ኩባንያ፣ አርሶ አደሮች ይነሱባቸዋል ወደተባሉት ቦታዎች ቅድመ-ጥናት የሚያካሄድ የባለሙያዎች ቡድን መላኩንም ዘገባው አመልክቷል።

አኹን ከሚኖሩበት ቀያቸው 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንዲሠፍሩ ይደረጋሉ የተባሉት አርሶ አደሮች እስከ 2 ሺሕ 500 ይደርሳሉ ተብሏል።

ተነሺዎቹ አርሶ አደሮች፣ በአንድ ስኩዌር ሜትር 322 ነጥብ 5 ብር ካሳ እንዲከፈላቸው እንደታሰነ ከአርሶ አደሮቹና ከአንድ ደብዳቤ ላይ መመልከቱንም የዜና ምንጩ አውስቷል።

@sheger_press
@sheger_press


በአማራ ክልል ያለው የመምህራን ደመወዝ አለመከፈል መምህራንን የጉልበት ሥራ እንዲሰሩ ማስገደዱ ተገለጸ

በአማራ ክልል ከመስከረም እስከ ታሕሳስ ወር ደመወዝ ያልተከፈላቸው መምህራን፤ ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተዳምሮ የጉልበት ሥራ ለመስራት ተገደዋል ሲል የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አስታወቀ፡፡

በክልሉ ያሉ መምህራን ለተማሪዎቻቸው ሲሉ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ተቋቁመው እየሰሩ ነበር ያለው ማህበሩ፤ "አሁን ላይ ግን ያለው ሁኔታ ካቅማቸው በላይ እየሆነ ነው" ብሏል፡፡

"ለወራት ደመወዝ ያልተከፈሉ መምህራን ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለስ ባለመቻላቸው የጉልበት ሥራ የሚሰሩ አሉ" ያሉት፤ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አበበ ናቸው፡፡

"በዚህም ቀጣዩ የመምህራኑ እጣ ፋንታ ምን እንደሆነ አይታወቅም" ያሉት የማህበሩ ምክትል ፕሬዝደንት የትምህርት ሥራውንም ወደ ኋላ ጎትቶታል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ትምህርት ባልተጀመረባቸው አካባቢዎች ያሉ ተማሪዎች ትምህርት ወደሚሰጥባቸው ቦታዎች ሄደው ለመማር ሲሞክሩ በተፈጠረ የቦታ ጥበት፤ በአንድ ክፍል ውስጥ 90 የሚሆኑ ተማሪዎች እንዲቀመጡ አስገድዷል ነው የተባለው፡፡

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ያሉ መምህራንን የተመለከቱ ችግሮች በሁሉም አካባቢ አይነት እና መጠናቸውን እየቀያየሩ መቀጠላቸውም ነው የተገለጸው፡፡

@sheger_press
@sheger_press


"በህወሓት አመራሮች መካከል እየተካረረ የመጣው ልዩነት በክልሉ እየታየ ያለውን የሰላም ጭላንጭል የሚያጨልም ነው” - አቡነ ማትያስ

በህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል እየተካረረ የመጣው ልዩነት በክልሉ የተገኘችውን የሰላም ጭላጭል የሚያጨልም ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሊቀጻጻስ የሆኑት አቡነ ማትያስ ለህወሓት ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) እና ለግዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በተናጠል በጻፉት ደብዳቤ ገለጹ።

“ሁኔታዎች ከግዜ ወደ ግዜ እየከፋ፤ የተገኘችውን የሰላም ጭላጭል ሊያጠፋ ወደሚችል ሁኔታ እያመራ ይገኛል፤ ይህንን እያየን ዝምታን መምረጥ በሰውና በፈጣሪ የሚያስጠይቅ በመሆኑ ይህንን የምክር ደብዳቤ ለመጻፍ ተገድጃለሁ” ብለዋል።ፓትርያርኩ በደብዳቤያቸው ሁለቱን አመራሮች በአካል አግኝተው ለመወያየት ያደረጉት ጥረት እንዳልተሳካላቸው በመጠቆም ደብዳቤውን ለመጻፈ መገደዳቸውን አስታውቀዋል።

“በእልክ እኔ እሻላለሁ፣ እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን፣ እኔ ብቻ ነኝ ለህዝብ የማስበው በሚል በተፈጠረው ውስብስብ ችግር የሚያዝን እንጂ የሚደሰት ህዝብ የለም” ሲሉ ጠቁመዋል።“በአመራሩ መካከል የተፈጠረው መለያየት እንዳይበቃ በአንድነት ተስማምቶ ሲኖር በነበረው ህዝብ መካከልም ተጽእኖው እየወረደ ይገኛል” ሲሉ ስጋታቸውን አስቀምጠዋል።

@sheger_press
@sheger_press


" ተመልሶ መጥቷል"

ታይም መፅሄት ትራምፕን በአዲሱ እትም ሽፋን ላይ አስቀምጦ በኋይት ሀውስ ውስጥ ሰነዶችን ጠራርገው ሲያፀዱ ያሳያል

@sheger_press
@sheger_press


🙏 ቃና ዘገሊላ 🙏

#የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ

ወርሀ ጥር የሙሽርነት፣ ጎጆ የመውጫ ዘመን ነው፡፡ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ዘመነ መርዓዊ በመባል ከሚጠሩ ወቅቶች አንዱ ነው፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በገሊላ ቃና ሰርግ የታደመበት በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 2 የሚገኘው ታሪክ በዚህ ቀን ይነገራል፡፡ በርካቶች የሚስቱበት በርካቶችም ለሕይወት የሚያደርጉት ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት የታየበት፣ ንፁህ ውሃ ወደ ግሩም ወይን ጠጅ የተለወጠበት፣ ጌታችንም የመጀመሪያውን ተዓምራት ያሳየበት ነው፡፡ ከቅዱሳን ሐዋርያትና ከእናቱ ጋር በገሊላ ቃና ሰርግ የታደመው ኢየሱስ ክርስቶስ የወይን ጠጅ እንዳለቀ የተነገረው ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ነበር፡፡

“እርሱም አንቺ ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት፡፡ እናቱም ለአገልጋዮቹ። የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው። አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፥ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር። ኢየሱስም ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሞሉአቸው። አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት አላቸው፤ ሰጡትም። አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደ መጣ አላወቀም፤ ውኃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪው ሙሽራውን ጠርቶ" ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፥ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል አለው። ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።”

ይህ “ከቁጥር 4–11” የሰፈረ ቃል የቅድስት ድንግል ማርያምን ምልጃ፣ በጎደለው ሁሉ የምታስጨምር እደሆነች ያሳያል፡፡ የዘመናችን ስሁታን “አንቺ ሴት ካንቺ ጋር ምን አለኝ?” ስላላት ክብር ይግባትና በውርደት ቃል እንደጠራት ይገልጻሉ፡፡ ይህ ግን በእስራኤላውያን ልማድ የሆነ አነጋገር ነው፡፡ “ጥያቄሽን እንዳልፈጽም የሚያደርግ ካንቺ ጋር ምን ጸብ አለኝ?” የሚል ትርጓሜም ይይዛል፡፡ ይህን ካላት በኋላ መግባባታቸውን የሚያሳየን ደግሞ “እናቱም ለአገልጋዮቹ። የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው።” የሚለው ቃል ነው፡፡ የሰጣት ምላሽ በጎ ባይሆን ይህን ትዕዛዝ ለአገልጋዮቹ አታስተላልፍም ነበር፡፡ ከሠላሳ ዘመን በላይ አብራው የኞረችው እናቱ ናትና ንግግሩ የሚገባት ሀሳቧን የሚቀበል ነው፡፡ በዚያውስ ላይ እናትና አባትሕን አክብር ብሎ ትዕዛዝ የሰጠ አምላክ እንዴት እናቱን ዝቅ አድርጎ ተናገራት ልንል እንችላለን?

“ድንቅ ወይን ጠጅ ከንጹህ ውሃ ተገኘ፣ የሰርግ ቤቱም በደስታ ተሞላ፣ ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።” ስንል የሕይወታችንን ውሃ ንጽሕና እየጠየቅን ሊሆን ይገባል፡፡ በአባቶች ጸሎት በገዳማውያኑ ምልጃ ወደ መልካሙ ወይን ለመለወጥ በበጎ ምግባር እንሳተፍ፣ የሚለንን ሁሉ እናድርግ፡፡    
 
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444




የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ እንዲደረግ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጥሪ መቅረቡን የእንግሊዝኛ ጋዜጣ Capital ዘገበ ።

የውጪ ምንዛሪ ለውጡን ተከትሎ ከግምት ውስጥ ያስገባ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ እንዲደረግ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጥሪ ቀረበ ።

መንግስት ለረጅም ጊዜ ሲጠብቅ የነበረውን የኤሌክትሪክ ታሪፍ ጭማሪ ተግባራዊ ቢያደርግም ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋማት ግን ተጨማሪ ክለሳዎች እንዲደረጉ እየጠየቁ መሆኑን ካፒታል ተረድታለች።

የሚኒስትሮች ም/ቤት ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ባካሄደው 36ኛው መደበኛ ስብሰባ ላይ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ጭማሪን ያፀደቀ ሲሆን ይህም ጭማሪ ከመስከረም 1/2017 ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን መወሰኑ ይታወቃል።

አገልግሎቱ በአዲሱ የታሪፍ ማሻሻያዉ እስከ 200 ሜጋዋትስ ሰዓት የሚጠቀሙ ደንበኞችን ድጎማ እንደሚያደርግ ገልጿል ። ማሻሻያው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙትን ደንበኞች ታሳቢ አድርጓል ቢባልም የተደረገው ጭማሪ በዓመት ውስጥ 122 በመቶ ደርሷል።

ይሁን እንጂ ከማክሮ ኢኮኖሚ ለውጡ ጋር በተገናኘ እንደ ዓለም ባንክና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋምን (አይ.ኤም.ኤፍ) የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ አጋሮች የተለያዩ ድጋፍ ከማድረጋቸው ጋር ተያይዞ መንግስት ያፀደቀውን የታሪፍ ጭማሪ በድጋሚ እንዲያጤነው መጠየቃቸውን ነው ለማወቅ የተቻለው። (Capital news)

@sheger_press
@sheger_press


#ቴምር ሪልስቴት
😱7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ ለሽያጭ ያወጣናቸው 3 ሳይቶች
🎯1,አያት ሳይታችን
        👉 2መኝታ 87ካሬ
        ሙሉ ክፍያ 4,976,400ብር
         👉 3መኝታ 107ካሬ
        ሙሉ ክፍያ 6.1ሚሊዮንብር
         👉 3 መኝታ 121ካሬ
        ሙሉ ክፍያ 6.9ሚሊዮን ብር
🎯2,ተክለሃይማኖት ሆስፒታል ፊት ለፊት
         👉3 መኝታ 113ካሬ
         10%ቅድመ ክፍያ 1ሚሊዮን ብር
          ሙሉ ክፍያ 10,961,000ብር
         👉3መኝታ 119ካሬ
        10%ቅድመ ክፍያ 1.1ሚሊዮን ብር
        ሙሉ ክፍያ 11,543,000ብር
         👉ቀሪውን 90% በ15 ዙር ከፍለው የሚጨርሱት
🎯3,ፒያሳ (ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት) ጀርባ
         👉1 መኝታ 66ካሬ=
         10% ቅድመ ክፍያ 693,000ብር
         ሙሉ ክፍያ 6,930,000 ብር
         👉2መኝታ 71ካሬ
        10%ቅድመ ክፍያ 745,000ብር
        ሙሉ ክፍያ 7,455,000ብር
         👉2መኝታ 93ካሬ=
       10% ቅድመ ክፍያ 1,044,000ብር
       ሙሉ ክፍያ 10,044,000ብር
        👉3መኝታ 130ካሬ
      10%ቅድመ ክፍያ 1,365,000ብር
      ሙሉ ክፍያ 13,650,000ብር
        👉ቀሪውን 90% በ17ዙር ከፍለው         የሚጨርሱት
        👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273


Tik Tok‼️

ለግማሽ ቀን በአሜሪካ ተቋርጦ የቆየው Tiktok በድጋሚ መስራት ጀምሯል

@sheger_press
@sheger_press


እስራኤል ዞልፋካር በተሰኘ ተምዛግዛጊ ሚሳኤል ተመታች

በኢራን የሚደገፈው የየመኑ ሃውቲ ታጣቂ ቡድን የሚያደርስባት ዙሪያ መለስ ጥቃት ያንገሸገሻት ኢስራኤል፣ አሁን ይባስ ብሎ የየመን መንገስት ጥቃት ስለባ ሆናለች እየተባለ ነው፡፡

በዚህም የየመን መንግስት ጦር በቴል አቪቭ ከባድ የባላስቲክ ሚሳኤል ጥቃት መፈጸሙ እየሩሳለምን ክው አድርጓታል፡፡

የየመን ጦር ሃይል ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጄኔራል ያህያ ሳሬ እንደተናገሩት፣ የየመን ጦር የእስራኤል መንግስት መከላከያ ሚኒስቴር ግቢን፣ ዞልፋካር በተሰኘ ተምዛግዛጊ ሚሳኤል መምታቱን እስታውቀዋል፡፡

የየመን ጦር ሃይል ቃል አቀባይ ባወጣው መግለጫ እንዳመላከቱት፣ “በቴላቪቭ የሚገኘውን የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር፣ በሚሳኤል ጥቃት ኢላማ አድርገናል” ብለዋል።

ኦፕሬሽኑ የተካሄደው 'ዞልፋካር' በተሰኘ ባላስቲክ ሚሳኤል ሲሆን፣ ጥቃቱ በጥንቃቄ የተፈጸመ እና ግቡን የመታ ትክክለኛ ድብደባ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡

የጠላት መከላከያ ስርአቶች ሊመከቱት ያልቻሉትን፣ ከባድ ጥቃት ፈጽመናል ሲሉ ቃል አቀባዩ ፎክረዋል።

@sheger_press
@sheger_press


#ከ5530 ዘመን በኋላ የተደመሰሰው የዕዳ ደብዳቤ

ዮርዳኖስ ቃሉ ያርዴን ከሚለዉ የእብራይስጥ ቃል የተወሰደ ሲሆን ትርጓሜውም “ወራዲ፣ የሚወርድ፣ ወራጅ ወንዝ” ማለት ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን 175 እንዲሁም በሐዲስ ኪዳን 15 ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ስሙ የተጠቀሰ ቅዱስ ስፍራ ነዉ፡፡ ዮርዳኖስ ወንዝ ከሶርያ ምድር፣ ከሄርሞን ወይም በግእዙ አርሞንኤም፣ በአማርኛዉ ጎላን ከሚባለው (እስራኤል በኃይል የተቆጣጠረችው ንብረትነቱ ግን የሶሪያ የሆነ) ተራራ ሰሜናዊ ክፍል ተነስቶ ወደ ደቡብ የሚፈስ ነው፡፡ ሶርያን፣ ጆርዳን ወይም ዮርዳኖስ የምትባለውን ሀገር፣ የፍልስጤም አስተዳደርና እስራኤልን በማዋሰን በአማካይ ከ314 እስከ 320 ኪ.ሜ ተጉዞ ሙት ባህርን የሚቀላቀል የእስራኤል ትልቁ ወንዝ ነው፡፡

ይህ ወንዝ አዳኝና ፈዋሽም ነዉ የሶርያዉ ሰዉ ንዕማን በለምጽ ሲሰቃይ ነቢዩ ቅዱስ ኤልሳዕ እንዲፈውሰው ወደ እስራኤል መጣ፡፡ ነቢዩም በዮርዳኖስ ወንዝ ሦስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ እንዲል ነግሮት፣ መጀመሪያ ቢያንገራግርም ኋላ ግን ይህን ሲፈጽም ከለምጹ ድኗል፡፡ ጻድቁ ኢዮብ በደዌ ሥጋ ሲሰቃይ በዚሁ ወንዝ ታጥቦ ነበረ ቁስሉ የነጻው፡፡ ነቢዩ ቅዱስ ኤሊያስም በእሳት ሰረገላና ወደ ሰማይ ሲነጠቅ ደቀ መዝሙሩ ነቢዩ ኤልሳዕ በሁለት አጥፍ የኤልያስን መንፈስ የተቀበለው በዮርዳኖስ ወንዝ ነዉ /2ኛ ነገ 2፡1-15/፡፡ ከመነሻው በአንድ ምንጭ የሚፈልቀው ዮርዳኖስ በሁለት ተከፍሎ “ዮር” እና “ዳኖስ” ሆኖ ሲፈስ ይቆይና ከታች መልሶ ይገናኛል፡፡ ዮርዳኖስ የሚለው ስሙም መነሻው ይህ ነው፡፡

በዘመነ ብሉይ በነቢዩ ኢሳይያስ መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንሰሓ ግቡ ብሎ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ እንደሚመጣ የተነገረለት መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ እንዲሁም በዮርዳኖስ ዙርያ ያሉ ሕዝቦችን “መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሃ ግቡ” እያለ ኃጢያታቸዉን እየተናዘዙ የንሰሃ ጥምቀት ያጠምቅበት የነበረው የዮርዳኖስ ወንዝ ከኢያሪኮ በስተምሰራቅ በኩል ይገኛል፡፡ ማቴ 3፡1-6 ሁለቱም በሚገናኙበት ስፍራ የትህትና ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰማይ ምድር ፈጣሪ ሲሆን በሰዉ እጅ ራሱን ዝቅ አድርጎ የጽድቅ ሥራ መሥራት ይገባ ዘንድ ሊያስተምረን ተጠመቀ፡፡ ጌታችን ለምን በዮርዳኖስ ተጠመቀ?

ዲያብሎስ በአዳምና በሔዋን ላይ ከገነት ከወጡ በኋላ መከራ አጸናባቸውና እንዲያቀልላቸው አዳም የዲያብሎስ ባሪያ፣ ሔዋን የዲያብሎስ ገረድ ብለው ጽፈው እንዲሰጡት ነገራቸው፡፡ እነዚህን የእዳ ደብዳቤዎች አንዱን በሲኦል ሌላኘውን ደግሞ በዮርዳኖስ ወንዝ ቀብሮት ነበርና የዮርዳኖሱን በዩሐንሰ እጅ ሲጠመቅ እንደ ሰወቅነቱ ተረግጦ እንደ አምላክነቱ አቅልጦ አጥፍቶላቸዋል፡፡ ማቴ 3፡15—17 ቅዱስ ኤፍሬምም በሰኞ ውዳሴ ማርያም “የአዳምና የሄዋን የእዳ ደብዳቤያቸዉን ቀደደ ደመሰሰ” ይላል፡፡ ሌላው በዮርዳኖስ የተጠመቀነት ምክንያት ደግሞ በቅዱስ ዳዊት “ባህር አየችህ ሸሸችም፣ ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ” ተብሎ የተነገረው ትንቢት እንዲፈጸም ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ራሳቸውን የለዩ፣ እንደ ዮሐንስ ያሉ ገዳማውያንን በመርዳት በዓታቸውንም በማጽናት ከበረከታቸው እንካፈል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444



20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.