Simon Dereje( DAGU JORNAL)


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Siyosat


"Welcome to EthioPulse NewsHub – your premier source for the latest Ethiopian news updates! Stay informed with timely reports covering politics, economy, culture, and more. Join us for reliable news straight to your Telegram feed. Subscribe now!"

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Siyosat
Statistika
Postlar filtri


#Update🚨

“ በሠራተኛዋ እጅ ላይ የተገኘውን ነው እንጂ ያጋራነው ከየት ነው ? የሚል ዝርዝር መረጃ የለውም ፤ እርሱ የሚቀጥል ይሆናል ”  - የአዲስ አበባ ፓሊስ

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፤ ወረዳ 2 አያት ዞን 1 አካባቢ ተቀጥራ ትሰራበት ከነበረው ቤት 18 ሺሕ የአሜሪካን ዶላርና የህንድ ሩፒን ጨምሮ የተለያዩ የወርቅ ጌጣጌጦች በአጠቃላይ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት በመስረቅ የተጠረጠችን የቤት ሠራተኛ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፓሊስ ከሰዓታት በፊት መረጃ አጋርቶ ነበር።

ፓሊስ ማህበረሰቡ የቤት ሠራተኛ ሲቀጥር ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ መሆን እንዳበት ያሳሰበ ሲሆን፣ መረጃው ከተጋራ በኋላ " ይህን ያህል ዶላር በአንድ ቤት እንዴት ተነኘ ? ይህስ ሌላ ምርመራ አያስፈልገውም ? የሠራተኛዋን መታወቂያ የሰጣት አካልስ ማነው ? " የሚሉ በርካታ ጥያቄዎች ሲንሸራሸሩ ተስተውለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ፣ የዶላሩን ምንጭና ማንነትን በደንብ አያሳይም የተባለውን የቤት ሠራተኛዋን መታወቂያ በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጡ የአዲስ አበባ ከተማ ፓሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰን ጠይቋል።

ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ምን ምላሽ ሰጡ ?

ጥሩ ነው እንደዚህ አይነት መነጋገሪያ መሆኑ ሰው በደንብ እንዲያነበውና ጥንቃቄ እንዲያደርግም ይጋብዛል። ዞሮ ዞሮ አሁን ጥሬ ምርመራ ላይ ያለን ጉዳይ መረጃ ነው ለህብረተሰቡ ያጋራነው።

በጣም በርካታው የከተማው ነዋሪ ሠራተኛ ስለሆነ ሥራውን የሚያቀለው አብዛኛው በሠራተኛ ነው፤ ብዙው ሰው ተሯሯጭ ስለሆነ። ስለዚህ ዞር ብሎ ሠራተኞቻቸውን የሚያዩ፣ ያስያዙትን መታወቂያ ቼክ የሚያደርጉ፣ ፎርጅድ ከሆነም ለምን? ብለው የሚያስይዙ አናሳ ናቸው።






#ኮንታ

ዛሬ በኮንታ በደረሰ የመሬት መሸራተት አደጋ 6 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ ጫሬ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በቀበሌው ትናንት ምሽት የጣለው ከባድ ዝናብ ተከትሎ ዛሬ ጠዋት 2 ሠዓት ላይ የመሬት መንሸራተት መከሰቱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

በአደጋው ህይወታቸውን ያጡት ሰዎች የሁለት ቤተሰብ አባላት ሲሆን ከአንደኛው ቤተሰብ አራት እንዲሁም ከሌላኛው ቤተሰብ ሁለት ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።


#ቅዱስሲኖዶስ

" በጦርነትና በግጭት የመጣ ሰላም፣ የተገነባ ሀገር የለም !! ... ችግሩ በእርቅ እንዲፈታ ለሁሉም ወገኖቻችን የሰላም ጥሪ እናቀርባለን " - ቅዱስ ሲኖዶስ

የጥቅምት 2017 ዓ/ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ተጠናቋል።

ምልዓተ ጉባኤው ከጥቅምት 11 እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ መደበኛ ስብሰባውን ሲካሄድ ሰንብቷል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈሳዊ፣ በማኅበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉ ተገልጿል።

የስብሰባውን መጠናቀቅ ተከትሎ በቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ተሰጥቷል።

ከመግለጫው የተወሰደ ፦

" በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች እየተከሰተ ባለው የሰላም እጦት፣ የእርስ በርስ ግጭት ምክንያት የሰው ሕይወት እየተቀጠፈ፣ አካል እየጎደለ፣ ማኅበራዊ ትሥሥር እየተናደ፣ ሰብአዊ ክብር እየተጎዳ፣ መብት እየተጣሰ፣ በዜጎች ላይ ሥጋትና አለመረጋጋት እየበዛ ሀብትና ንብረት እየወደመ ስለሆነ ጉዳዩ አስቸኳይ መፍትሔ የሚያስፈልገው መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ 

ስለሆነም በጦርነትና በግጭት የመጣ ሰላም፣ የተገነባ ሀገር የለምና በሀገራችን እያጋጠመ ያለውን ችግር ለመፍታት ካለፈው በመማር በጥበብ፣ በማስተዋልና በሰለጠነ አካሄድ በሰላማዊ መንገድ በመወያየት ችግሩ በእርቅ እንዲፈታ ለሁሉም ወገኖቻችን ቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ጥሪውን በአጽንኦት ያቀርባል፡፡ "


(ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት)


በአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የዋጋ ጭማሪ የተደረገባቸው አገልግሎቶች ምን ምን ናቸው ?

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ የአገልግሎት ክፍያ ታሪፍ ጭማሪ አድርጓል።

ተቋሙ በአንዳንድ አገልግሎቶች ላይ ያደረገው የዋጋ ጭማሪ ከፍ ያለ ነው።

ለአብነት ፦

° የተሽከርካሪ የዋጋ ግምት ማሳወቅ አገልግሎት 500 ብር የነበረው 1,000 ብር ገብቷል።

° የተሽከርካሪ የዋጋ ግምት ለሽያጭ አገልግሎት 2,310 ብር የነበረው 4,000 ብር ገብቷል።

° የተሽከርካሪ የባለቤትነት ስም ዝውውር አገልግሎት 3,000 ብር የነበረው 5,000 ብር ገብቷል።

° ለዓመታዊ ምርመራ ተለጣፊ ምልክት (ቦሎ) ግልባጭ ለመጀመሪያ ጊዜ 1,010 ብር የነበረው 2,500 ብር ተደርጓል።

° የተሽከርካሪ ባለቤት ማረጋገጫ ሊብሬ 300 ብር የነበረው 1200 ብር ተደርጓል።

° ሊብሬ ሲበላሽ ወይም ሲጠፋ ምትክ ፣ የማደሻ ቦታው ሲያልቅ መስጠት 3,000 ብር የነበረው 3,500 ብር ሆኗል።

° መረጃ መስጠት 300 ብር የነበረው 700 ብር ተደርጓል።

° አዲስ መንጃ ፍቃድ መስጠት 680 ብር የነበረው 1500 ብር ተደርጓል።

° ለጠፋ መንጃ ፍቃድ ማፈላለጊያ ለፖሊስ ወይም ለፕሬስ የሚሰጥ መረጃ 100 ብር የነበረው 700 ብር ተደርጓል።

° ከ3 ጊዜ በላይ የፅሁፍ ፈተና ለወደቁ በየወሩ ለመፈተን የሚሰጥ አገልግሎት 100 ብር የነበረው 300 ተደርጓል።

° ከ3 ጊዜ በላይ የተግባር ፈተና ለወደቁ በየወሩ ለመፈተን የሚሰጥ አገልግሎት ከ300 ብር ወደ 600 ብር ጨምሯል።

° የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ እድሳት ከ620 ብር ወደ 1000 ብር ገብቷል።


#እንድታውቁት🚨

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን " አርቲሜተር " የተባለውን በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድኃኒት ጥቅም ላይ እንዳይውል አግዷል፡፡

መ/ቤቱ ተደርጓል ባለው የገበያ ቅኝት መድኃኒቱ መገኘቱን ፣ በባለስልጣኑ ያልተመዘገበ እንዲሁም ናሙናው ተወስዶ በላብራቶሪ ሲፈተሽ አርቲሜተር (Artemether) የተባለው ንጥረ ነገር በውስጡ አለመገኘቱ መረጋገጡን ገልጿል፡፡

በዚህም ይህን መድኃኒት የጤና ባለሙያዎች እንዳይጠቀሙት እና በየደረጃው ያሉ የክልል ተቆጣጣሪዎች በየአካባቢያቸው ጥብቅ ክትትል በማድረግ እርምጃዎች እንዲወስዱ ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡

መድኃኒቱ ' ሻይንፋርም ' በተባለ የቻይና የመድሃኒት አምራች የተመረተ ሲሆን፤ አርቲሜተር (Artemether 80mg/1ml) የሚል ስያሜ ያለው እና በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድኃኒት ነው።

(የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን)


#IMF #Ethiopia

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ሠራተኞች ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር የተራዘመ የብድር አቅርቦትን በተመለከተ የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገለጸ።

አይኤምኤፍ ባወጣው መግለጫ፣ ድርጅቱ በአራት ዓመታት የሚያቀርበው የ3.4 ቢሊዮን ዶላር የተራዘመ የብድር አቅርቦትን (Extended Credit Facility) በተመለከተ የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት ላይ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ተደርሷል።

ስምምነቱ በይፋ በዓለም አቀፉ ገንዘብ ተቋም ዋና የአመራር ቦርድ ከታየ በኋላ ኢትዮጵያ ወደ 345 ሚሊዮን ዶላር ገደማ እንደምታገኝ ተገልጿል።

" በገበያ ሥርዓት ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ተመንን ጨምሮ ኢትዮጵያ አገር በቀል የምጣኔ ሃብት ፖሊሲ ማሻሻያ ማድረጓ በጥሩ ሁኔታ ውጤት እያሳየ ነው " ብሏል ተቋሙ በመግለጫው።

በገበያ ሥርዓት ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ተመን መተግበሩ በትይዩና በይፋዊ ገበያ መካከል ያለውን ልዩነት በስፋት እያጠበበ እንደሆነ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ያለፈው ዓመት ሐምሌ ላይ በገበያ ሥርዓት ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ተመንን ለመተግበር ውሳኔ አሳልፎ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩ ይታወሳል።

ኢትዮጵያ የመጣው በአልቬሮ ፒሪስ የተመራው የልዑካን ቡድን ሲሆን ከተደረሰው የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በኃላ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አልቬሮ ፒሪስ ምን አሉ ?

➡ የአይኤምኤፍ ሠራተኞችና የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣኖች ስምምነት በተቋሙ ዋና የአመራር ቦርድ በቀጣይ ሳምንታት የሚታይ ይሆናል።

➡ ቦርዱ ከተመለከተው በኋላ ኢትዮጵያ በመጀመሪያ 345 ሚሊዮን ዶላር ታገኛለች።


#ኢትዮጵያ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፦

" ባለፉት ዓመታት ሲፈታተኑን የቆዩ ዙሪያ መለስ ችግሮች መስቀሉ ባስተማረን ሰላማዊ መንገድ እልባት እንዲያገኝና ህዝባችን ያለምንም ስጋት ወጥቶ እንዲገባ ፣ ሰርቶ እንዲያተርፍ ፣ ተምሮ እንዲያውቅ ፣ ሃይማኖቱን በነጻነት እንዲከተል መንግሥትና ኢትዮጵያውያን ሁሉ ለዘላቂ ሰላምና አንድነት አበክረው እንዲሰሩ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። "

9 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.