📌
የህዳር 11 ረፋድ አበይት የዓለም ዜናዎች፡-🔸 የጀርመን ዜግነት ያለው የሀምበርግ ነዋሪ ኒኮላይ ጋይዱክ፤ ከፖላንድ ወደ ሩሲያ ካሊኒንግራድ ክልል ዘልቆ እንደገባ በቁጥጥር ስር መዋሉን የሩሲያ ፌዴራል ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ። ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋለው በክልሉ ውስጥ የኃይል መሰረተልማቶችን ለማውደም በማቀዱ መሆኑ ተገልጿል። የሩሲያ ፌዴራል ደህንነት አገልግሎት እንደገለጸው ግማሽ ሊትር ፈሳሽ ፈንጂዎች መኪናው ላይ በተደረገ ፍተሻ ተይዘዋል።
🔸 የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የሩሲያን ጥቃት ለመግታት ፀረ-ሰው ፈንጂዎች ለዩክሬን እንዲቀርቡ ፈቃድ መስጠታቸውን የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ሁለት የአሜሪካ ባለስልጣናትን ዋቢ አድርገው ዘግበዋል።
🔸 የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር 275 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ወታደራዊ ዕርዳታ ለዩክሬን ለማስተላለፍ ማቀዱን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
🔸 ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከስፔስ ኤክስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኤሎን ማስክ ጋር በመሆን ከቴክሳስ ጣቢያ ተወንጭፈው በሕንድ ውቅያኖስ ላይ ያረፉትን የስፔስ ኤክስ ስታርሺፕ ስድስተኛ የሙከራ በረራ ተመልክተዋል።
🔸 ትናትና ምሽት የሩሲያ አየር መከላከያ፤ በ9 የሩሲያ ክልሎች የተፈጸሙ 44 የዩክሬን የድሮን ጥቃቶችን ማውደም እና ማክሸፍ መቻሉን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ዜናውን በእንግሊዝኛ ያንብቡ📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ
👉 ለአንድሮይ ስልኮች በዚህ
APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዩጵያን ይወዳጁ 👉
@sputnik_ethiopia