Sumeya sultan


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


ነጻ ሃሳብ! ነጻ ግጥም!!
ሃሳብ አስተያየት በ @Sumeyaabot አድርሱኝ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


አህለን
ወላሂ እንደዚህኛው ረመዳን በጉጉት የጠበቅኩት ያለ አይመስለኝም። አልሃምዱሊላህ የምንወደው ረመዳን መጣልን❤️❤️❤️❤️


"አስበሽዋል አላህ ዛሬ ጾሜን በቂም አልጀምርም ብለሽ አዉፍ ያልሽውን ሰበብ አድርጎ ሙሉ ወንጀልሽን አዉፍ ቢልሽ?" ስትለኝ "አላህ ፊት አቆማቸዋለሁ" ያልኩትን ሁላ ልቤ ሲለዝብላቸው አስተዋልኩ። አስባችሁታል ዛሬ ለርሱ ብላችሁ አዉፍ ያላችሁትን አላህ "እስከዛሬ ይሄ ባሪያዬ በኔ መንገድ ከሰራው ሁሉ ይሄ ተግባሩ በለጠብኝ"ቢልላችሁ?
ዱዓችሁ የማይመለስበት፣ህመማችሁ የሚሽርበት፣ ጭንቀታችሁ የሚረግብበት፣ከጌታችሁ የምትታረቁበት መልካም የረመዳን ጊዜ ይሁንላችሁ። ይሁንልን❤️
@sumeyasu


ተሰብሬ ነበር። ብቻዬን ሆኜ ተከላካይ አጥቼ። አላህ ጋር ብቻ ነበር አቅሙ ያለው። ከሱ ውጪ የምጠይቀው አልነበረኝም እና "ጌታዬ ሆይ ብቻዬን ነኝ" አልኩት። አላህ ብቻውን ቆመልኝ። ያስከፋኝን አካል አላህ ቀጣው። ያኔ ከሰው ጋር ባለኝ ግንኙነት እጅጉን ጠንቃቃ ሆንኩ። አስከፍቼ ዱአ እንዳይደረግብኝ። የኔ የአመጸኛ ባሪያውን ዱዓ የሰማ ጌታ ለሱ ቅርብ የሆነን ሰው አስከፍቼ ዱአ ቢያደርግብኝስ? የኔን ዱአ የሰማ ጌታ ሁሉንም ሰሚ ነው።


እስክትደሰቺ ነው ስጦታው
(ሱመያ ሱልጣን)

"አላህ እኮ ከዛፍ ላይ ስለምትወድቀው ቅጠል እራሱ ያውቃል" እያለች ስታወራ ያየውን መሰበሬን እያሰብኩ ፈገግኩ። "እንኳን አየህልኝ አይነት።
"وَلَسَوۡفَ يُعۡطِيۡكَ رَبُّكَ فَتَرۡضٰى

" ጌታህም ይሰጥሃል ትደሰታለህም።"(ዱሃ:5)

መስጠት ብቻ አይደለም የ አላህ ስራ እስክትደሰቺ መስጠቱ ነው" እያለች አብራራች። ረጅም የ እፎይታ መተንፈስን ትንፍሥ አልኩ። አለ አይደል ቅጠል መውደቁን የሚያውቅ ጌታ "እኔንም አይተወኝም" የሚል ተስፋ? አለ አይደል "ጉንዳንን የሚመግብ ጌታ እኔን እስክደሰት ይሰጠኛል" የሚል ጉጉት? እንዲያ ነው የሆንኩት። ድንገት የሜሴጅ ድምፅ ገባ እና ከ እንቅልፉ እንደባነነ ደንብሬ ስልኬን አየሁት። ከ እህቴ ነበር። ወላሂ አላህዬ እስከዛሬ ዱንያ ላይ ከሰጠኝ ፈተናም ደስታም በበለጠ ነገር ተበሰርኩ። አላህ እስክደሰትም ሰጠኝ።
እና ቅጠል ስትወድቅ የሚያውቅ ጌታ እያንዳንዱን ስብራት እያየ ነው። አላህም እስክትደሰቱ ይሰጣችኋል። በርሱ ብቻም ተመኩ እርሱንም ብቻ ጠይቁት
@sumeyasu
@sumeyaabot


የላይኛውን ጽሁፍ ከለቀቅኩ በኋላ የማውቃቸው ሴቶች ሜሴጅ ስልኬን አጨናንቆት አደረ።
"እከሊት ናት አይደል የነገረችሽ? "
"ሱም እንዴት አወቅሽብኝ?"
"ላንቺ እንደተነገረ አድርገሽ የጻፍሽው ከነገረሽ ሰው እንዳልጣላ ነው አይደል?"
ምንም እንኳ እኔ በቀጥታ የነገረችኝን ለመተንፈስ ብዬ ብጽፍም ቤታቸው ያለውን የተጻፈባቸው የመሰለባቸው ነበር። የታሪኩ ባለቤትም "ሌላውን ተይው እና አንዱን ህመም ብቻ የበረታብሽን ጻፊው" አለችኝ።
"ልጄ ታማብኝ ነበር። አንጠልጠለናት ሃኪም ቤት ሄድን። እንደተደፈረች የሚገልጽ ነገር ነገሩን። ቤት ውስጥ ከብዙ የሱ ወንድሞች ጋር ስለምንኖር ከነሱ ውጪ ማንንም መጠርጠር አልቻልኩም። " ባልተረጋገጠ ነገር ወንድሜን አታንሺው። አርፈሽ ተቀመጪ ሳይንስ ያለውን ሁላ አምነሽ ቤተሰቤን አትበጥብጪ።" አለኝ። ፍቺ ጠይቂያለሁ።" ሌላን ማለት አልችልም።ምን እላለሁ? አላህዬ በ ቲቪ በመስማት ብቻ ማቀውን ሲያሰማኝ ምን እላለሁ? አላህ ይፈርጃት እንጂ። በ ዱአችሁ
በየቤቱ ያለው ህመም ጭራሽ አስጨነቀኝ። ለ አንድ ወዳጄ
"ፈራሁ። ትዳር ያስፈራል። ዙሪያዬ ያለው መልካም ገጽታ የለውም" አልኳት።
" ታዲያ ለመፍራት ለመፍራት ለምን የ ፊርዓውንን ሚስት ትዳር አይተሽ አልፈራሽም? መጨረሻው ስለተነገረሽ ነው አይደል? ከወዱድ ጋር ያለሽን ግንኙነት ብቻ አሳምሪ። በሶብርሽ በርቺ እንጂ አላህዬ በምን እንደሚክስ በ አሲያ አይተሻል። ሁሉም ትዳር እንደዛ አይደለም። ትንንሽ ግጭቶች ልብሽን አያሸብሩት። እንኳን አብሮ የሚኖር የተለያየ ሰው ልብም እኮ በ ከፍታ እና ዝቅታ ውስጥ ነው ሃያቱ። ቀጥ ያለ ቀንማ እኮ አበቃለት።" አለችኝ ልቤን አረጋጋቻት።
@sumeyasu


"አሁን ቀለለኝ"
ሱመያ ሱልጣን

"ላወራሽ ፈልጌ ነበር ደውይልኝ!" ።በቃ ይሄን ነው ያለችኝ። ንግግሯን ቀለል አደራረጓ " እኔ ምልሽ ሻይ መቼ እንጠጣ?" የሚልን እንጂ ተራራን አንድሸከምላት" አደራ" የምትል አይመስልም ነበር። ቀለል አድርጋ " ላወራሽ ፈልጌ ነበር።"ብቻ
ስልኬን አንስቼ ስደውል ያነሳችበት ፍጥነት ጥሪውን ይቀድማል። በሳግ በታፈነ ድምፅ
"ሱም"
"ወዬ ምነው በአላህ አፈነሸ እንዴ ድምፅሽ?አየሩ ነው ሳይነስ?" ዘባረቅኩ። ሳቂታ እሷን እንዴት በ እንባ ልጠርጥራት?
" አንድ ጥያቄ መልሺልኝ" ልቤ እየፈራ እንድትቀጥል ስል ዝም አልኩ።
" የምትሳሺለት ብርጭቆሽ ሊወድቅ አየር ላይ ተንሳፎ ቢሆን እና እጅሽ ደግሞ ሌሎች ብዙ እቃዎች ሲወድቁ በስብርባሪው ጉዳት የቆሳሰለ ቢሆን ያን ብርጭቆ በቆሳሰለ እጅሽ ለመያዝ ትሞክሪያለሽ ወይስ እንዲወድቅ ትተይዋለሽ? ልጆችሽ ድምፅ እንዳያስደንግጣቸው ስትይ የቆሰል እጅሽን ለ ብርጭቆው ትልኪያለሽ ወይስ "ቢደነግጡ ለ ደቂቃ ነው" ብለሽ ለማገገም የሚቆየውን ቁስል ታስቀድሚያለሽ?" ከ እንባዋ ጋር ስትታገል እንደምንም ጨረሰች።
ጉዳዩ ስለ ብርጭቆ እንዳልሆነ ቢገባኝም ያቺ ከውጭ ስትታይ ሙሉ የምትመስለው ሴት ላይ "ምን ክፍተት አለ ብዬ ልገምት?"።
" ሱም መልሺልኝ"
"ምን ተፈጥሮ ነው? በአላህ አስጨነቅሽኝ"
"መልሺልኝ"
"የኔ ቆንጆ በአላህ ተጨነቅኩ"
ከቀድሞ እጅግ በበረታ ድምፅ ያለችውን መስማት እስኪያቅተኝ ድረስ እያለቀሰች
"ሱም ትዳሬ ትዳሬ" ለቅሶዋ የምትለውን ጨርሶ አያሰማም
"ትዳርሽ ምን ሆነ?"
"ብርጭቆው ሆነ" ለጭንቅላቴ ከባድ ነበር።
የሆነችውን የከፈለችውን የተደረገችውን የተሰማትን ሁሉ ጣልቃ ሳልገባባት በለቅሶዋ አጅባ አወራችኝ። እሷ ያን ስታወራ ረጅም ጊዜ ሳላያት ቆይቼ "እንዴት ናት ግን?" ብዬ ስጠይቅ "አምሮባታል ቢስሚላህ። ከቤት ስለማትወጣ ያ ቅላት ብሶበት አረብ መስላ" የተባልኩት በጭንቅላቴ መጣብኝ። አለች እየተባለች ስለጠፋችው ነፍስ ልቤ ቆሰለች።
አስተውያለሁ። እያወራችው እንባዋ ሲቀንስ። ጭንቀቷ ሲረጋጋ። ሸክሟ ከሷ ላይቀንስ ለኔ ስትደርበው። አይቻለሁ እየተረጋጋች ነበር።
"እንደ እድሜሽ አይደለሽም ብዬ ነው ማማክርሽ። ወይም ለትዳር እንዳትቸኩይ ከኔ እንድትማሪም ይሆናል። ብቻ አላቅም ይቅለለኝ ብዬም ይሆናል። ሱሚዬ ወላሂ ስለተነፈስኩ ይሁን አላቅም ተረጋጋሁ። አመሰግናለሁ የኔ እናት በኔ የደረሰ እንዳይደርስብሽ ዱዓ በማድረግ ነው ምክፍልሽ። በይ ቻው እሱ መጣብኝ" ብላ ዘጋችው።
በደሏ ከኔነቴ አጣላኝ። ሰው ሸሽቼ በጀመዓ እና በቢዚነት ተደበቅኩ። ያሸከመችኝ ቁስል "ቀለል አለኝ አሁን" ብላ እንዳለችው በቀላሉ የሚረጋጋ አልነበረም። በኔ እድሜ ሊደረግላት የሚችል እገዛ ባጣ ይሄን የሚያምር ትግስት ላለበሳት ጌታ ሰጥቼ ለራሴም ጤንነት ዱዓዬን አድረስኩ። ወዶ አይደለም ለካ ሰው የሚፈዘው🥹
ታሪኩ እውነተኛ ነው። አንዳንድ ቃላቶችን ከመቀየር ውጪ ያልተደባለቀበት። የነገረችኝን መጻፍ ፍቃድ ስላልጠየቅኩ ዘልዬዋለሁ
@sumeyasu
@sumeyaabot


የማይቆጨኝ 2ኛ እድል
( ሱመያ ሱልጣን)

ለተከፋሁበት ሰው 2ኛ እድል ከማይሰጡት ነኝ። ልከፋ የምችለው እጅግ በቀረብኩት ሰው ስለሆነ ላጣው አካባቢ ላለማጣት የምከፍለውን ያህል ለ 2ኛ እድል እጄ አይዘረጋም።
የምወዳት ጓደኛ ነበረችኝ። ሃይስኩል ነበርን። ገና ሁሉ ነገር ብርቅ የሆነብን ሰዓት። እና የሆነ ቀን ላይ ይሄ ለወጣትነት አዲስ መሆን አለያየን። የመከፋቴን ጥግ አልረሳውም ክፍሌ ውስጥ እንዳልታይ አንዱ ክፍል ላይ ጥግ ሄጄ እስከማልቀስ ነበር። የ "አይጎዳ" መጸዳጃ ቤቶች እንባዬ እስኪያጥባቸው። ከዛ ከልቤ ለረጅም ጊዜ አስወጣኋት። አንድ ቀን የ እድሜያችን ግርግር ሲያበቃ ድጋሚ ተፈላለግን እና "ይቅርታ" ም ባልነበረው እርቅ አብረን ቀጠልን። አሁን ላይ ዱንያ ላይ ካሉኝ ኒዕማዎች ውስጥ "እሷ" አንድ ብዬ ከምቆጥራት ናት። አለ አይደል የሆነ ቦታ ስትሄዱ ብቻውን የማይዘንጥ ሰው ፣ ይሄ የሰርጋችሁ ወይም የናንተ ፕሮግራም ላይ ራሱን የማያደምቅ እና ከናንተ በላይ የሚጨነቅ ሰው፣ ልክ ቤተሰቦቻችሁ እነሱን ሲያዩ ልባቸው የሚያርፍባቸው ሰዎች። እንደዛ ናት ለኔ።
እና ከሰሞኑ ለ 2 እና 3ወር አካባቢ በሆነ ድብርት ውስጥ ገብቼ ተደበቅኳት። መውደቄ ስለሚሰብራት አፍራታለሁ። ዛሬ ምንም እንኳን ከድብርቴ ባልወጣም የናፍቆቴን ጻፍኩላትና "ህይወት ላይ ስወድቅ እኮ ስለማፍርሽ ነው" ብዬ አልኳት።
"አብረን መውደቅ እንችላለን እኮ። ካልሞትኩ በስተቀር እኮ ሁሌም ላንቺ አለሁ እኮ ምንም ቢፈጠር" አለችኝ።
ወላሂ 3 ጊዜ ህይወት ላይ አሸነፍኩ። አንድ ስተዋውቃት፣ 2ኛ ድጋሚ እድል ሥሰጣት እና 3ኛው በምንም ሁኔታ ውስጥ እንዳለችኝ ምዬ መናገር ስለምችል።
@sumeyasu
@sumeyaabot


"ልባችሁን አውሱኝ"
በሱመያ ሱልጣን
አንዳንድ ሰዎች ሰደቃ መስጠት በደማቸው ውስጥ ነው። ወላሂ ኖሮት አንዴ የሚለግስ አውቃለሁ። ብዙ ኖሮት ያልገራለትም አይቻለሁ። የአንዳንድ ሰው መስጠት ግን ይለያል። በ ኢፋዳ ማህበረሰብ 22የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮዎችን በተለያዩ የኢትዮጵያ ገጠራማ ቦታዎችን በዚህ 2ወር ውስጥ ለማድረግ እንደመነሳታችን የብዙሃንን ልብ እያየሁ ስቀና ከረምኩ። ያላቸውን ደጋግመው ሰጥተው 1ብር የጨመሩልንን ተማሪዎች፣ ደጃቸው ሳያመላልሱ በ 100ሺዎች የለገሱ ሃብታሞች፣ የቲምነት እና የዱንያ አለመሙላት ያላጎደላቸው ምስኪን ነፍሶችን በ 10ሺዎች መሰብሰብ መቻል፣ ሙስሊም ያልሆኑ አካላትም የ ቴሌግራም ስቶሪዎቻችን እያዩ የሰጡትን እያየሁ ወላሂ ልቦቻቸውን ተመኘሁ😍😍በምን ስራ ነው አላህ ያን ልብ የሚሰጠው? አታውሱኝም?
ከዚህ አጅር መካፈል የሚፈልግ
@sumeyasu
@sumeyaabot
ላይ ያውሩኝ


በጣም ጮክ ብዬ እያወራሁ እና እየሳቅኩ ነበር። እንደ 17 አመት ልጅ ቅዥቅዥ እያልኩ። "ሱምሊ እኮ ታድለሽ ሁሌ መሳቅ" እያሉኝ ነበር። እሷ የምትጠጣውን ቡና ቁጭ አድርጋ ሳብብብ አድርጋ ይዛኝ ወጣች።
"ሱም ደህና ነሽ?" ስትለኝ ነው "ከየት መጣ?" የማይባል እንባዬን ያዘራሁት። ብቻችንን ነበርን። በሳቄ መሃል ያየችውን ሃዘኔን ተወጣሁባት። በመሳቅ ውስጥ የደበቅኩትን ሃዘን በመንቀዥቀዤ ውስጥ የሸፈንኩትን ተስፋ መቁረጥ ትከሻዋ ላይ አረገብኩት። ከዛ "ሱምሊ እኮ ታድለሽ ሁሌ መሳቅ" የሚለውን እያስታወስኩ ፈገግግግግ።
የሳቅን ሁላ ደልቶን አይደለም። እኛን እያያችሁ ህይወት በናንተ ላይ ብቻ የዞረች አይምሰላችሁ
@sumeyasu
@sumeyaabot


ያማረ ኺታም
የ እርሷማ ኺትማ ከብረት መዝጊያ
ከመልከ መልካም ከ አይን መርጊያ
እየተባለ
ከ አንዱ አንዱ ሲገፋ ከርሞ
               ለርሷ ሳይመጥን
በሃብት በ ዘር ሲታይ ሲመዘን
ከ ቀናት በ አንዱ ጌትየው ሲሻው
ከባሮቹ አንዱን ለሷ መረጠው
ከመልክ ያልሰጠው ከሃብትም እንዲያ
መጠሪያ የለው ከሙስሊም ወዲያ
አባት ቅር አለው ለ'ንደሱ ላለ
                 ብሌኑን ሊያጭ
እምቢ አይል ነገር አሸማጋዩ
              የ አለም በላጭ
እናት አቃታት ልቧን እምቢ አለው
እንዴት ለዚህ ሰው ልጇን ትዳረው?
ሙሽሪት ሰማች
የጠየቃት ሰው
መልክተኛውን አጥብቆ ይወዳል
ከአኺራ ውጪ
       ሃጃ የለውም ልቧ ያን ያውቃል
የተላከባት
  ከነፍሷ አልቃ ምትወዳቸው ሰው
ሳታመነታ "እሺ" ን መለሰች
            ሰው ያጥላላውን ለ አላህ ሰጥታው
ያላቀቻቸው ታላቁ ነብይ እርሷን መረቋት
ባትታደለም ያፈቀረችው መዝለቅን አብሯት
ከ እለታት ባንዱ ጀግና የልቧ ሰው
ገዝዋ ሄደና አፈር ዱንያን ተሰናበተው
ከነቢ ውጪ
ሁሉም ሰው ረሳ መሞት መኖሩን
እሳቸው ብቻ ልባቸው አወቅ
            ይህ ሰው መጉደሉን
ከፈን ከፍነው ሊሰገድበት እያዘጋጁት
እርሱ ከሳቸው እሳቸው ከርሱ
         መሆናቸውን መሰከሩለት
ምስኪን ጁለይቢብ ዱንያ ጤፉ
መመረጡ ነው በጌታው
              መንገድ ልቡ ማረፉ
@sumeyasu
@sumeyaabot




መስጠት በተሰጡ ነፍሶች እቀናለሁ። በ አላህ የተመረጡ እንደሆነ ይሰማኛል።
ጀነት ላይ የተቀጣጠሩ ሰዎች ለወደዱት የወደዱትን በ 22 የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ላይ አሻራ እየጣሉ ቀጠሮዋቸውን እያጸኑ ነው።
አላህ ያማረን መቀበል ይቀበልልኝ😍😍


መሰጠት የተሰጣቸው ሰዎች ለሚወዱት የወደዱትን ሲሰጡ። የ ጀነት ላይ ቀጠሮዋቸውን በሰደቃ ሲያሲዙ አይተን "አላህዬ የመውደድን ጥግ ይውደዳችሁ" እንላለን አላህ ያማረን መቀበል ይቀበለው😍😍


የወደድኩትን ለወደድኩት
ሱመያ ሱልጣን
"ይሄን ሱቅ ዘጉት እንዴ?" አለኝ የህጻናት ልብስ መሸጫ የነበረበትን የሰፈራችንን ሱቅ ስናልፍ። ገና የትውውቃችን ሳምንት ነበር።
"አዎ የስጦታ እቃ መሸጫ ሊያደርጉት መሰለኝ" አልኩት።
"ምንድነው የምትወጂው ስጦታ?" አለኝ ቀኝ እጁ የመኪናውን መሪ እንደያዘ አንገቱን ወደኔ አዙሮ በፈገግታ።
"ሰው ለራሱ የወደደውን ሲሰጠኝ" አልኩት።
ዛሬ ከ አመታት በኋላ በአዘቦት ቀን በቤት ስራ "busy" ሆኜ ሰዓቱን ለማየት ስልኬን ሳነሳ ከባሌ 3 ሜሴጅ አየሁና ከፈትሁ
1ኛው ሜሴጅ
" ሃያቲ አሰላሙ አለይኪ"
2ኛው "የወደድኩትን ለ ወደድኩት በሚል ሪዝን ወደ ሰደቃ የገባ ገንዘብ "screenshot"
3ኛው "የውሃ ጉድጓድ ለማስቆፈር " ብለው ቢሮ ላይ ኩፖን ሲሸጡልኝ " ለፍቅሬ" ብዬ በስምሽ" አለኝ።
በ አመታት ውስጥ የነገርኩትን አልረሳም። ጀነት ይዞኝ ሊገባ የወደደውን ወደደልኝ።
እናንተም ለወደዳችሁት የጀነት መግቢያ ትኬት ግዙለት። በ 22 የ ጉድጓድ ውሃ ቁፋሮ ላይ ዛሬ ከናንተ ጋር ለሌለ ሰው፣ ለምትወዱት፣ ጀነት ላይ ለተቀጣጠራችሁት፣ ጀነት አብራችሁት መግባት ለምትፈልጉ ሰው ነይታችሁ ለግሱ።
አካውንት ለሚፈልግ @sumeyaabot አዋሩኝም
"ስጦታ ፍቅርን ይጨምራል" ነብዩ(ሰ.ዓ.ወ)


አግቡ
"ቀይ አበባ እንደምትወጂ አስቤ ነው" ብሎ 1ፍሬ ቀይ አበባ ፊቱ ሙሉ ሳቅ በሳቅ ሆኖ ሲሰጠኝ እድሜ ልኬን ነጭ አበባ እንዳልወደድኩ ሆኜ ቀይ አበባን አፈቀርኩ።
ሰርግ ሲሉኝ ሁላ "ኧረ ወደዛ ማን ከ ቬሎ ጋር ይጎትታል" የምለው እኔ "በ ቬሎ የምታምሪ ይመስለኛል" ሲለኝ የስልኬ "ጋለሪ" በ ቬሎ ዲዛይን ሞላ። የሰርጌ ቀን ቬሎሽ ሲያምር ሲለኝ ድንኳን የሚመስለውን ጎታታ ቬሎ ሳላወልቅ መቅረትን ልቤ ተመኘ። እንደዚህ ነው ከ ቃሉ ጋር ተፋቅሬ የምቀረው። "ወንድ ልጅ አግብቼ አስተምራለሁ ካለ በልጅ ነው ዲግሪ ሚያሳቅፍሽ" ያሉኝን ሰዎች እሱ ፈተና ሲኖርብኝ እሱ ልጆቼን ከስራ እየቀረ እስከ ማስተርስ እንዳስተማረኝ መንገር ያምረኛል።
"አዪ ወንድ ልጅ ባክሽ መድከም አይፈልግም ካንቺ የተሻለች የቀራች ያመጣል" ሲሉኝ በሱ እገዛ 13ጁዝ እንዳፈዝኩ አያውቁም
ብቻ ማግባት ደስ ይላል ወጣቶች አግቡ❤️
@sumeyasu
@sumeyaabot


ዝም
ሱመያ ሱልጣን
ሂጃብ ያልገራላት የ 1ልጅ እናት እና ባለትዳር አረብ ቲክቶከር አለች። ከ እናቷ ጋር አስቂኝ ቪዲዮዎች ሲለቁ ነው የማውቃቸው። ከ 2ሳምንት በፊት የሚያምር ጥቁር ረጅም ጸጉሯን "ስታይል ለመቀየር" ብላ ቨአጭሩ ስትቆረጥ በጣም ብዙ ኔጌቲቭ አስተያየቶች የ ኮመንት ቦክሱን ሞሉት። "ፋሽን ብለሽ ገና አንገትሽን ትቆርጫለሽ፣ ለምን ሙሉ አትላጪም ምናገባን..." ከቀናት በኋላ ሙሉውን ተላጭታ ኮፍያ ማድረግ ስትጀምር አሁንም እጅጉን የበዛ ሰው በስድብ አሰጣት። ዛሬ ወጥታ በ ጡት ካንሰር ምክንያት ኬሞ ላይ እንደሆነች እና በዛ ምክንያት ጸጉሯን እንዳጣች ምናምን አወራች።
ፊቱ ላይ የሳቅ ብርሃን የታየበት ሁላ ደስተኛ አይደለም። ያልወደድነውን ማውገዝ ማለትም መሳደብ አይደለም። ብዙዎቻችን በ አድካሚ የህይወት ጉዞ ፈገግ ብለን የምንራመደው ተመችቶን አይደለም ሌላው ላይ ድካም ላንጨምር ብለን እንጂ።
ዝም እንበል!
@sumeyasu
@sumeyaabot


Ifada Community Hadra Chain dan repost
የኢፋዳ ኢስላማዊ ድርጅት የYouTube ቻናል ላይ እሁድ የምናስተላልፈውን የላይቭ ስርጭት ለማስተላለፍ ቻናሉ 1k ሰብስክራይበር ያስፈልገዋል በመሆኑም እኛ ኢፋድዮች የወደድነውን ለሰዎች ማካፈል ማይሰለቸን ነንና ቻናላችን ሰብስክራይብ እንዲደረግ የበኩላችንን አስተዋጽኦ እናበርክት።

ለምናቃቸው በሙሉ ሼር እናድርግ እስከ ጁምአ ማታ ዘመቻ እናድርግ።

ከላይ በተቀመጠው QR code ስካን በማድረግ ወደ ኢፋዳ ኢስላማዊ ድርጅት የማህበራዊ ሚዲያ ድህረገጾችን መቀላቀል ይችላሉ ።

ይህ የyoutube ቻናላችን ሊንክ ነው ።👇👇👇

https://youtube.com/@ifadaislamicorg?si=WQ--SeP_VHVnsegm


ቂያማ እና አየር መንገድ
(ሱመያ ሱልጣን)
እንደ አየር መንገድ ትልቅ የቂያማ ማስታወሻ መኖሩን እጠራጠራለሁ። መያዝ የሚችለውን ብቻ ይዞ መሄዱ፣ ከወዳጅ ዘመድ እየተላቀሱ እና እየተቃቀፉ መለያየቱ ፣የያዝነውን በሚመለከተው አካል ማስመዘኑ፣ የ አየር መንገዱን ፕሮሰስ አልፎ እስከ ፕሌኑ መገኛ መጓዙ እና ለመዳረሻ መሮጡ ሁሉም ቂያማን የማስታወስ ሃይል አለው። ከዛ ደግሞ የናፈቁን ወዳጆቻችንን ስናገኝ ያለው ጀነትን ይመስለኛል። የሚጠብቀንን የተደበቅነውን መርዶ መስማቱ ደግሞ ጀሃነምን ያስታውሰኛል። እነዛ የናፈቅናቸውና የናፈቁንን የምናገኝበት የጌትዬን ጀናህ አላህ ይወፍቀን💚
@sumeyasu
@sumeyaabot


"ፍትህ"
(ሱመያ ሱልጣን)
ታናሽ እህት አለችኝ ስሟን በስሜ አስከትዬ እራሴን "ሱምሊና" ብዬ የምጠራባት። ሊንዬ ሲደክማት ሁላ አዝናለሁ! በጣምምምም ብዙ አመታትን "ጠበቃ" መሆን እመኝ የነበረው የመደፈር ዜናዎችን እኔም ቤት ደርሶ እስኪገድለኝ ድረስ "አዑዙ ቢላህ፣ አስተግፊሩላህ!" እያልኩ ቲቪዬን ላለማጥፋት እና ፍትህ ለማምጣት ነበር። እያንዳንዱ የመደፈር ዜናዎችን ሳይ የማለቅሰው "ሊንዬ ብትሆንስ" እያልኩ ነው። ጓደኞቼ " የሊናን ጦስ" ይላሉ። እኛ ቤት የማይደርስ ይመስል!
ሴት ሆነን ስንወለድ ጀምሮ ከሞት እኩል ተሸክመነው የምንወለደው ጉዳችን፣ ሰቀቀናችን ነው። የማዝነው እኔ እራሴን እንኳን መከላከል በማልችልበት ሁኔታ ታናሽ እህት እንዳለኝ ማሰብ ነው። ስለ 1ሄቨን አይደለም ነገሩ ስለ እያንዳንዱ ቀናችን ነው ፍትህ የምንለምነው፣ በ አባያ እና ጅልባባችንም ውስጥ ለማይቀርልን ትንኮሳ ነው፣ የመደፈራችን መልስ "ምን ለብሳ ነበር?" ስለሆነብን ነው፣ ፍትህ የምንለው እያንዳንዱ ቀናችን ላይ "ማነሽ ሰሚራ፣አታወሪም እንዴ? አንቺን እኮ ነው!" እየተባልን እየተጎተትንም ወጥተን ስለምንገባው ነው፣ በ እያንዳንዱ ቀን ሶሻል ሚዲያ ላይ ፎቶ ኖረን አልኖረን፣ ፖስት አደረግን አላደረግን በውስጥ ለሚደርሱን የጾታዊ ንግግሮች እና ዝም ስንል ለሚደርሱብን ስድቦች ነው፣ "ፍትህ" እያልን የምናለቅሰው ስለሞተችው ሄቨን ብቻ አይደለም ስለምንሞተው ብዙዙዙ ሄቨኖች ነው። እኔ "ፍትህ" ን ከመንግስትም ሆነ ከሰው ፍጥረት አልጠብቅም። ፍትህ ያለው በጌታዬ እጅ ነው "አልጀባር" በጀባርነቱ ፍትህ እንዲሰጠን ነው ዱዓዬ። ይኔ ልመና "አልሰታር" ሁሉንንንንንምምም ሴት ከ አረመኔዎች እንዲሰትረን ብቻ ነው። ፍትህ የ አላህ ነው!!!!!
ተቃጠልን
@sumeyasu
@sumeyaabot


ሰሪውን ነው ማመን
(በሱመያ ሱልጣን)
የ ልጅ እጄን በ ወፍራም መዳፉ ጥብቅ አድርጎ ይዞኝ መንገድ እየሄድን የምናውቃትን ከኔ በ 2አመት ከፍ የምትልን ልጅ ስም ጠርቼ 2ጥርስ እንዳወለቀች ነገርኩት። ወደኔ ዞር ብሎ ፈገግ ካለ በኋላ "አንቺም አሁን 6አመትሽ አይደል ልክ 7 ሲሆንሽ ታወልቂያለሽ" አለኝ። አስታውሳለሁ የጥርሶቼን ጥንካሬ ለማስረዳት የዘባረቅኩትን ብዛት። "የኔ ድርድር ያሉ የተጣበቁ ጥርሶቼ ሊወጡ?"
ደጋግሜ ስሙን እየጠራሁ" እየኝማ እየኝማ ጥርሴ እኮ አልተነቃነቀም ሁላ የኔ እኮ ጠንካራ ነው" ለፈልፋለሁ። "እሺ" ብቻ አለኝ። ከ አመት በኋላ ጥርሴ ተነቀለ። 1ብቻ አይደለም እየቆየ ብዙ ነቀልኩ። ከዛ ደግሞ ተመልሶ በቀለ።
ካደግኩም በኋላ "በጭራሽ እኔ ላይ አይሆንም" ያልኩት ሲሆን በሌላ ሲተካ አየሁና ህይወት ገባችኝ።
ዱንያ ላይ በሰሪው እንጂ በስራው መተማመን ያከስራል።
@sumeyasu
@sumeyaabot

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.