👉 ዓሹራእና ምንዳው
ዓሹራእ ማለት የሙሐረም ወር 10ኛ ቀን ሲሆን ከነብዩላሂ ሙሳ አስገራሚ ታሪኮች አንዱን የሚያስታውሰን ቀን ነው ።
ነብዩላሂ ሙሳ ፊርዓውን ህፃናቶችን በሚያርድበት ዘመን ተወልደው በራሱ ቤት እንዲያድጉ አላህ ያሻውን ሰሪ የሆነው ጌታ አደረገ ። ይህም ፊርዓውን በይተል መቅዲስ አካባቢ የተነሳ እሳት የግብፅን ምድር ሲያጠፋ በህልሙ ያይና ለጠንቋዮቹና ድግምተኞቹ ሲነግራቸው ከእስራኤላዊያን የሚወለድ ህፃን የንግስናቸው መጥፊያ ሰበብ እንደሚሆን ነግሩት ። ፊርዓውንም ከሚወለዱት ህፃናት ሴቶቹ ቀርተው ወንዶቹ እንዲታረዱ አዘዘ ። ይህ ነገር አገልጋይ እንዳያሳጣቸው የፈሩ ግብፃዊያን ፊርዓው ዘንድ አቤቱታ ሲያቀርቡ አንድ አመት የሚወለደው ተትቶ በሚቀጥለው አመት የሚወለደው እንዲታረድ አዘዘ ። የአላህ ፍላጎት ሆነና ነብዩላሂ ሙሳ ወንድ ህፃናቶች በሚታረዱበት አመት ተወለዱ ። የእስራኢላዊያን ህፃናት መወለድ የሚጠባበቁ ሰራዊቶች በመኖራቸው የነብዩላሂ ሙሳ እናት ጊዜዋ በሚታረድበት ጊዜ በመድረሱ ጭንቅ ውስጥ ገባች ። የተፈራው አልቀረም ህፃኑ ተወለደ ። እናት ምን ይዋጣት !!!!!?
አላህ ሁሉን ቻይ መሆኑን ሊያሳያት በሳጥን አድርገሽ ወደ ቀይ ባህር ወርውሪው የሚል መልእክት እንዲመጣላት አደረገ ። ወረወረችውም ። ወደ አላህም ፍፁም ተማፀነች ። አላህም ልጇን እንደሚመልስላት ቃል ገባ ። ባህሩ ሳጥኑን ወደ ፊርዓውን ቤተመንግስት እየነዳ አደረሰው ። የፊርዓው አገልጋይ ሴቶች ሳጥኑን አገኙት ሲከፍቱት የሚያምር ህፃን ነው !!! ። ወደ ቤተመንግስት ተወሰደ ። ኣሲያ የፊርዓው ባለቤት የአይናችን ማረፊያ ይሆናል ልጅ አድርገን እንያዘው አትግደለው አለችው ተቀበላት ።
ረሃብ ይዞት ሲያለቅስ የሚቀርብለት ጡት በሙሉ እንቢ አለ ። ምናልባት የሚስማማው ጡት ከተገኘ ብለው ሴቶችን ሲፈለጉ እህታቸው ማንነቷን ደብቃ አንድ ህፃናት በሙሉ ጡቷን የሚጠቡላት ሴት ላመላክታችሁ ወይ ብላ ጠየቀች አው አሉ ። እናታቸው ወደ ቤተመንግስት መጣች !!! ። ሱብሃናላህ በፊርዓውን ቤተመንግስት በእሱ ተንከባካቢነት በእናታቸው ጡት እንዲያድጉ አላህ አደረገ ። አላህ በሙሐረም 10ኛ ቀን ፊርዓውንን አጥፍቶ እሳቸውንና ህዝቦቻቸውን ነጃ አወጣ ።
የአላህ መልእክተኛ ነብዩ ሙሐመድ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም – ወደ መዲና ሲሄዱ አይሁዶች ይህን ቀን ሲፆሙ አገኙዋቸው ። ለምንድነው የምትፆሙት ብለው ሲጠይቁዋቸው ይህ ቀንማ አላህ ፊርዓውን አጥፍቶ ሙሳን ያዳነበት ቀን ነው ። ለዚህ ነው የምንፆመው አሉዋቸው ። እሳቸውም ለሙሳማ እኔ ከናንተ የቀረብኩኝ ነኝ ብለው መፆም ጀመሩ ተከታዮቻቸውንም እንዲፆሙ አዘዙ ። ያለውንም ምንዳ ሲናገሩ እንዲህ አሉ : –
" صِيَامُ يَوْمِ عَرَفَةَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ وَالسَّنَةَ الَّتِي بَعْدَهُ وَصِيَامُ يَوْمِ عَاشُورَاءَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ "
رواه مسلم ( 1162).
" የዓረፋ ቀንን መፆም ያለፈውንና የሚመጣውን አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ።
የዓሹራእ ቀንን መፆም ደግሞ ያለፈውን አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ "።
ኢማሙ ሙስሊም ዘግበውታል ።
Copy