ስፓኒሽ ፍሉ ጥሎት ያለፈው ቆሻሻ የማቃጠል እና የማጠን ባህል
፣
ልክ ዛሬ ህዳር 12 ቀን፣ ነገር ግን በ1911 ዓ.ም በአዲስ አበባ የህዳር በሽታ እጅግ የበዛ ሰው ገደለ። በዚህ ምክንያት ዛሬም ድረስ ህዳር 12 ቀን ሲመጣ ከማለዳ ጀምሮ፤ አዲስ አበባ በጭስ ትታጠናለች። ሁሉም ከየቤቱ ቆሻሻ አውጥቶ ያቃጥላል። ይህ የህዳር 12 ባህል ከመቶ አመት በላይ ሆነ። በዚህ ቀን በአዲስ አበባ እዚህም እዚያም ጭስ ስለሚታይ፤ ብዙዎች “ህዳር ታጠነ” በሚል ያልፉታል። ለመሆኑ ከዚህ የህዳር በሽታ ጀርባ ምን ታሪክ አለ?
ነገሩ እንዲህ ነው። ይህ የህዳር በሽታ በአንደኛው የአለም ጦርነት ወቅት፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል። በሽታው እንደጉንፋን አድርጎ በሳል ይጀምርና በሽተኛው ላይ ከፍ ያለ ትኩሳት ያወርድበት ነበር። የሰውነት ውጋት እና ቁርጥማትም የበሽታው ምልክቶች ነበሩ። ምናልባት አሁን በመላው አለም ከተዛመተው የኮቪድ 19 ጋር የሚያመሳስለው ምልክት በዛ ያለ በመሆኑ፤ “ኮሮና ድሮም ነበር እንዴ?” ያስብላል። የሆኖ ሆኖ ብዙዎች ይህን በሽታ ግሪፕ ይሉታል። ሌሎች ደግሞ ስፓኒሽ ፍሉ ይሉታል።
በመላው አለም በዚህ የህዳር በሽታ ምክንያት 50 ሚሊዮን ሰው ሞተ። በመላው አለም ከሚገኙት ህዝቦች 1/3ኛው በዚህ በሽታ ተጠቅቶ፤ መልሶ አገገመ። በኢትዮጵያም በህዳር በሽታ ምክንያት በአዲስ አበባ ውስጥ ብቻ አርባ ሺህ ሰው ሞተ። ይህም የቀብር ስርአት የተደረገላቸውን እንጂ፤ በየቦታው ሳይቀበሩ የቀሩትን አይጨምርም። በዚህ የህዳር በሽታ ምክንያት በአንድ ቤት ውስጥ የሚገኙ እናት አባት፤ ልጆች ጭምር አብረው ሞተው ይገኙ ነበር። በብዙ ቦታዎች የአዲስ አበባ ሟች የሚቀብረው ሰው ጠፍቶ፤ አውሬ ይበላው ጀመር። መቃብር ቆፋሪ ብቻ ሳይሆን ሬሳ ተሸክሞ የሚወስድ ሰው ጠፋ። በአንድ መቃብር ውስጥ ሁለት እና ሶስት ሰዎች ይቀበሩም ነበር።
ይህ በሽታ በንፋስ መጣ ተብሎ ስለሚታመን በወቅቱ የነበሩ አዋቂዎች የንፋስ ቸነፈር ብለው ይጠሩታል። በሽታው በሸዋ እና በሌሎች አካባቢዎች ተዛምቶ ስለነበር፤ በኦሮምኛ “ዱኩባ ቂሌንሳ” ወይም የንፋስ በሽታ የሚል ስም ተሰጥቶት ነበር። በዚያን መጥፎ ዘመን… ከታዋቂ ሰዎች መካከል የአዲስ አበባ ከንቲባ የነበሩት ወሰኔ ዛማኔል ህዳር 12 ቀን ሞተ… አዲስ አበባ ያለመንግስት ቀረች። ከሶስት ወራት በኋላ ግን ነገሮች እየተሻሻሉ መጥተው፤ ለአዲስ አበባም ቀኛዝማች ማተቤ አዲስ ከንቲባ ሆነው ተሾሙ -1911። ከዚያ በኋላ በየ አመቱ ህዳር ሲመጣ አዲስ አበባ ትታጠን ጀመር። ከህዳር ውስጥ ደግሞ …በተለይ ህዳር 12 ቀን ተመርጦ ቆሻሻ ይቃጠልበት ጀመር። ቆሻሻ የማቃጠሉ ባህል በአዲስ አበቤዎች ዘንድከአንድ መቶ አመታት በላይ ቆየ - እነሆ ባህልም ሆነ።
፣
ዳዊት ከበደ ወየሳ