ዓድዋ‼️
"ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል!"
እንኳን ለ129ኛዉ የዓድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
የአድዋ ጦርነት ኢትዮጵያዊያን የአፍሪካ አዉራ ህዝቦች መሆናቸውን ያረጋገጡበት፣ በደም እና በህይወት ነፃነትን የተቀነጀንበት የማሸነፍና የድል ምዕራፍ ነው።
በመላው ኢትዮጵያዊያውያን የተመራዉ የአድዋ ጦር እያቅራራ፣ እየፎከረ እና እየሸለለ በመዝመት ለመላው የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ምልክት ሆነዋል።
አድዋ ኢትዮጵያዊያንን በአንድነት ያስተሳሰረ የአንድነት ገመድ ነው።
የአድዋ ጦርነት ለኢትዮጵያዊያን የህልውና የነበረ ስሆን ለቅኝ ገዥ ፋሽስት ደግሞ የቅኝ ገዥነት ስሜት ለማርካት ያሰበ ነበር።
ሆኖም ግን ጀግናዉ የኢትዮጵያ ህዝብ የጦርነት ጊዜ ወታደር እና የሰላም ጊዜ ገበሬ አሻፈረኝ በማለት ገፍቶ የመጣዉን የውጭ ጠላት ሀይል በመጣበት እግሩ አንበርክኮ እና ማርኮ ወደ መጣበት ሸኝተዋል።
እኛ ከተባበርን እና አንድነታችንን ካጠናከርን የሀገራችንን ስምና ክብር ከፍ በማድረግ ድህነታችንን ታሪክ ማድረጋችን አይቀርም።
በመጨረሻም የአድዋን የአይበገሬነት ወኔ በመላበስ የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች ወደ መልካም ዕድል በመቀየር ፀጋዎቻችንን በሙላት ለህዝብ የላቀ ተጠቃሚነት ለማዋል ሁላችንም የድርሻችንን በተነሳሽነት እንድንወጣ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
እንኳን ለ129ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሰን ! አደረሳችሁ !!
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሉን Join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇
https://t.me/thejamalnews#the_ጀማል