"ቅኝ ገዥ ኃይሎች በአፍሪካ ግጭትን እያቀጣጠሉ ነው" - ጄነራል አልቡርሃን
የሱዳን ሉዓላዊ ምክርቤት ሊቀመንበር ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን በካርቱም ከጊኒ ቢሳው አቻቸው ኡማሮ ሲሴኮ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ ወቅት፣ "አፍሪካ በውጭ ጣልቃ ገብነት እየተናጠች ነው" ያሉት አልቡርሃን ለዚህም በደፈናው የውጭ ኃይሎች ሲሉ የጠሯቸውን ሀገራት ወቅሰዋል።
ጄነራሉ፣ "አንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት የድሮውንና ዘመናዊውን ቅኝ ግዛት ለመታገል ያሳዩትን ቁርጠኝነት እንደግፋለን" ብለዋል።
በሱዳን በቀጠለው የርስበርስ ጦርነት አልቡርሃን የሚመሩት የሀገሪቱ ጦር የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ለፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ድጋፍ እያደረገች ነው በሚል በተደጋጋሚ ይከሳል። #anadoluagency
@ThiqahEth