"የባለሙያውን ሚና ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ እና እንደ ስጋት የጠቀስናቸውን ጉዳዮች ተመልሰውልናል " -የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የኢትዮጵያ ሕንፃዎች አዋጅን፤ አዋጅ ቁጥር 1356/2017 አድርጎ በሙሉ ድምጽ ማጽደቁ ይታወሳል።
አዋጁ የወጣው በነባሩ የኢትዮዽያ ህንፃ ሕግ ይታዩ የነበሩ ክፍተቶችን በመሙላት የህዝብ መገልገያ ህንፃዎች ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽነትንና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ለማስቻል ነው ተብሏል።
አዋጁ ከመጽደቁ በፊት ረቂቁ ለከተማ መሰረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በቀረበበት ወቅት ረቂቁ ከዚህ ቀደም የነበረውን "ባለሞያ ተኮር " ሂደት በአዲሱ ረቂቅ "ድርጅት" ተኮር እንዲሆን መደረጉ አግባብ አይደለም በሚል ከኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር እና ከሌሎችም ትችት ሲቀርብበት ነበር።
ከዚህ ቀደም በነበረው አዋጅ ባለሞያ ተኮር የሆኑ እና የባለሞያውንም የሞያ ክብር የሚያረጋግጡ አንቀጾች በአዲሱ ረቂቅም እንዲካተቱ እና ወደ ድርጅት ተኮር ወደ ሆነ አሰራር እንዳይቀየሩ የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር ጠንከር ያለ ክርክር ሲያደርግ ቆይቷል።
ክርክር ሲያደርግ ከቆየባቸው ነጥቦች ውስጥ አዋጁ ማተኮር ያለበት እያንዳንዱ ባለሞያ ማለትም አርክቴክት፣ ስትራክቸራል ኢንጂነር፣ የኤሌክትሪክ ባለሞያ የሚመለከተውን ስራ ብቻ እንዲሰራ አዋጁ ማረጋገጥ አለበት የሚለው አንዱ ነው።
ይህ ካልሆነ ድርጅቱ እነዚህን ባለሞያዎች ቀጥሮ ሲያሰራ ሃላፊነታቸውን በትክክል መወጣታቸውን በማያረጋግጥ መንገድ ከመሆኑም በላይ ጥቅሙ ወደ ድርጅት ሲሄድ ጥፋት ሲኖር ግን የጥፋት ተጠያቂነትን ወደ ባለሞያው የሚያመጣ አሰራር መሆኑን ሲገልጽ ቆይቷል።
በተጨማሪም የህንጻ ዲዛይን ስራን ማንኛውም ሰርተፍኬት ያለው ባለሞያ ወይም ሌላ ሰው ማስተባበር እንዲችል በመጀመሪያው ረቂቅ ላይ መቅረቡ አግባብ አለመሆኑን እና ሁሉም ሙያውን አክብሮ እንዲሰራ መደረግ እንዳለበትም ሲገልጽ ቆይቷል።
የማህበር ፕሬዝዳንት አርክቴክት ሐብታሙ ጌታቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት "ረቂቁ ላይ ሃሳባችንን ከሰጠን በኋላ የመጨረሻ ረቂቁን የማየት እድል አልነበረንም አሳዩን ስንል እናንተ የምትሰጡትን ግብአት ስለጨረሳችሁ ተሳትፏቹ አልቋል ስንባል ከተጠያቂነት ለመዳን በሚል ረቂቁ በሙያ እና በሙያ ባለሙያ ላይ ስጋት የሚያሳድር በመሆኑ ስጋቶች አሉን በሚል አቋማችንን አሳውቀናል" ብለዋል።
ማህበሩ በወቅቱ በአቋም መግለጫው ያሳወቃቸው እና በረቂቁ ላይ መካተት አለባቸው በማለት አጽንኦት የሰጠባቸው ነጥቦች
1) አዋጁ ድርጅት ተኮር ሳይሆን ባለሙያ ተኮር ተደርጎ መዘጋጀት እንዳለበት።
2 ) የሙያ ጥሰት ተጠያቂነት የሚመጣው በገለልተኛ የባለሙያ ቦርድ ተገምግሞ እንጂ ሚዛናዊነትን ባልጠበቀ መልኩ አንድ ተቋም ራሱ ከሳሽ ራሱ መርማሪ እና ራሱ ፈራጅ መሆን እንደሌለበት።
3 ) የሕንፃ ዲዛይን ስራ የአርክቴክቱ የፈጠራ ውጤት እንደመሆኑ በብቸኝነት የዲዛይን ስራን ማስተባበር ያለበት አርክቴክቱ መሆን አለበት የሚሉ ነበሩ።
የማህበሩ ፕሬዝዳንት አርክቴክት ሐብታሙ በአቋም መግለጫው የተካተቱት ነጥቦች በትክክል መመለሳቸውን እና በአዋጁ ተካተው እንዲጸድቁ መደረጉን ነግረውናል።
"በተለይ የባለሙያውን ሚና ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ እና እንደ ስጋት የጠቀስናቸውን መሰረታዊ ጉዳዮች በሙሉ ምላሽ በማግኘታቸው ይህንን ድምፃችንን ሰምተው ተገቢውን ማስተካከያ ያደረጉ አካላትን በሙሉ ማህበሩ ማመስገን ይፈልጋል" ብለዋል።
"በብዛት እኛ ሃገር ያለው ልምምድ እንደሚያሳየው የህንጻውን ዲዛይን የሰራው ባለሞያ ሳይሆን ሌሎች ገብተው ህንጻውን ሲያምሱት ይታያል መጨረሻ ላይ ተጠያቂ የሚሆነው ግን ዲዛይነሩ ነው የአሁኑ አዋጅ ግን በግልጽ ህንጻውን ዲዛይን ያደረጉት ሰዎች ገብተው ሥራውን ሰርተው ተቆጣጥረው የማስረከብ ሃላፊነትን ከተጠያቂነት ጋር ሰጥቷል ለዚህም ምስጋና አለን" ብለዋል።
የማህበሩ ፕሬዝዳንት "ገለልተኛ የሞያ አጣሪ ቦርድ የሚለው ወይም በአቋም መግለጫው ላይ በሁለተኛነት የተቀመጠው ይቀራል በደንብ እና በመመሪያ ጸንቶ ይወጣል ብለን እናስባለን ተጠሪነቱ ለተቋሙ መሆን የለበትም ነው የምንለው የፍትህ መዛባት እንዳያስከትል ይህን መለየት አለብን የሚል አቋም አለን "ሲሉ አክለዋል።
#TikvahEthiopia
@TikvahethMagazine