"በሰቆጣ ቃልኪዳን እስካሁን መድረስ የቻልነው ሀገሪቱ ካሏት ወረዳዎች ከአንድ አራተኛ በታች ነው " - ዶ/ር ሲሳይ ሲናሞ
በኢትዮጵያ በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክንያት በእድሜያቸው ሊደርሱበት የሚገባው ቁመት ላይ ያልደረሱ ወይም መቀንጨር ያጋጠማቸው ህጻናት ቁጥር 39 በመቶ ሲሆን 11 በመቶ ህጻናት ደግሞ መቀጨጭ እንዳጋጠማቸው ጥናቶች ያመላክታሉ።
ይህንን ሃገራዊ የህጻናት የመቀንጨር ምጣኔን ለመቀነስ እየተሰሩ ካሉ ስራዎች ውስጥ የሰቆጣ ቃልኪዳን አንዱ ነው።
ይህ ቃልኪዳን የህጻናትን የመቀንጨር ምጣኔ መቀነስ ቢችልም እየተተገበረ የሚገኝባቸው ወረዳዎች ቁጥር ግን ሃገሪቱ ካሏት አጠቃላይ ወረዳዎች ሩቡን ያህል ብቻ መሆኑን በሰቆጣ ቃልኪዳን የፌደራል ፕሮግራም ማስፈጸሚያ ክፍል ሲኒየር ፕሮግራም ማናጀር የሆኑት ዶ/ር ሲሳይ ሲናሞ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
የመቀንጨርን ምጣኔን በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ 2022 ዜሮ ለማድረስ ታቅዶ እየተሰራበት ያለው የሰቆጣ ቃልኪዳን በአሁኑ ሰዓት በ 334 የኢትዮጵያ ወረዳዎች ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።
ቃልኪዳኑ የሁለተኛ ምዕራፍ የአምስት አመት የማስፋፊያ ትግበራ ላይ ነው።
ዶ/ር ሲሳይ "ሃገራዊ የመቀንጨር ምጣኔ መረጃው 39 በመቶ ነው። እንደ ሰቆጣ ቃልኪዳን በአርባ ወረዳዎች ጀምረን ገና ዘንድሮ ነው 334 ወረዳዎች መድረስ የቻልነው" ሲሉ ገልጸዋል።
ይህም በሀገሪቱ ካሉ ወረዳዎች አንድ አራተኛ በታች ነው የሚሉት ዶ/ር ሲሳይ፥ "የኢትዮጵያ ወረዳዎች ከ 1,100 በላይ ናቸው የሰቆጣ ቃልኪዳንን ተጽዕኖ ለማየት በጣም ብዙ ስራ መስራት አለብን" ብለዋል።
ለዚህም ተግባራዊ የሚሆንባቸውን አካባቢዎች ከፍ አድርገን በርካታ ወረዳዎችን ካልደረስን ይህንን ሀገራዊ ቁጥር በፍጥነት መቀነስ አንችልም፤ ነገር ግን በልዩነት ይሄ ሥራ በተሰራባቸው አካባቢዎች ተስፋ ሰጪ ውጤት አለ ሲሉ አክለዋል።
የሰቆጣ ቃልኪዳን ከ 7.8 ሚሊየን በላይ የሆኑ ህጻናትን እስከ 2022 ዓ/ም ድረስ ከመቀንጨር በመታደግ ሙሉ እድገታቸው ተመጣጣኝ እንዲሆን ለማድረግ በ 2007 ዓ/ም ቃል የተገባበት ስምምነት መሆኑ ይታወቃል።
@tikvahethmagazine