በኡጋንዳ በኢቦላ የተያዙ ሰዎች ወደ ዘጠኝ ከፍ ማለቱ ተገለፀ
በኡጋንዳ በኢቦላ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ ዘጠኝ ከፍ ያለ ሲሆን 265 ሌሎች ሰዎች ደግሞ በኳራንቲን ውስጥ ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን የጤና ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።
ስምንት ታካሚዎች “የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው ሲሆን በጥሩ ሁኔታ ላይ ናቸው” ሲል የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ገልጿል።
ከእነዚህ ውስጥ ሰባቱ በዋናው የህዝብ ሆስፒታል በካምፓላ ሲገኙ አንዱ በምስራቃዊ ምባሌ አውራጃ ውስጥ እየታከመ ነው ሲል ሚኒስቴሩ ገልፀዋል።
ካምፓላ ወደ 4 ሚሊዮን የሚጠጋ ከፍተኛ ተንቀሳቃሽ ህዝብ ያላት ሲሆን ባለሥልጣናት አሁንም የወረርሽኙን ምንጭ እየመረመሩ ነው።
እስካሁን አዲስ በተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ከተያዙ ዘጠኝ ሰዎች ውስጥ የአንድ ሰው ሞት ተመዝግቧል።
Credit: AP News
@tikvahethmagazine