🟢 "ቤንዚን በ8 ቀን አንደዬ ብቻ ነው የምንሞላው፣ የባንክ ብድራችንን መክፈል አልቻልንም፣ ቤተሰቦቻችን ችግር ላይ ናቸው " - የደሴ ከተማ የቤንዚን ተጠቃሚ ታክሲ አሽከርካሪዎች
🟢 "ተራ አስከባሪዎችን በከተማዋ ሙሉ በሙሉ እንዳይሰሩ ታግደዋል" - የደሴ ከተማ ንግድ ቢሮ
የከተማ አስተዳደሩ የቤንዚል ተጠቃሚ ታክሲዎች በስምንት ቀን አንድ ቀን ብቻ ያውም 50 ሌትር እንድንሞላ በማድረጉ ቤተሰቦቻችን ችግር ውስጥ ናቸው ሲሉ የደሴ ከተማ አሽከርካሪዎች ቅሬታ አቅርበዋል።
የቤንዚን እና የነዳጅ አቅርቦት ችግር በአገር አቀፍ ደረጃ መኖሩ የሚታወቅ ነው ያሉት የደሴ ከተማ ንግድ ቢሮ መምሪያ ሃላፊ አቶ ዮናስ እንዳለ በደሴ ከተማም የአቅርቦት ችግር መኖሩን ገልፀዋል።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ በዝርዝር ምን አሉ?
"እኛ የቤንዚል ተጠቃሚ ታክሲ አሽከርካሪዎች በደሴ ከተማ 18 ነን የከተማ አስተዳደሩ በ8 ቀን አንድ ቀን ብቻ ቤንዚን መሙላት እንድንችል በማድረጉ በወር ውስጥ ለ4 ቀን ነው መስራት የምንችለው" ብለዋል።
በተጨማሪም "ለከተማው ንግድ ቢሮ ቅሬታ ስናቀርብ 'የቤንዚል እጥረት አለ ይለናል' ነገር ግን በከተማችን በየመንገዱ በጥቁር ገበያ ቤንዚን ሲቸረቸር በስፋት ይስተዋላል" ሲሉ አብራርተዋል።
"መኪኖችን የገዛነው በባንክ ብድር ነው፤ አሁን ላይ በየወሩ ለባንክ የምንከፍለውን ብድር መክፈል ባለመቻላችን ባንኮች ማስጠንቀቂያ እየሰጡን ነው ሲሉም" አክለዋል።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ፥ በተደጋጋሚ ለከተማ አስተዳደሩ፣ ለንግድ ቢሮ እና ለብልፅግና ፅህፈት ቤት ቅሬታችንን አቅርበናል፤ ምላሽ የሰጠን አካል ግን የለም ሲሉ ያሉበትን ችግር አስረድዋል።
ስሙን መግለፅ ያልፈለገው አሽከርካሪ ከጥቅምት ወር ጀምሮ እስካሁን ቤንዚል በሳምንት አንድ ቀን ብቻ ከማደያዎች መቅዳት እንድንችል ተደርገናል ሲል ተናግሯል።
አያይዞም ፥"እኔ መኪናውን የገዛሁት 280 ሺ ብር ከባንክ ተበድሬ ነው እሱን የምከፍለው እየሰራሁ በየወሩ ነበር አሁን ግን ያበደረኝ ባንክ ብድርህን በየወሩ መክፈል አልቻልክም ብሎ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶኛል" ሲል ገልጿል።
የደሴ ከተማ ንግድ ቢሮ መምሪያ በጉዳዩ ላይ ምን አለ ?
የደሴ ከተማ ንግድ ቢሮ መምሪያ ኃላፊ አቶ ዮናስ እንዳለ በምላሻቸው ተሽከርካሪዎች ለከተማችን ማህበረሰብ የሚሰጡትን የትራንስፖርት አገልግሎት ታሳቢ በማድረግ የከተማ እና የኤርፖርት ታክሲዎች በ 8 ቀን አንድ ቀን እና ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ደግሞ በየቀኑ መሙላት እንድችሉ አድርገናል ብለዋል።
ይህም የሆነበት ምክንያት አንዳንድ አሽከርካሪዎች የሚሞሉትን ቤንዚን ለትራንስፖርት አገልግሎት ከማዋል ይልቅ በህገወጥ መንገድ እየቸረቸሩ ስላስቸገሩን እንደ ከተማ አስተዳደር ጥናት በማድግ ከክልሉ ንግድ ቢሮ ጋር በመነጋገር በተላከልን መመሪያ መሰረት ነው ሲሉ ገልፀዋል።
አሽከርካሪዎች መመሪያው ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ የተለያዩ ቅሬታዎችን እያቀረቡ ነው ያሉት ሃላፊው እኛም ቅሬታቸውን ተቀብለን ለክልሉ ንግድ ቢሮ አሳውቀናል፣ ነገር ግን ከክልሉ ቢሮ የተሰጠን አቅጣጫም ሆነ መመሪያ #የለም ብለዋል።
አያይዘውም በተደጋጋሚ ቅሬታቸውን ስላቀረብን በቅርቡ መመሪያ ይሰጡናል ብለን እንጠብቃለን። ካልሆነ ግን እንደ ከተማ ክልሉን አሳውቀን የምንወስደው አሰራር ካለ እንወስዳለን " ሲሉ አስረድተዋል።
በከተማችን የቤንዚን አቅርቦት መሰረታዊ ችግር ነው ያሉት ኃላፊው በየማደያዎች የሚሰሩ ተራ አስከባሪዎች ግር ግር በመፍጠር ያለአግባብ ገንዘብ እየተቀበሉ ችግር እየፈጠሩ ነበር ብለዋል።
ስለሆነም ለህገወጥ ችርቻሮ መስፋፋት ቁልፍ ሚኒ ስለነበራቸው አሁን ላይ ተራ አስከባሪዎችን በከተማዋ ሙሉ በሙሉ እንዳይሰሩ ታግደዋል ሲሉ አብራርተዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ ከከተማ አስተዳደር እና ከፀጥታ ሃይሎች ጋር በጋራ በመሆን በባለፈው ሳምንት በህገወጥ መንገድ ሊቸረቸር የነበረ ከ 620 ሊትር በላይ ቤንዚን በፖሊስ ቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ጠቁመዋል።
በመጨረሻም አሽከርካሪዎቹ ቤተሰብ አስተዳዳሪ በመሆናችን የሚመለከተው አካል ችግራችንን ሰምቶ በአስቸኳይ ምላሽ ይሰጠን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethmagazine