#Somalia 🇸🇴
አሜሪካ ከቀናት በፊት በሶማሊያ ሞቃዲሾ የሚገኘውን አደን አዴ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ጨምሮ በታጣቂዎች ጥቃት ሊፈጸም ይችላል በሚል Level 4 የሆነ የጉዞ ጥንቃቄ ለዜጎቿ መስጠቷን ተከትሎ ዓለም አቀፍ በረራዎች ወደ ሞቃዲሾ የሚያደርጉትን በረራ ሰርዘዋል።
የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ በበኩላቸው ይህንን በማጣጣል "ተራ ፕሮፖጋንዳ" ነው ሲሉ ይህንን የጸጥታ ስጋት ሪፖርት አጣጥለዋል። በአልሸባብ ላይ እየወሰዱት ያለውን እርምጃም ውጤታማ ሲሉ ገልጸዋል።
የሶማሊያው የመከላከያ ሚኒስትር በቅርቡ ባደረጉት ቃለመጠይቅ ላይ የኢትዮጵያ የጦር ኃይል በመካከለኛው ሸበሌ በነበረው አልሸባብን የማጥቃት ተልዕኮ የአየር ጥቃት በመፈጸም ተሳታፊ እንደነበረ ጠቅሰዋል።
የሶማሊያ የዜና ምንጮች ኢትዮጵያ ከአየር ጥቃት በተጨማሪ ወታደሮቿን ወደ ሶማሊያ ለመላክ በፌርፌር የመከላከያ ካምፕ እያስገባች መሆኑንና በሶማሊያ በመካከለኛው ሸበሌና በሂራን በሚደረገው ዘመቻ ለመሳተፍ እቅድ እንዳለ እየዘገቡ ነው።
የሀገሪቱ ደኅንነት ቢሮ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ደግሞ በዓለም አቀፍ ወዳጆች በመታገዝ በመካከለኛው ሸብሌ ክልል ኤል ባድ አካባቢ ታጣቂዎችን ማጥቃቱንና የቡድን አዛዡን ጨምሮ ተሽከርካሪዎች ማውደሙን ገልጿል።
አልሸባብ ከሞቃዲሾ በስተደቡብ ምስራቅ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን ባድማ ከተማ መቆጣጠሩን ካስታወቀ በኋላ በታጣቂ ቡድኑ እና በመንግሥት ኃይሎች መካከል በተለያዩ ቦታዎች ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደ ይገኛል።
@tikvahethmagazine