#Bundesliga 🇩🇪
በጀርመን ቡንደስሊጋ ሀያ አንደኛ ሳምንት መርሐግብር ቦርስያ ዶርትመንድ ከስቱትጋርት ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።
የስቱትጋርትን የማሸነፊያ ግቦች ቻቦት እና አንቶን በራሱ ግብ ላይ ሲያስቆጥሩ ለዶርትመንድ ብቸኛዋን ግብ ብራንድት ከመረብ አሳርፏል።
ቦርስያ ዶርትመንድ ካለፉት ስድስት የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አንዱን ነው በአራቱ ሲሸነፉ በአንዱ አቻ ተለያይተዋል።
አሰልጣኝ ኒኮ ኮቫች ዶርትመንድን እየመሩ ያደረጉትን የመጀመሪያ ጨዋታ ተሸንፈዋል።
በሌላ ጨዋታ የአምናው የሊጉ አሸናፊ ባየር ሌቨርኩሰን ከዎልፍስበርግ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።
የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?
2️⃣ ባየር ሌቨርኩሰን :- 46 ነጥብ
4️⃣ ስቱትጋርት :- 35 ነጥብ
1️⃣1️⃣ ዶርትመንድ :- 29 ነጥብ
⏩የሌሎች ጨዋታዎች ውጤት ከላይ በመስሉ ተያይዟል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe