🦋……………
ዝምታውና ግድየለሽነቱ ነገሩን ምን ያኽል እንደተለማመድነው ያሳየናል………
ኢትዮጵያ ሴት ልጆች ከሚደፈሩባት የዓለም ሃገራት ማሃል አስር ውስጥ አለችበት ……… ስሰማ አልገረመኝም ቅዱስ ሃገር ትባላለች እንጂ እንዳልሆነች ቀድሜ ካወኩ ቆይቻለው ………
የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ ስለህጉ መሻሻል ተሰብስበን እያወራን አንዷ ልጅ ህንድ ውስጥ በ 24 ሰዓት ውስጥ ከሰባ በላይ ሴቶች እንደሚደፈሩ እያወራችልን በመሃል ግቢ ውስጥ "ኦ ሃይማኖተኛ እኮ ነው" ሚባለው ልጅ ጣልቃ ይገባና
"ካላቸው የህዝብ ብዛት አንፃር ትንሽ ነው እንደውም " ብሎ ሲናገር ሌሎቹ ሲያማትቡና ሲደናገጡ አይቼ ነበር ፣ እኔ ግን አልገረመኝም
ሲጀምር እዝች ሃገር ላይ ያሉ የእምነት ተቋማት ስለእርስታቸውና ስለወንበራቸው ሲቆሙ በዘመኔ አይቻለው ነገር ግን እንደተቋም የአንዲት ሴት በደል ስለወለደው እንባ ትንፍሽ ሲሉ አልተመለከትኩም ……
' የሃይማኖት ሃገር ናት' ከምትባል ሃገር ውስጥ ብዙ ደፋሪዎችን ከልላና ተንከባክባ አወድሳ እንደምትኖር መስማት ባያስገርምም መታለል ግን ያማል !
ነፍሴን እርር ያረጋት ደሞ የህፃን ሔቨንን በአሰቃቂ ሁኔታ መደፈርና መገደል በአንድ በኩል ለፖለቲካዊ አጀንዳ መጠቀምያ አርገው የሁለት ጎራ የብሔር ፍጅት መፍጠሩን ሳይ፣ በሌላ በኩል ደሞ "አንዲት ዶሮ እንቁላል መውለዷን" እንኳን ሳይቀር ትልቅ ሽፋን የሚሰጡ ሆድ አደር ሚዲያዎች ሳይቀሩ ቀባ ቀባ አርገው ማለፋቸው ስመለከት ፣ በዚህ በኩል ደሞ አንድ አንዱ ለዮቱዮብ መሸቀያ በሌላው ስቃይ ሲቀልድ ሳይ ከአንዲት ሴት ህይወትና ክብር በላይ አንድ የበሰበሰ የሃጥያት ወንበር ዋጋ አለው የሚል መልዕክት አይቻለው ፣ ሃገሪቷ ምትመራው ፣ ስትመራ የነበረው ፣ በቀጣይም ምትመራው በእንደዚህ የወደቀ አስተሳሰብና ቁሽሽና በተሞሉ አመራራሮች ስለሆነ አስር ውስጥ መግባታችን አይግረማቹ !
እኔ ግን አሁንም ለታናናሾቼም ሆነ ፣ለታላላቆቼ ሴቶች ለራሴም ጭምር ይኼን እላለው ፣……………:
:
"የበቃሽና ጠንካራ ሴት ሁኚ በዙርያሽ ያሉትንም ሴቶች ጠብቂ ፣ ሃገር ምትቃናው ባንቺ ነው ፣ የራስሽ ፍርድና አቋም ይኑርሽ ፣ ሃጥያት እራስን መሆን ሳይሆን እራስሽን እንዳትሆኚ የሚጨቁኑ እጆች ላይ ነው ያለውና ያን እጅ ሰብረሽ ቁሚ !……… ምታፈቅሪውን፣ ምታገቢውን ምትመርጪበት ፣ ወንድ ልጅሽን ሴት ልጅሽን ምታሳድጊበት መንገደሽ የበሰለ ይሁን:( ስለደበደበሽ ፣ ስለሰደበሽ ፣ ስለቀና እያፈቀርሽ ሳይሆን መጥፍያ መንገድሽን እየቆፈረልሽ ነው እና ምርጫሽ ጤነኛና ሰላማዊ የፍቅር ምርጫ ይሁን : ስላፈቀርሽው ብቻ አታግቢው የሰውነት ስብዕናው ያልተጓደለና ለሰውነት ትልቅ ዋጋ ያለው መሆኑን አረጋግጪ ፣) ጤነኛ ልጆች በመረጥሽው ጤነኛ ትዳር ላይ ይመሰረታል ! ጤነኛ ቤተሰብ ደሞ ጤነኛ ሃገር ይሰራል !
………… ምን ልልሽ ነው ቁልፉ በእጃችን ነው !
ምን አልባት ያን ፍትሕ አንድ ቀን ታመጪው ይሆናል በራስሽ ታላቅነት ውስጥ ፣ አሁንም ቢሆንም ግን በብዙ ጠላቶች ተከበሽ ቢሆንም ስለራስሽ መጮኽ እዳታቆሚ !! "
ፍትሕ !!!
ፍትሕ በአሰቃቂ ሁኔታ ተደፍረው ህይወታቸውን ላጡ ሴቶች ፣ ህፃናት !
ፍትህ ተራቸውን ለሚጠብቁ በፍርሃት ለተደበቁ ሴቶች ፣ ህፃናት !
ፍትሕ ጓዳው የደበቃቸው እንባቸው ደም ሆኖ የስቃይ ድምፅ ለሚያሰሙ ሴቶች !
ፍትሕ !!