ኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር(አቡ ዓማር) dan repost
ውድ አንባቢያን እንደሚታወቀው አላህ (ሱብሀነሁ ወተዐላህ) በእዝነቱ የሰው ዘር ሁሉ የበላይ የነብያት ሁሉ አለቃና መደምደሚያ ፍጡራንን ከፈጣራ የሚያስተዋውቁ ለአለም እዝነት የተላኩ የሰው ልጅን ከሽርክ ጨለማ ወደ ተውሂድ ብርሃን የሚያወጡ አላህን እንዴት ማምለክ እንዳለብን በታላቅ ትህትና የሚያስተምሯቸውን መልክተኛ ልኳል፡፡እሳቸውም ለዑማው ምንንም ሳያስቀሩ ግልፅ ባለ መልኩ አስተምረዋል ስለዚህ እኛም የአላህ ውዴታ አግኝተን ጀነት ለመግባት የምንፈልግ ከሆነ የሳቸውን ፈለግ ስንዝር በስንዝር እርምጃ በእርምጃ መከተል ይኖርብናል ፡፡
ታዲያ ይህንን ለማረጋገጥ (ለማግኘት ) ደፋ ቀና ስንል ከሸሪዓ ጋር በስድስት ነጥቦች መከተላችን መግጠም እና መጣጣም አለበት እነሱም፡-
👉1.ምክኒያት (السبب) ፡- የምንተገብረው ተግባር በምክንያቱ ላይ ሸሪዓን የገጠመ መሆን አለበት፡፡ ለምሳሌ፡- አንድ ሰው ቤት በገባ ቁጥር ሁለት ሪአዓ ቢስዓድና ሰላቱንም ሱና ብሎ ቢይዝ ይህ ተግባሩ በሸሪዓ እይታ መሰረት ቢስና ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው፡፡ ምክኒያቱም ሰላቱ ዒባዳ ሲሆን ቤት መግባቱ ግን ሁለት ረከዓ ለመስገድ በሸሪዓ ምክንያት አልተደረገም፡፡
👉2. አይነት(الجنس)፡- የምንተገብረው ተግባር በአይነቱ ላይ ከሸሪዓን ጋር የገጠመ መሆን አለበት ለምሳሌ አንድ ሰው ዶሮን ለኡዱሂያ ቢያርድና ተግባሩንም ሱና አድርጎ ቢወስድ ይህ ተግባሩ ከሸሪዓ ሚዛን አንፃር መሰረተ ቢስ እና ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው፡፡ ምክኒያቱም ኡዱሂያ ዒባዳ ቢሆንም ለእርድ ያቀረበውን አይነት ግን ሸሪዓ ካስቀመጣቸው ጋር የገጠመ አይደለም፡፡ ለኡድሂያን መቅረብ ያለባቸው ከቤት እንስሳት ውስጥ ግመል፣ከብትና ፍየል ናቸው፡፡
👉3 .ልክ ወይምመጠን (القدر)፡- የምንተገብረው ተግባር በልኩ (መጠን) ላይ ሸሪዓን የገጠመ መሆን አለበት ለምሳሌ አንድ ሰው እያንዳንዱ አካሉን ውዱእ በሚያደርግ ጊዜ አራት አራት ጊዜ ቢያደርግ ይህ ተግባሩ በሸሪዓ እይታ መሰረት ቢስ እና ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው፡፡ ምክኒያቱም የውዱእ ተግባሩ ዒባዳ ቢሆንም ከሶስት በላይ ጨምሮ ማድረግን የሚከለክል የአላህ መልክተኛ(ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ) ሀዲስ ስላለ ሰውየው ሸሪዓ ካስቀመጠው መጠን (ልክ)ሳይገጥም ድንበር ተላልፋል፡፡
👉4.ሁኔታ ወይም ገፅታ(الكيفية)፡- የምንተገብረው ተግባር ሁኔታው ገፅታው ላይ ሸሪዓን የገጠመ መሆን አለበት፡፡ለምሳሌ አንድ ሰው ሰላት እየሰገደ ሩኩዕ ሳያደርግ ሱጁድ ቢወርድ ይህ ተግባሩ በሸሪዓ እይታ መሰረተ ቢስና ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው፡፡ምክንያቱም ሰላት መስገዱ ዒባዳ ሆኖ የተከተለው ያሰጋገድ ሁኔታ (ቅደምተከተል)ግን ሸሪዓን ያልገጠመ ነው፡፡
👉5.ጊዜ ወይም ወቅት (الزمان)፡- የምንተገብረው ተግባር ከጊዜ አንፃር ሸሪዓን የገጠመ መሆን አለበት፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው ሰላትን ያለ ወቅቱ ወይም ኡድህያን ከኢድ ሰላት በፊት ቢያርድ ሁለቱም ተግባሮች ከሸሪዓ እይታ ተቀባይነት የሌላቸው ተግባሮች ናቸው፡፡ ምክንያቱም ሰላትም ይሁን ኡዱህያ ዒባዳ ቢሆንም ሰውየው የፈፀማቸው ሸሪዓ ባስቀመጠው ጊዜና ወቅት አይደለም ፡፡
👉6. ቦታ( المكان)፡-የምንተገብረው ተግባር ከቦታ አንፃር ሸሪዓን የተከተለ መሆን አለበት ለምሳሌ አንድ ሰው ቤቱ ወይም መድረሳ ኢዕቲካፍ ቢያደርግ ኢዕቲካፍ ከሸሪዓ ሚዛን አንፃር ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው፡፡ ምክንያቱም ኢዕቲካፍ ኢባዳ ቢሆንም ከቦታ አንፃር ግን ሸሪዓን የገጠመ አይደለም ፡፡ኢዕቲካፍ ቦታ መስጂድ ነውና፡፡
ውድ አንባቢያን በአሁኑ ሰአት የተለያዩ ሰዎች ቢድዐን ይሰሩና ለምን ይህ ተግባር ትሰራላችሁ ተብለው ሲጠየቁ ምናለበት የፈፀምነው ኢባዳ ነው ሲሉ መስማት የዘውትር ጉዳይ ሆኗል ፡፡ ነገር ግን ኢባዳ መስራታችንን ብቻ ሳይሆን መመልከት ያለብን ተግባሬ ሸሪአን ገጥሟል ወይ የሚለው ጭምር ነውና እንጠንቀቅ !!! ፡፡በቢድዐ ተግባር ላይ ደክመን እና ባዝነን ተጠያቂነት ከማትረፍ በሱና ላይ ተገድቦ መፅናቱ ትልቅ እድል ነው፡፡ደግሞስ ወደ ቢድዐ የምንሄደው ምን ያክሉን የነብዩን ሱናዎች በህይወታችን ውስጥ ተግብረን ነው ?፡፡ አላህ ሆይ ቅናቻውን መንገድ ምራን ፡፡አሚን !!!
🌲ቢድዓ በቁርኣን እና በሐዲስ ብርሀን🌲ከተሰኘው መፅሐፍ የተወሰደ፡፡