#ክረምቱን___እንጠቀምበት!
ክረምቱን ነፃ የሆናችሁ ተማሪዎችና መምህራን በምትችሉት አቅም ጊዜያችሁን ስለዲናችሁ በመማር አሳልፉት፡፡
#የሚያስተምራችሁ ካጣችሁ በድምፅ የተለቀቁ ትምህርቶችን በማዳመጥ፣ ቁርኣን በመሐፈዝ፣ መፃህፍትን በማንበብ እራሳችንን እንለውጥ፡፡
#ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡- “አላህ መልካም የሻለትን ሰው ዲኑን ያሳውቀዋል፡፡” ባይሆን የወላጆችን ሐቅ በማይጋፋ መልኩ መሆኑ እየተስተዋለ፡፡
#ማስተማር የምትችሉ ደግሞ ያላችሁን በማካፈል ላይ ተጠመዱ፡፡
ቁርኣን በደንብ የያዘ እሱን ያስተምር፡፡ ዛሬ ዛሬ ነብዩ ﷺ “ከናንተ በላጫችሁ ቁርኣንን ተምሮ ያስተማረ ነው” ማለታቸውን ብዙዎቻችን ትኩረት ነፍገነዋል፡፡
#አጫጭር የተውሒድ ኪታቦችን የቀራ ሰው ያንኑ ያካፍል፡፡
ደዕዋ ማድረግ የሚችል በተለይም በገጠር አካባቢ አቅሙ በሚችለው ሰዎችን ያስተምር፡፡
#ወላጆች ልጆቻችሁ ክረምቱን ባግባቡ እንዲጠቀሙ አግዙ፡፡ የክረምት ትምህርት የሚሰጡ መድረሳዎች ካሉ ልጆቻችሁ፣ ታናናሽ ወንድምና እህቶቻችሁ እዚያ እንዲከታተሉ አድርጓቸው፡፡
#አስተማሪዎች አመቱን ሙሉ እንደ ልብ የማታገኙት ሙስሊም እንዳለ አስባችሁ የተሻለ ጥረት ለማድረግ ተንቀሳቀሱ፡፡
#ነብዩ ﷺ “ወደ መልካም የሚያመላክት እንደሚተገብረው ሰው ነው” ማለታቸው ይታወስ፡፡ አላህ ሁላችንንም ያግዘን፡፡
ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር (ሀፊዘሁአሏህ)
https://www.facebook.com/selewa.kibebu
https://t.me/joinchat/AAAAAERyyRMpclyde0IEZw