🌹ሀያዕ የኢማን መመዘኛ🌹 dan repost
🌷ጥቅል ምክሮች ~ለሙስሊም ቤተሰብ🌷
#بسم الله الرحمن الرحيم
الحمد لله رب العالمين والعاقبة للمتقين ولا عدوان على الظالمين وصلي اللهم وسلم وبارك على نبينا محمد وعلى آله وصحبه ومن تبعهم بإحسان إلى يوم الدين
أما بعد:
①,ልጅን በተርቢያ ማሳደግ ኢስላማዊ ግዴታ እንጂ ሱና ወይም ሲፈለግ ብቻ ሚደረግ አይደለም::
,
②,ተርቢያ የሁለቱም ወላጆች ግዴታ እንጂ አንዱ ላይ ብቻ የሚጣል አይደለም::
③,ተርቢያ ስኬታማ የሚሆነው እያንዳንዱ ወላጅ የስራ ድርሻውን ሲያውቅና አንዱ በሌላው ስራ ጣልቃ ካልገባ ነው::
④, ለተርቢያ ሀብታም መሆን ወይም ድሃ መሆን መስፈርት አይደለም::
⑤,ተርቢያ ልክ እንደሌሎች ኢባዳዎች ኢኽላስ ይፈልጋል::
⑥,ተርቢያ በፍቅርና በመተሳሰብ የሚሆን እንጂ አምባ ገነንነትና ግትርነትን አይቀበልም::
,
⑦,ልጆችን በተሳካ መልኩ ተርቢያ ለማድረግ ከያንዳንዱ የእድሜ ደረጃቸው ጋር የሚመጥነውን አያያዝ ማወቅ ያስፈልጋል::
,
⑧,በልጆች መካከል ማፎካከር ወይም አንዱን ከሌላው ማስበለጥ እርስ በርሳቸው ምቀኝነት መበቃቀልና ጥላቻን ስለሚፈጥር ከባድ ጥንቃቄ ይሻል::
,
⑨, የወላጆች አለመከባበር ወይም በልጆች ፊት መወቃቀስ ልጆች ላይ አሉታዊ ተጽኖ ይፈጥራል::
,
⑩,ልጆችን መጥፎ ስድብ መስደብ ብልግና ከመሆኑም በተጨማሪ ወላጅን እንዳይታዘዙና እንዲጠሉም ያደርጋል::
,
⑪, ቁጣና ቅጣት እንዲሁም ተደጋጋሚ ምክር ልጆችን ያሰልች እንጂ አያቀናም:: ስለዚህ ከወላጅ ጥሩ ጥሩ ነገሮችን እንዲያዩ ማድረግ አልፎ አልፎ ሳይበዛ መምከር አንዳንዴም ጥፋታቸውን እንዳላዩ ሆኖ ማለፍ አስፈላጊ ነው::
,
⑫,ልጆች ላይ መጮህ አሉታዊ ተፅኖ ያሳድራል::
⑬, ልጆች ልጅ እንደመሆናቸው እንዲጫወቱና እንዲዝናኑ ማድረግ ግድ ነው:: በመሆኑም እንዳይረብሹ ወይም ልብሳቸው እንዳይቆሽሽ በማለት ከጫወታ ማገድ ከባድ በደል ነው::
,
⑭, ልጆች በትምህርትም ሆነ በማንኛውም ስልጠና አቅማቸው ሊታወቅና ከሚችሉት በላይ እንዳይሸከሙ መቆጣጠር ያስፈልጋል::
⑮, ልጆችን ተርቢያ ማድረግ ብዙ ትግል የሚጠይቅና ውጤቱ ቶሎ ላይታይ ስለሚችል ሰብር አድርጎ መቀጠል እንጂ ተስፋ መቁረጥ አያስፈልግም::
Be_Ustaz_Selsebil zumekan [Hafizehullah]
☞ https://t.me/ye_Sunnyi_Setochi_Medrek