Postlar filtri


#Update

- ኃፍረት የማይታይባቸው ናቸው በጥቂት ግለሰቦች ጥቅም ሲባል የትግራይ ህዝብ መጎዳት የለበትም
የትግራይ ህዝብ ወደ ባሰ መከራ ለማስገባት ርብርብ ላይ ናቸው።

- ትግራይ ህዝብ ሰላም ነው የሚሻው ድጋሚ ጦርነት አይፈልግም። የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ጣልቃ እንዲቀባ ጠይቀዋል።

- ይህ ቡድን ጠቅላይ ሚንስትር ጋር ቀን ከለሊት አየደወሉ ስልጣን የሚለምኑ ኃይል ነው።

"ለምንድን ነው ከትግራይ የምሸሸው? . . . እመለሳለሁ" አቶ ጌታቸው ረዳ

ጌታቸው ረዳ ከትግራይ ሽሹ ስለተባለው የሰጡት ምላሽ :


ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ያለኝን ስበሰባ ማጠናቀቅ አለብኝ። በሚቀጥሉት ቀናት ሌሎች ስብሰባዎችም አሉኝ። በሚቀጥለው ሳምንት መጀመሪያ [ወደ ትግራይ] እመለሳለሁ። ዕቅዴ እሱ ነው።

ትላንት [ማክሰኞ] ከሰዓት ከሕዝብ ጋር ውይይት እያደረግኩ ነበር። የጊዜያዊ አስተዳደሩ አጋር የሆነው የፌዴራል መንግሥቱ ስልክ ደወለልኝ።

እርግጥ ነው ሁኔታው የሚያሳስብ ነው። ፌዴራል መንግሥቱ ትግራይን የሚያስተዳድሩ ሰዎችን ስብሰባ ጠርቶ የማናገር መብት አለው።

ነገር ግን ይህ የሚባለው ነገር እንደኛው የህወሓት ክፍል ብዥታ መፍጠር ካለው ዓላማ ነው። ለውጥ ማምጣት የሚሹ ሰዎችን እኔን ጨምሮ ከትግራይ እየወጡ ነው ይላሉ።

ነገር ግን ትግራይን ሸሽቶ ወጥቷል የሚባለው ሐሰት ነው። ሕዝቡን ግራ ለማጋባት ያሰራጩት ወሬ ነው።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ አዲስ አበባ ይገኛሉ።

ፕሬዝዳንቱ በአሁን ሰዓት አዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆነው ስለ ክልሉ ሁኔታ ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጡ ናቸው።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


የየካቲት ወር የሀገሪቷ  አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 15 በመቶ መሆኑን አገልግሎቱ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ባወጣው መረጃ መሰረት የየካቲት ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 15 በመቶ ደርሷል።

ይህ አሀዝ ከጥር ወር ጋር ሲነጻጸር የ0.5 በመቶ ቅናሽ ያሳየ ሲሆን፣ በየካቲት ወር ከተመዘገበው የዋጋ ግሽበት መካከል የምግብ ነክ እቃዎች የ14.6 በመቶ ድርሻ ሲይዙ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ እቃዎች ደግሞ 15.6 በመቶ ድርሻ እንዳላቸው ተጠቁሟል ።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


❗️ጌታቸው ረዳ በትግራይ ወቅታዊ ጉዳይ ከ አሜሪካ እና አውሮፓ አምባሳደሮች ጋር መነጋገራቸውን አሳወቁ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ፣ በትግራይ እያሽቆለቆለ የመጣውን ኹኔታ መቀልበስ በሚቻልበት ኹኔታ ዙሪያ በኢትዮጵያ ከአሜሪካ፣ ብሪታንያ፣ ጣሊያን፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመንና አውሮፓ ኅብረት አምባሳደሮች ጋር ትናንት መወያየታቸውን አስታውቀዋል።

ጌታቸው፣ ውይይቱ የፕሪቶሪያ የግጭት ማቆም ስምምነት ባለድርሻዎች ዳግም በትግራይ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ማድረግ ባለባቸው ጥረቶች ዙሪያ ጭምር እንደኾነ በኤክስ ገጻቸው ላይ ገልጸዋል።

በትግራይ ዳግም ጦርነት ከተቀሰቀሰ፣ ሥውርና አፍራሽ ዓላማ ያላቸው በርካታ የቀጠናው ኃይሎች ሊገቡበት የሚችሉበት እድል እንዳለ ጌታቸው ጠቁመዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


በመቀሌ ከተማ ያለው ሁኔታ ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል።

ህወሓት በኃይል በመጠቀም ከተማዋን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል ተብሏል።

የከተማው ነዋሪዎች ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የገቡ ሲሆን፣ ከቤታቸው ለመውጣት እንኳን እየተሳቀቁ ነው።

የደብረጽዮን ገብረሚካኤል ደጋፊዎች በስፋት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ "ህወሓት ማለት የትግራይ ህዝብ ነው፣ የትግራይ ህዝብ ማለት ህወሓት ነው" የሚሉ መፈክሮችን እያስተጋቡ ነው።

ይህ ሁኔታ በከተማው ውስጥ ያለውን ውጥረት የበለጠ አባብሶታል።

በተጨማሪም፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የፌዴራል መንግሥቱ በአስቸኳይ ጣልቃ እንዲገባ እና አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ይሁን እንጂ፣ የፌዴራል መንግሥቱ እስካሁን ድረስ በጉዳዩ ላይ ይፋዊ ምላሽ አልሰጠም።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


የወንዝ ብክለት ፈጻሚዎች ላይ ከ6.7 ሚሊዮን ብር በላይ ቅጣት ተጣለባቸው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን፣ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር፣ ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቁ 24 ድርጅቶችና 3 ግለሰቦች ላይ በአጠቃላይ 6,700,000 ብር (ስድስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሺህ ብር) የገንዘብ ቅጣት መጣሉን አስታውቋል ።

ቅጣቱ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተጣለ ሲሆን፣ በተለይም አዲስ ከተማ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ እና አራዳ ክፍለ ከተሞች ከፍተኛ ቅጣት ተመላክቷል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


ብሄራዊ ክህደት ተፈፅሞብናል-ህወሃት

"በትግራይ የጸጥታ ሃይሎች የተጀመረው ህገ መንግስታዊ እና የህግ የበላይነት የማስከበር ንቅናቄ የፕሪቶሪያን የሰላም ሂደት ያከብራል እንጂ የሚጥስ አይደለም።

ሰራዊቱ እና አመራሩ የፕሪቶሪያን ስምምነት በከፈሉት መስዋዕትነት ያመጡ ሲሆን አሁንም ለተግባራዊነቱ እየታገሉ ነው። ህወሓት፣ የትግራይ ህዝብና ሰራዊት፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ተልእኮውን ለመወጣት እንዲችል በአዲስ መልክ ሊዋቀር ይገባል በማለት ወስኗል። ስለዚህ የብሄራዊ ክህደት ቡድኑ [የጌታቸው ረዳን ቡድን ነው] በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ  በትግራይ  ላይ የሶስተኛ ወገን/የፌደራል መንግሥቱ/ ጣልቃ እንዲገባ  ያቀረበው ጥሪ፣ ግልፅ ብሄራዊ ክህደት እና የፕሪቶሪያውን ስምምነት አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ በፍጹም ተቀባይነት የለውም።"

በደብረጽዮን የሚመራው ሕወሓት ዛሬ ካወጣው መግለጫ

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


የኤርትራን ጣልቃ ገብነት እና የአካባቢውን ሰላምና መረጋጋት የሚፃረሩ የውጭ አካላት ሚናን ለመግታት አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል ሲሉ በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች አስታወቁ

👉 ፓርቲዎቹ በጦር በመታገዝ የሚደረግ ይስልጣን ንጥቅያ ይቁም ሲሉም ተደምጠዋል።

የትግራይ ነፃነት ፓርቲ ፣ ባይቶናና ዓረና ትግራይ በጋራ ባወጡት መግለጫ የህወሓት ካድሬ ጄነራሎችና አጋሮቻቸው በህገወጥ መንገድ ስልጣን ለመንጠቅ እየሞከሩ ባሉበት ወቅት የክልሉ ሰላምና መረጋጋት መደ ቀወስ ውስጥ ከተውታል ብለዋል።

ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው ህገወጥ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መንግስታዊ መዋቅር ከታች እስከላይ በማፍረስ ክልሉ ወደ ከፍተኛ አለመረጋጋት እስገብተዋል ያሉ ሲሆን ይህ በግዴሌሽነት እየተፈፀመ ያለው የስልጣን ወረራ የተናጠል ተግባር ሳይሆን ከኤርትራ መንግስት ጋር በመቀናደት የተሰራ ነው ሲሉ አስታውቀዋል።

በዚህ መሰረትም አለም አቀፍ አካላትና ሁሉም የፕሪቶርያ ስምምነት ተዋናዮች በአስቸኳይ ጣልቃ እንዲገቡ እንጠይቃለን ያሉ ሲሆን ተጨማሪ ትርምስ ለመከላከልና እስከፊ ክልላዊ ቀውስን ለመከላከል ሲበላል የህግ የበላይነት መከበር አለበት ሲሉ ተደምጠዋል።

በመጨረሻም የኤርትራን ጣልቃ ገብነት እና የአካባቢውን ሰላምና መረጋጋት የሚፃረሩ የውጭ አካላት ሚናን ለመግታት አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል ብለዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር መግለጫ ትርጉም የፌደራል መንግሥቱ ጣልቃ እንዲገባ ጠይቋል።

ከጥር 15 ቀን 2017 ጀምሮ አንዳንድ የትግራይ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዦች የጠባቦችን የስልጣን ጥማት ለማርካት ግልጽ የሆነ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ይታወቃል።

በተመሳሳይ የሰሜን ምስራቅ እና ደቡብ ግንባር አዛዦች የሚመሩ ህገወጥ ድርጊቶች በዚህ ሳምንት ተጠናክረው ቀጥለዋል።

ይህንን አደገኛ መንገድ ለመግታት እና ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ሁሉ ለማስቆም የካቲት 26 ቀን 2017 ዓ.ም ለትግራይ ጦር ዋና አዛዥ የተጻፈ ትዕዛዝ ቢሰጥም የጥፋት ድርጊቱ ለሰዓታት ቀጥሏል። ሁኔታው እልባት ባለማግኘቱ የግንባሩ አዛዦች በመንግስት እገዳ ተጥሎባቸዋል። የጸጥታው ቢሮ ኃላፊም ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል።

ሆኖም በሰላማዊ ዜጎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች አሁንም ቀጥለዋል። መንግስትን ከላይ እስከታች የማፍረስ ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል። የትግራይ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዦች የኋለኛውን ቡድን ፍላጎት ለማስፈጸም መንግስትን በመበተን እና የፕሪቶሪያን ስምምነት በይፋ በመጣስ የትግራይን ህዝብ ወደ ሌላ ጥፋት እያመጡ ነው።

ያለፉትን ስህተቶች ከማረም ይልቅ ከትናንት ጀምሮ የግዚያዊ አስተዳደር አመራሮችን እያደኑ፣ እያፈኑ እና እያሰሩ ነው።

ይህም በማኅተም ስም መንግሥትን ለመጣል የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ የበለጠ ያጠናክራል። ይህ ኋላ ቀርና ወንጀለኛ ቡድን ዕድሉን ካገኘ ማፈንና ማሰር ብቻ ሳይሆን የጊዚያዊ አስተዳደር አመራርን ለሶስተኛ ወገን እንደሚያስረክቡ መረዳት ያስፈልጋል።

በሰራዊቱ አዛዦች ስም የሚካሄደው ዘመቻ ሁኔታውን ከጊዚያዊ አስተዳደር ቁጥጥር ውጪ የሚያደርግ እና እንደ ህዝብ ራሳችንን እንድንዋጋ የሚያደርግ ሃላፊነት የጎደለው እና ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው። በአጠቃላይ የትግራይ ህዝብ ከውስጥም ከውጪም; የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የትግራይ ወጣቶችና የትግራይ ሰራዊት ይህንን ሁኔታ በመረዳት አካባቢያቸውን እንዲጠብቁና በእነዚህ የሁለቱም ግንባሮች አዛዦች ላይ እንዲነሱ ጥሪውን ያቀርባል። የትግራይ ወጣቶች ባንተና በህዝባችሁ ላይ እየደረሰ ያለውን አደጋ ለመታገል በተደራጀ መልኩ አካባቢያችሁን ጠብቁ።

የትግራይ ሰራዊትም እንዲሁ የጥፋት ስርዓቱን አጥብቆ በመቃወም ህዝቦቻችሁን ከፊት ካለው ከባድ አደጋ መታደግ አለበት። የፌደራል መንግስትም በጸጥታ ሃይሎች ስም የሚንቀሳቀሱት ኋላ ቀር እና ወንጀለኛ ቡድን ተላላኪ እንጂ የትግራይን ህዝብና ጊዜያዊ አስተዳደር የማይወክሉ መሆናቸውን ሊረዳ ይገባል። የፕሪቶሪያ ስምምነት በዚህ መንገድ መፍረስ የለበትም የትግራይ ህዝብም ዝም አይልም። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በዚህ ቡድን እና አጋሮቹ ላይ ወንጀላቸውን ለመከላከል የፕሪቶሪያ ስምምነትን እየጣሱ በመሆኑ አስፈላጊውን ሁሉ ጫና እንዲያደርግ እንጠይቃለን። ይህ ካልተደረገ የትግራይ ህዝብ ማምለጥ ወደማይችልበት ሌላ የጥፋት ዙር ውስጥ ይገባል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የተባረሩት የግንባሩ አዛዦች እና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር (ሞንጄሪኖ) በመቀሌ ሰሜን ሆቴል ስብሰባ ተቀምጠዋል።

አጀንዳቸው ከፌደራል መንግስት ጋር ያለውን ግጭት ለመገምገም መሆኑን ምንጮቼ ገልፀዋል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በትናንትናው ዕለት ወደ አዲስ አበባ ተጉዘዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


አባይ ባንክ ለመቄዶንያ የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

የባንኩ ፕረዜዳንት አቶ የኃላ እንደተናገሩ ባንኩ እንደ ባንክ ላለፉት ዓመታት ከመቄዶንያ ጎን አልጠፋም ዛሬም ይህንን እርዳታ ለማድረግ ስናስብ ሰራተኛውንም እናሳታፍ በማለት ከሰራተኛው 3 ሚሊዮን ብር ባንኩ 7 ሚሊዮን ብር በአጠቃላይ 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል።

ድጋፉንም የተረከቡት ክቡር ዶክተር ቢንያም በለጠ፣ አርቲስትና ጋዜጠኛ ሰይፉ ፋንታሁን እና አርቲስት ይገረም ደጀኔ ናቸዉ።

የክቡር ዶክተር ቢንያም በለጠ ሌሎችም ተቋማት መሳተፍ እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


በዓዲጉዶምና በመቀለ ከተማ ዙርያ ንፁሀን ላይ በተከፈተ ተኩስ ጉዳት መድረሱ አቶ ጌታቸው ረዳ አስታወቁ

በተወሰኑ የጦር አዛዦች የተወሰነ የተሳሳተ ውሳኔና ህግን በጉልበት በማስፈፀም የመንግስት መዋቅር ለማፍረስ እየተደረገ ባለ ሙከራ ክልሉን አለመረጋጋት ውስጥ ከቶታል ያሉት ፕሬዝደንቱ፤ ይህንን የመንግስት መዋቅር ለማፍረስ የሚደረገውን ሙከራ በተቃወሙ ሰዎች ላይም ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተዋል ሲሉ የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ በኤክስ ገፃቸው ፅፈዋል።
ፕሬዝደንቱ በዓዲ ጉዶም ከተማና በመቀለ ዙርያ ድርጊቱን ለመቃወም በወጡ ንፁሓን ላይ በተከፈተ ተኮስ ጉዳት ደርሳልም ያሉ ሲሆን ድርጊቱ ህገወጡን የህወሓት ቡዱን ወደ ስልጣን የመመለስ እቅድ አካል መሆኑንም አስታውቀዋል። ይህም ከትግራይ ህዝብ ፍላጎትና ከፕሪቶርያ ስምምነት ተቃራኒ ነው ብለዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


ኤርትራ ለጄኔራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ መልስ ሰጠች፡፡

ጄኔራል ፃድቃን በትላንትናው እለት በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ጦርነት ሊነሳ ጫፍ ላይ እንደደረሰ ገልፀው በዚህም ትግራይ የጦር አውድማ መሆን እንደሌለባት ማስታወቃቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ለዚህ አስተያየት የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል ዛሬ መልስ ሰጥተዋል፡፡

በመልሳቸው ያሰፈሩት የመጀመሪያው ነጥብ ጄኔራል ፃድቃን ከዚህ ቀደም ኤርትራን የመውረር አጀንዳ ደጋፊ መሆናቸውን ነው፡፡

በተለይም አሰብን በሀይል ወደኢትዮጵያ ስለመጠቅለል ጄኔራሉ በራሳቸው አንደበት የተናገሩትን አውስተዋል፡፡

በሁለተኝነት ያነሱት ነጥብ ደግሞ የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት ጥሩ በነበረበት ወቅት ጭምር ኢትዮጵያ በአሰብ ላይ ይገባኛል ጥያቄ እንድታነሳ በሚስጥር ሲቀሰቅሱ እንደነበር ነው፡፡

አቶ የማነ ሲቀጥሉም "በኢትዮጵያና ኤርትራ ጦርነት ወቅት ኢትዮጵያ አሰብን ለመጠቅለል እድሉን ባለመጠቀሟ ጄኔራል ፃድቃን ተቆጭተዋል" ያሉ ሲሆን አሁን ደግሞ ሁለቱ አገራት የጦርነት ዝግጅት እንደጨረሱ አስመስለው መግለፃቸውን ጠቅሰዋል፡፡

የዚህ የትላንቱ አስተያየታቸው መነሻም የአዞ እንባ በማንባት የጦርነት አጀንዳ መቀስቀስ መሆኑን የገለፁት አቶ የማነ ይህም በኤርትራና በጎረቤቶቿ መካከል ጠላትነትን የመፍጠር ስሌት አካል ነው ብለዋል፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


ዩክሬን ከሩሲያ ጋር የ30 ቀን የተኩስ አቁም ስምምነትን ለመቀበል ዝግጁ መሆኗ ተሰማ

በሳውዲ አረቢያ ከአንድ ቀን የዩናይትድ ስቴትስ እና የዩክሬን ውይይት በኋላ በአሜሪካ የቀረበውን የ30 ቀን የተኩስ አቁም ስምምነት ዩክሬን ለመቀበል ዝግጁ መሆኗን ተናግራለች። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ዋና ፀሀፊ ማርኮ ሩቢዮ ይህንኑ ሀሳብ ለሩሲያ እንደሚያቀርቡ እና " አሁን ኳሱ በእጃቸው ውስጥ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል።የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ እንዳሉት ሩሲያ በ"አዎንታዊ" ሀሳብ እንድትስማማ የማሳመን ድርሻ የዩናይትድ ስቴትስ ብቻ ነው ብለዋል።

የማክሰኞው የጄዳ ንግግር በዜለንስኪ እና በአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሞላላው የዋይት ሀውስ ቢሮ ውስጥ ከተፈጠረው ያልተለመደ ግጭት በኋላ በሁለቱ ሀገራት መካከል የመጀመሪያው ይፋዊ ውይይት ነው።በጋራ የሁለቱ ሀገራት ተወካዮች በሰጡት መግለጫ፣ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የትራምፕ እና የዜለንስኪን ግጭት ተከትሎ ዋሽንግተን ያቋረጠችውን ለዩክሬን የስለላ መረጃ ልውውጥ እና የደህንነት ድጋፍ ወዲያውኑ እንደገና እንደሚጀምር ተናግራለች። የአሜሪካ እና ዩክሬን መግለጫ እንደሚያሳየው “ሁለቱም ልዑካን ቡድን ተደራዳሪ ቡድኖቻቸውን ለመሰየም መስማማታቸውን እና ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የዩክሬን ደህንነትን ለማስፈን ድርድር ይጀምራሉ” ይላል።

ሩቢዮ ማክሰኞ ማምሻውን በጄዳህ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሩሲያ ሃሳቡን እንደምትቀበል ተስፋ አደርጋለው ብለዋል። ዩክሬን " ተኩስ ለማቆም እና ለመነጋገር ዝግጁ ነች" ሲሉ አክለዋል። ሩሲያ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ውድቅ ካደረገች " በሚያሳዝን ሁኔታ ሰላም ለማምጣት እንቅፋት የሆነው ማን እንደሆነ እናውቃለን" ብለዋል። "ዛሬ ዩክሬናውያን የተቀበሉትን ሀሳብ አቅርበናል ይህም የተኩስ ማቆም እና አፋጣኝ ድርድር ለማድረግ ነው።"፤ "ይህንኑ ለሩሲያውያን እናቀርባለን እናም ለሰላም አዎ እንደሚሉ ተስፋ እናደርጋለን፤ ኳሱ አሁን በእነሱ ግቢ ውስጥ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


የጊዜያዊ አስተዳደሩ በሶስት ጄነራሎች ላይ ያሳለፈው የእግድ ውሳኔ ተቋማዊ አሰራርን እና ህግን ያልተከተለ ነው” - የክልሉ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በክልሉ በተለያዩ ግንባሮች አዛዦች መሆናቸው የተገለጸ ሶስት ጄነራሎችን፤ ሜጀር ጀነራል ዮሃንስ ወ/ጊዮርጊሰ፣ ሜጀር ጀነራል ማሾ በየነ እና ብርጋዴር ጀነራል ምግበይ ሀይለ በግዜያዊነት ማገዳቸውን አስታወቁ።

በፕሬዝዳንቱ የተጻፈው ደብዳቤ እንደሚያሳየው ጄነራሎቹ በግዜያዊነት የታገዱት “ከመንግስት ውሳኔ ውጭ መላ የክልሉን ህዝብ እና ወጣቱን ወደ ግርግር፣ የጸጥታ ሀይሉን ወደ  እርስ በርስ ግጭት የሚያስገባ እንቅስቃሴዎች እያደረጉ በመሆኑ ነው” ብሏል፤ የጀነራሎቹ እንቅስቃሴ “ህዝቡ ወደማይወጣው አዘቅት የሚከት ነው” ሲል አስታውቋል።

የፕሬዝዳንቱን ውሳኔ ተከትሎ የክልሉ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ “የወንጀለኞች ጠበቃ መሆን ይብቃ” በሚል ርዕስ ዛሬ መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ውሳኔውን እንደማይቀበለው አስታውቋል፤ “ያልሾመውን ያወረደ ነው” ሲል ገልጿል።

በተመሳሳይ በደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ባወጣው መግለጫ የጉዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ውሳኔን ህገወጥ ሲል ኮንኗል፤ “የትግራይ ሰራዊትን ለማፍረስ ሲያደርግ የነበረው ሴራ ወደ ከፍተኛ እና አደገኛ ደረጃ አሸጋግሮታል” ሲል ገልጿል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


"በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል በማንኛውም ቅፅበት ጦርነት ሊነሳ ይችላል"
- ሌተናንት ጄኔራል ፃድቃን ገብረትንሳይ

ጄኔራል ፃድቃን ገብረትንሳይ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል "በማንኛውም ቅፅበት ጦርነት ሊነሳ ይችላል" በማለት አስጠነቀቁ።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳም "በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል በግልጽ የሚታይ መቃቃር አለ። የእኔ ስጋት ይህ ከቃላት አልፎ ወደ ጦርነት እንዳያድግ ነው" ብለዋል።

ጦርነቱ ለቀጠናውም ዳፋ እንደሚሆንም ጄኔራል ፃድቃን በእንግሊዘኛ ባስነበቡት ጽሑፍ አስታውቀዋል።

በሁለቱ አገራት መካከል የሚደረግ ጦርነት በሁለቱም ወገኖች እንደሚባለው "አጭርና ወሳኝ" እንደማይሆን የገለጹት ጄኔራል ፃድቃን ለቀጠናው አውዳሚ እንደሚሆን ጠቅሰዋል።

"ጦርነቱ ሲያከትም አሁን የምናውቀው የአገራቱ ጂኦግራፊ ይለወጣል። በአፍሪካ ቀንድና ከቀይ ባሕር አሻግሮም ጉልህ የፖለቲካ አሰላለፍ ለውጥ ያስከትላል" ብለዋል።

በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ ያልተማከለ አስተዳደር እና ዴሞክራታይዜሽን ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ የሆኑት ሌተናንት ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳይ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የሚቀሰቀሰው ጦርነት "የሱዳንና የቀይ ባሕር ደኅንነት ላይ በቀጥታ ተጽዕኖ ያሳድራል" ብለዋል።

"በጦርነቱ ማዕከላዊ የምትሆነው በደንብ የሠለጠነና ልምድ ያካበተ ከፍተኛ የወታደር ቁጥር ያላት ትግራይ ናት" ሲሉም አክለዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት " እገዳው መሰረተ ቢስና የማይተገበር " ሲል ውድቅ አድርጎታል።

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን " አምባገነን ፕሬዜዳንት ነበር " ሲል አጣጥሏቸዋል።

ደብረፅዮን (ዶ/ር) የሚመሩት ህወሓት ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ሦስት ከፍተኛ የሰራዊት አመራሮች ላይ የወሰዱት ጊዚያዊ የእግድ እርምጃ አስመልክቶ ሌሊት መግለጫ አውጥቷል።

በዚህም ፕሬዜዳንቱ የወሰዱት እርምጃ " በሌለ ስልጣናቸው የወሰዱት የማይተገበር " ሲል በፅኑ ተቃውሞታል።

" እገዳው መሰረተ ቢስና የማይተገበር " ሲል ውድቅ ያደረገው መግለጫው ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳን " ከስልጣቸው የኋላፊነት ቦታ ማንሳቱን " አስታውሰዋል።

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን " አምባገነን ፕሬዜዳንት ነበር " ሲልም አጣጥሏቸዋል።

" የእግድ እርምጃውን የተደራጀ ሰራዊት ለማፍረስ ሲደረገው የቆየው ተንኮል አካል ነው " ያለ ሲሆን " እርምጃው አደገኛ ውጤት የሚያስከትል ነው " ሲል አስጠንቅቋል።

" መሰረተ ቢስ " ሲል የገለፀው የሦስቱ ከፍተኛ የሰራዊት አመራሮች ጊዚያዊ እግድ ፤ የሰራዊት አባላትና ህዝቡ እንዳይቀበሉት የሚል ጥሪም አስተላልፏል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


የሱዳን ጋዜጠኞች የፕሬስ ነፃነትን ለማፈን እየተወሰደ ያለውን እርምጃ ተቃወሙ

በፖርት ሱዳን የሚገኙ ሱዳናውያን ጋዜጠኞች የሳዑዲ አረቢያ ንብረት የሆነው የአልሻርክ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሱዳን መንግስት መታገዱን ተከትሎ በፕሬስ ነፃነት ላይ እየደረሰ ያለውን አፈናና የመረጃ ተደራሽነት እያሽቆለቆለ ነው ሲሉ ተችተዋል።

የአል ሻርክ የሱዳን ቢሮ ኃላፊ ካሊድ ኦዋይስ ቅዳሜ ዕለት በተካሄደው የፕሬስ ነፃነት ሲምፖዚየም ላይ እንደተናገሩት ለባለሥልጣናቱ ጥያቄ ቢያቀርብም ለጣቢያው መደበኛ የመዘጋት ምክንያት እንዳልተነገረና የመዝጋት ውሳኔው ብቻ ለጣቢያው ኃላፊዎች በስልክ ብቻ እንደተነገራቸው ተናግረዋል።

የኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር ባለስልጣናት የካቲት 20 ላይ የአል-ሻርክን ተግባራት በማገድ ስርጭች እንዲያቆም አድርገዋል። እገዳው ቴሌቭዥኝ ጣቢያው በካርቱም ውስጥ ስላለው የሰራዊት ግስጋሴ የአርኤስኤፍ አስተያየትን ያካተተ ዘገባ ካሰራጨ በኋላ ነው። የውጪ የዜና ማሰራጫዎች በግጭት ውስጥ ተደጋጋሚ ችግሮች ገጥሟቸዋል። ከነዚህም መካከል በኤፕሪል 2024 አል-አራቢያን እና አል-ሃዳትን የተሰኙ ጣቢያዎች ከፍቃድ እድሳት ጋር በተገናኘ ታግደው ነበር።

የሱዳኑ የጋዜጠኞች ቡድን ሲኒዲኬትስ ኃላፊ አብደል ሞኒም አቡ ኢድሪስ፣ ይፋዊ መረጃ አለማግኘት እና ተደራሽነት ላይ ገደብ በመኖሩ አሉባልታ እና የተሳሳቱ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያ እንዲስፋፉ ምክንያት ሆኗል ብለዋል። በህግ እና በመከባበር ላይ የተመሰረተ የፕሬስ እና የባለስልጣናት ግንኙነት እንዲኖርም ጠይቀዋል።

የአል-አራቢያ የሱዳን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሊና ያዕቆብ አል ሻርክን የማገድ ውሳኔ ሕጋዊ መሠረት የለውም ብለዋል።  የፕሬስ ነፃነትን በተመለከተ በሱዳን እና በሌሎች ሀገራት መካከል ተገቢ ያልሆነ ንፅፅር ማድረጋቸውንም ኃላፊዎቹን ነቅፈዋል። በሲምፖዚየሙ ላይ የተገኙት ጋዜጠኞች ባለሥልጣናቱ "የብሔራዊ ደህንነት" ጽንሰ-ሐሳብ ያለ ግልጽ ትርጉም እየተጠቀሙበት ነው ብለዋል።  “ብሔራዊ ደኅንነት” በሚለው ላይ ትክክለኛ ትርጉም እና ስምምነት እንዲደረግ እናም ፕሬስ ለዚህ መስፈርት ተጠያቂ እንዲሆኑ ጠይቀዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


የአሜሪካ እና ዩክሬን ከፍተኛ ባለስልጣናት በሳኡዲ አረቢያ ተገናኝተው ሊመክሩ ነው

የአሜሪካ እና የዩክሬን ከፍተኛ ባለስልጣናት ልዑካን ቡድን ጦርነቱን ለማስቆም አላማውን ያረገ ውይይት በነገው ዕለት በሳኡዲአረብያ ያካሄዳል፡፡

ባለፈው ወር በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና በዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮለዲሚር ዘለንስኪ መካከል የተደረገው ውይይት ወደ ውዝግብ ከተቀየረ በኋላ ዩክሬናውያን ከትራምፕ አስተዳደር ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማሻሻል ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳዩ ምልክቶችን የአሜሪካ ልዑካን እንደሚከታተሉ ተነግሯል፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ሩብዮ ፣ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪው ማይክ ዋልትዝ እና የመካከለኛው ምስራቅ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ለጉባኤው ወደ ጂዳ አቅንተዋል፡፡ሮይተርስ ከልዑካን ቡድኑ አባላት መካከል ስማቸውን ያልጠቀሳቸው አንድ ባለስልጣን ዩክሬናውን ከ2014 እና 2022 ድንበር ጥያቄ ባለፈ ለሰላም ያላቸውን ቁርጠኝነት መመልከት እንፈልጋለን ብለዋል፡፡

የትራምፕ አስተዳደር ኪቭ ከሞስኮ ጋር ሰላም መፍጠር የምትፈልግ ከሆነ አንዳንድ የግዛት ጥያቄዎችን መተው እንደሚኖርባት ሲናገር በተደጋጋሚ ተደምጧል፡፡የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትላንትናው ዕለት ለጋዜጠኞች ባደረጉት ንግግር ከነገው የከፍተኛ ባለስልጣንት ውይይት ፍሬያማ ውጤት እንደሚጠብቁ ተናግረዋል፡፡በዛሬው ዕለት ወደ ሳዑዲ ያቀኑት የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ በበኩላቸው “ሰላምን ለማስፈን የማደርገውን ጥረት ለመቀጠል ወደ ሳኡዲ እጓዛለሁ” ብለዋል፡፡

ዘለንስኪ የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሰላምን እንደማይፈልጉ እና ሩሲያ በዩክሬን ላይ በጀመረችው ጦርነት ግልፅ የሆነ ሽንፈት ካላስተናገደች ሌሎች የአውሮፓ ሀገራትን ታጠቃለች ሲሉ ተናግረዋል፡፡አውሮፓውን የዩክሬን አጋሮች ደግሞ ኪቭ ከሩስያ ጋር ለመደራደር ጠንካራ ቁመና ላይ መሆን እንደሚገባት እና ወደ ድርድር ጠረጴዛ እንድትገባ ግፊት ሊደረግባት እንደማይገባ ያነሳሉ፡፡ ትራምፕ በበኩላቸው ምስራቃዊ አውሮፓዊቷ ሀገር የሰው ሀይል እና ሃብት እየመነመነ እንደሚገኝ አሳስበው ከሩሲያ ጋር ለመስማማት በፍጥነት ወደ ጠረጴዛው መምጣት እንደሚኖርባት አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

 https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


የሶማሌ ክልል መንግስት የቀረበበትን “የሙስና” ክስ “ሀሰት እና ስም የማጥፋት ዘመቻ ነው” ሲል ውድቅ አደረገ!

የሶማሌ ፌዴራሊስት ፓርቲ “በክልሉ ሙስና ተንስራፍቷ፤ ፕሮጀክቶች ተንጓተዋል” ሲል ያቀረበውን ክስ የሶማሌ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ፤ “ሀሰት” እና “ስም የማጥፋት ዘመቻ” ሲል ውድቅ አደረገ።

የሶማሌ ፌዴራሊስት ፓርቲ ባሳለፍነው ሳምንት ባወጣው መግለጫ፤  “በክልሉ ለልማት ስራዎች የተመደበው ከፍተኛ ገንዘብ  አላግባብ ጥቅም ላይ እየዋለ እንደሚገኝ ገልጿል። ፓርቲው በመግለጫው “ሙሉ ክፍያ ተከፍሎ ነገር ግን ፕሮጀክቶቹ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ሳይገነቡ” እንደቀሩም ገልጿል።

የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለአዲስ ስታንዳርድ በላከው ደብዳቤ፤ “በሙስና እና ፕሮጀክቶች መንጓተት” ላይ የቀረበው ወቀሳ “መሬት ላይ ያለውን እውነታ የማያሳይ ነው” ብሏል። የህዝብ ገንዘብ አላግባብ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው በሚል በፓርቲው የቀረበውን ቅሬታ ውድቅ በማድረግ የግንባታ ስራዎች ጨረታ "በግልፅ  በጋዜጣ ታትመዋል" እና የግንባታ ስራውም በውድድር ብቁ ለሆነ የግንባታ ተቋራጭ ተሰጥቷል ብሏል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.