❗እስራኤልን ያስገረመው የያህያ ሲንዋር አስከሬን ምርመራ ውጤት❗
በዚህ ምርመራም ሲንዋር ምንም አይነት አደንዛዥ እጽ እንደማይጠቀም ተረጋግጧል ነው የተባለው።
በሲንዋር ደም ውስጥ የሃማስ ከፍተኛ አመራሮች ይጠቀሙታል ተብሎ የሚነገረው "ካታጎን" የተሰኘ አነቃቂ ንጥረነገር አልተገኘም።
እስራኤል ከዚህ ቀደም የሃማስ ተዋጊዎች በአውደ ውጊያ ብርታትን የሚጨምርላቸውንና "አምፌታሚን" እና "ቲዮፋይሊን" የተሰኙ መድሃኒቶች ውህድ የሆነውን "ካታጎን" እንደሚጠቀሙ ስትገልጽ ቆይታ ነበር።
የሟቹ ሲንዋር አስከሬን ሲመረመር ግን በደሙ ውስጥ ምንም አይነት አበረታች መድሃኒት እንዳልተገኘ የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
የመጀመሪያው የአስከሬን ምርመራ የቀድሞው የሃማስ መሪ ከመገደሉ በፊት ባሉት ሶስት ቀናት ምግብ እንዳልወሰደ አመላክቶ ነበር።
የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን በሲንዋር ጭንቅላት ውስጥ ያሉ ጥይቶች እንዳይወጡ መወሰኑን ዘግበዋል።
ጥይቶቹን በሃይል ለማውጣት መሞከር እስራኤል ለአመታት ስታሳድደው የነበረውን ግለሰብ ማን እንደገደለው ለማወቅ የሚደረገውን ጥረት ያመክናል የሚል ስጋት ፈጥሯል።
https://t.me/voa_amharic1